Site icon ETHIO12.COM

በትግራይ ከ45 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ ሰብዓዊ ድጋፍ ተሰራጨ

 – ለሥራ ማስኬጃ ከ148 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ተልኳል

በአንድ ሺህ 17 ተሽከርካሪዎች፣ 40 ሺህ 63 ነጥብ 87 ሜትሪክ ቶን ምግብ፣ 839 ነጥብ 76 ሜትሪክ ቶን መድኃኒት በ25 ተሽከርካሪዎች፣ አራት ሺህ 254 ነጥብ ስድስት ሜትሪክ ቶን ለትምህርት፣ ንጽህና መጠበቂያና ሌሎች ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች በ115 ተሽከርካሪዎች ተጓጉዟል። በተጨማሪም 413 ሺህ 552 ሊትር ነዳጅ በ10 ተሽከርካሪዎች ተጓጉዟል።

በትግራይ ክልል የሚደረገው ያልተገደበ ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲል የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። ከ45 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ ሰብዓዊ ድጋፍ ተሰራጭቷል።

የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ያልተገደበ ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህም ከፕሪቶሪያው ስምምነት ወዲህ ብቻ ከ45 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ ሰብዓዊ ድጋፍ የተሰራጨ ሲሆን፤ አጋር አካላት ለሚያከናውኑት የሰብዓዊ አቅርቦት ሥራ ማስኬጃ የሚውል ከ148 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደርጓል።

አቶ ደበበ እንደገለጹት፤ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ያልተገበደው ሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፤ እስከ ህዳር 20 ቀን 2015ዓ.ም ድረስ አልሚ ምግብን ጨምሮ በአንድ ሺህ 17 ተሽከርካሪዎች፣ 40 ሺህ 63 ነጥብ 87 ሜትሪክ ቶን ምግብ፣ 839 ነጥብ 76 ሜትሪክ ቶን መድኃኒት በ25 ተሽከርካሪዎች፣ አራት ሺህ 254 ነጥብ ስድስት ሜትሪክ ቶን ለትምህርት፣ ንጽህና መጠበቂያና ሌሎች ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች በ115 ተሽከርካሪዎች ተጓጉዟል። በተጨማሪም 413 ሺህ 552 ሊትር ነዳጅ በ10 ተሽከርካሪዎች ተጓጉዟል።

በድምሩ ከጥቅምት 20 እስከ ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባለ መረጃ በሦስቱ ኮሪደሮች (በአፋር አብኣላ፣ በጎንደር ማይጸብሪ፣ ሽሬ፤ ኮምቦልቻ፤ ቆቦ፤ አለማጣ) በአጋር አካላት የተሰማሩ ከባድ ተሽከርካሪዎች ብዛት አንድ ሺህ 168 መሆናቸውን በመጥቀስ፤ 16 አጋር አካላት 45ሺህ 157 ነጥብ 63 ሜትሪክ ቶን ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ የእርዳታ ቁሳቁስና 413 ሺህ 552 ሌትር ነዳጅ ማጓጓዝ ተችሏል ብለዋል።

አጋር አካላት በክልሉ ለሚያከናውኑት የሰብዓዊ አቅርቦት ሥራ ማስኬጃ የሚውል 148 ሚሊየን 739 ሺህ 464 ጥሬ ገንዘብ ወደ መቀሌና ሽሬ በአውሮፕላን ማጓጓዝ እንዲችሉ ድጋፍ መደረጉንም አቶ ደበበ ገልጸዋል።

አዲሱ ገረመው አዲስ ዘመን 

Exit mobile version