Site icon ETHIO12.COM

ኢሳያስ “ተንፍሰዋል” ሲሉ ስጋት መወገዱን አስታወቁ

እንደፈረንጅ የግሪጎርያኑን የቀን መቁጠሪያ የሚጠቀሙት የኤርትራ ፕሬዚዳንት በዚሁ “በነጮች አዲስ ዓመት” ተብሎ በሚጠራው ቀን ስም ” [ትህነግ] ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” አይነት ንግግር አሰምተዋል። ስጋት እንደሌለ ማስታወቃቸው እንደሆነ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሚመራው ጥምር ጦር ሽሬን መቆጣጠሩን ተከትሎ ትህነግ የወሰደውና እንዲወስድ የተመከረው ምክር ከደርግ ጋር እንደሚመሳሰል ተጠቆመ።

“ቢሆንም ቅሉ፣ የሁን እንጂ” በሚሉ መገጣጠሚያዎች አጅቦ፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ “ትንኮሳንና ጸብ አጫሪዎችን” ሲሉ በደፈናው አስታውቀው ሰራዊታቸው እንዳስተነፈሰ መናገራቸውን ቀድሞ የዘገበው ቢቢሲ ነው።

የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር (ትህነግን) በስም መጥራት ያልፈጉት ኢሳያስ ፀብ ጫሪና ተንኳሽ ሃይል መሆኑን ጠቅሰው አሁን ግን ነገሮች መቀየራቸውን አመልክተዋል። ጦራቸውን አመስግነው ” አኩሪ ተግባር ፈጽሟል አስታግሶታል” ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ


“በሕዝቡ የሚሞቅ እቅፍ ውስጥ ያለው የኤርትራ መከላከያ ኃይል ወረራ ለመፈጸም ይፍጨረጨር የነበረን ኃይል በፀረ-ማጥቃት አስታግሷል። በዚህም ኩራቴ ገደብ የለሽ ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጦራቸውን አሞግሰዋል። የት የት ግንባር ድል እንደፈጸመ ግን አላብራሩም። ቢቢሲም አልገለጸም።

በተጠናቀቀው የነጮቹ ዓመት በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ ያሉ ኤርትራውያን “ንቁ ሆነው በጽኑ አቋም የሚያኮራ ትግል አድርገዋል” በሚል ለሁሉም ምስጋና ያሉት ኢሳያስ “ወረራ ለመፈጸም  ሲፍጨረጨር” የነበረው ሃይል አደብ እንዲገዛ መደረጉን ገልጸዋል። ስም ባይጠሩም ትህነግን ለማለት እንደሆነ ግልጽ ነው። እሳቸው ግን በስም መጥቀስ እንኳን ያልፈለጉበት ምክንያት አልተብራራም።

አቶ ጌታቸው ረዳ ባህር ዳር አየር ማረፊያ ላይ ሮኬት መወንጨፉን፣ ወደ ኤርትራምና ጎንደርም በተመሳሳይ መከናወኑን ሲናገሩ ሃይላቸው ጥቃቱን እንደሚቀጥል፣ የፊደራል መንግስት የጦር አውሮፕላኖች እንደሚመቱና የሮኬት ጥቃቱ እንደሚቀጥል አስታውቀው ነበር። ኤርትራም ይህን ተከትሎ “ትህነግ የደህንነቴ ስጋት ነው” በማለት በስም ባልተተቀሱ ቦታዎች ሃይሏን አሰማርታ ከኢትዮጵያ ጎን መቆሟ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ሰራዊቱም በንብረት ማውደምና በሰብአዊ መብቶች ጥሰት ሲከሰስ ነበር።

በአሜሪካና መዕራባዊያን ጫና የምትደቆሰው ኤርትራ በሚቀጥለው ዓመትም ተመሳሳይ ጫና ሊደርስባት እንደሚችል ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አመልክተዋል። እነዚሁ ሃይላት በተደጋጋሚ ማዕቀብና ተቃውሞ በማሰማት ኤርትራን ሲኮንኑ ነበር። አሁን ላይ የኤርትራ ሰራዊት ከትግራይ መውጣቱ በውጭ ሚዲያዎች በይፋ እየተነገረም ቢሆን እነዚሁ አገራት ጫናቸውን እንደቀተሉ ነው።

Exit mobile version