Site icon ETHIO12.COM

ቻይና ለኢትዮጵያ 30 ሚሊዮን ዩዋን የእዳ ስረዛ አደረገች

ቻይና ለኢትዮጵያ 30 ሚሊዮን ዩዋን የእዳ ስረዛ ማድረጓን ገለጸች፡፡

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቼን ጋንግ ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የእዳ ስረዛውን እንደገለጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በተለያዩ ወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች መግለጫ ሰጥተዋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋንግ ጉብኝት ወቅት ሁለት አበይት ስምምነቶች መፈረማቸውን የገለፁት አምባሳደር መለስ፣ በፖለቲካው ዘርፍ በጋራ ለመስራትና ከፊል የእዳ ስረዛ ስምምነት ተፈርሟል ብለዋል።

በዚህም ቻይና ለኢትዮጵያ የ30 ሚሊዮን የሀገሪቱ ዩዋን ብድር ሰርዛለች ሲሉ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

አምባሳደር መለስ ዓለም በተጨማሪም የጀርመንና የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉብኝት የእርስ በእርስ ወዳጅነትን ማጠናከር መሰረቱን ያደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

በቀጣይም ኢትዮጵያ አሳታፊ የዲፕሎማሲ አቅጣጫን ለመከተል ዝግጅት እያደረገች መሆኗንና በአዲሱ የፈረንጆቹ ዓመት ዲፕሎማሲውን የማነቃቃት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አምባሳደር መለስ አለም ተናግረዋል። OBN

Exit mobile version