ETHIO12.COM

ታከለ ኡማን ጨምሮ አራት ሚኒስትሮች ከሃላፊነታቸው ተነሱ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት አቶ ታከለ ኦማን ጨምሮ አራት ሚኒስትሮችን ” በክብር ሸኘቸው” ሲል አስታወቀ። ከተሰናባቾቹ መካከል አንዱ አቶ ታከለ ኡማ ትናንት የመጨረሽ የስድስት ወር የስራ አፈጻጸማቸውን በጋበዟቸው የሚዲያ ሰዎች አማካይነት ለሕዝብ በሚለስል መልኩ “ሰራሁ” ያሉትን ዘርዝረዋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞግስ፤ አቶ ታከለ ኡማ፤ አቶ ኡመር ሁሴንና አቶ ተፈሪ ፍቅሬን በክብር መሸኘቱን ከማመልከቱ ውጭ ሌላ ምክንያት አልሰጠም። የሚኒስትሮች ምክር ቤት አራቱንም የምክር ቤት አባላት ቀጣይ ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆንላቸው መመኘቱ ዜናውን ይፋ ባደረገው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሀፈት ቤት በኩል ተመክቷል። በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል ተብሏል።

ጉዳዩ ከሙስና፣ ከስራ አፈጻጸም፣ ወይም ለተሻለ የስራ ሃላፊነት ወይም ክለሳ ስለመሆኑ ምንም ያልተባለለት ” ሽኝት” ቀጥይ ዜና ሊኖረው እንደሚችል ግምት አለ። ባለፈው ሳምንት የመንግስት ካቢኔ ሰማኒያ ከመቶ እንደሚቀየር ጠቅሰን መጻፋችን ይታወሳል።



የሚኒስትሮች መነሳት ጉዳይ የተለመደ ቢሆንም የአቶ ታከለ ግን ለየት ብሎ እንዲታይ አድርጎታል። የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩት ታከለ ኡማ፣ በከንቲባነታቸው ወቅት በሰፋፊ ጉዳዮች ስማቸው በሰፊ ቢነሳም የማዕድን ሚኒስትር እንዲሆኑ ተደርጓል። የአዲስ አበባ ቆይታቸው “ሃዋሪያዊ ስራ በመስራት ተጠናቋል” የሚል ማጠቃለያ ባይሰጥም፣ የሚታሙበትን ጉዳይ ሁሉ ሪፖርተር ጋዜጣ በቆይታ አምዱ ያስተባበለበት አግባብ በወቅቱ ” ነገሩ ምንድን ነው” ያስባለ እንደነበር ተመዝግቦ የተቀመጠ እውነታ መሆኑንን በርካቶች ተችተው፣ በቆይታው የተዝናኑ ጥያቄና መልሱን እየቆራረጡ የማህበራዊ ገጽ ማድመቂያም አድርገውት እንደነበር ይታወሳል። በአንዳንድ የዩቲዩብ ቻናሎችም በዚህ ደረጃ ማስተባበያና ስም መገንቢያ መድረክ የተለቀቀበትን ምክንያትም ጠቅሰው በዝርዝር መናገራቸውም አይዘነጋም።

አቶ ታከለን በቀጥታ ባይጠቅስም ሪፖርተ ምንጮች እንደነገሩት አድርጎ ለወርቅ ግዢ ከተወሰደ ስድስት ሚሊዮን ብር ውስጥ አራት ሚሊዮኑ ወርቅ እንዳልተገዛበት፣ በዚህም የተነሳ ምርመራ መጀመሩን ጠቅሶ ከስንብታቸው በፊት ዘግቦላቸው ነበር። እሳቸውም ከትናንት በስቲያ በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት የስድስት ወር የስራ ሪፖርት ቃል በቃል ዜናውን በመድገም የሳቸው የብርታት ውጤት መሆኑንን አስታውሰው አልፈዋል።

አቶ ታከለ ኡማ ልክ እንደ ባልደረቦቻቸው ሁሉ የወደፊት ኑሯቸው የተሳካ እንዲሆን በምኞት ከመሰናበታቸው ውጪ ምንም የተባለ ነገር ባይኖርም አቶ ሽመልስ አብዲሳ በቢሮ ምክትል ሃላፊነት ሊመድቧቸው ቦታ እንደተመቻቸ ውስጥ አዋቂዎች ለኢትዮ 12 አስታውቀዋል። ታከለ ኡማ ግን በተባበሩት መንግስታት ሃላፊ ሆነው እንደሚሾሙ ለወዳጆቻቸው መናገራቸውን የሰሙ እድገት እንደተዘጋጀላቸው እየጠቆሙ ነው። በስድት ወር የሚዲያ ሪፖርታቸው የተፈጥሮ ጋዝ ለማምረት ከሩስያ፣ አሜሪካና ቻይና ኩባንያዎች ጋር ንግግር መጀመሩን ይፋ አድርገዋል። ዜናውን ሲያስታውቁ የሲሚንቶ ምርት እጥረት እንጂ ዋጋ የናረበትን ምክንያትና ዋጋውን ተስማምተው ስላናሩት ኔት ዎርክ አልተናገሩም።

ዛሬ ሽኝት ተደርጎላቸው ከተባሉት መካከል አቶ ኡመር ሁሴን ኦባ እና አቶ ተፈሪ ፍቅሬ ቡሳ በቅርቡ በፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአምባሳደርነት መሾማቸው ይታወሳል።

ሽኝት ተደርጎላቸው ከተባሉት መካከል አቶ ኡመር ሁሴን ኦባ እና አቶ ተፈሪ ፍቅሬ ቡሳ በቅርቡ በፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአምባሳደርነት መሾማቸውን ይታዋስል

Exit mobile version