Site icon ETHIO12.COM

የኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ አራት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ምርት ለወጪ ንግድ ገቢ ለማበርከት አቅዷል

የኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ አራት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ምርት ለወጪ ንግድ ገቢ ለማበርከት አቅዶ እየሰራ መሆኑ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የመንግስት ሀብት ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ ገለፁ።

የክልሉ መንግስት በክልሉ ተሠማርተው የተለያዩ ምርቶችን ወደ ወጭ ሀገራት ከሚልኩ ባለሀብቶችና ከባንኮች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በውይይት መድረኩ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የመንግስት ሀብት ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ የፌዴራል መንግሥት ላቀደው የወጪ ንግድ ገቢ መሣካት የክልሉ መንግሥት የራሱን አስተዋጽኦ ለማድረግ አቅዶ እየሠራ ነው።

በክልሉ መንግሥት እቅድ መሠረትም አራት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ምርት እንደ ክልል አስተዋጾ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከፌዴራል መንግሥት የወጪ ንግድ ውስጥ የኦሮሚያ ክልል 62 በመቶ ድርሻ አለው ያሉት ዶክተር ግርማ፤ የክልሉ መንግስት ለፌዴራል መንግሥት የወጪ ንግድ እቅድ መሣካት ያያዘውን ክልላዊ ዕቅድ ከዳር ለማድረስ ባለሃብቶችና መንግስት ዕቅዶቻቸውን አስተሳስረው መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በእቅዱ መሠረት በማዕድን ዘርፍ 900 ሚሊዮን ዶላር፣ በኢንዱስትሪው ዘርፍ 300 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ አስተዋጾ ለማበርከት መታቀዱ ተመላክቷል። በፋይናንስ አቅርቦት፣ የሴክተሮች መናበብ ችግርና ኮትሮባንድ ጋር የተያያዙ ተግዳሮች በውይይቱ ላይ ተነስቷል።

የወጪ ንግድ አምራቹን ህብረተሰብ ተጠቃሚ እንዲያደርግ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራም በመድረኩ ተገልጿል።

በገመቹ ከድር ENA

Exit mobile version