ETHIO12.COM

ጃልሜዳ 13 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ተይዘዋል‼

በጃንሜዳ የከተራ እና የጥምቀት በዓል ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 13 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ዋሉ። ከተለያዩ ግለሰቦች የተሰረቁ 20 ሞባይል ስልኮችም በኤግዚቢትነት ተይዘዋል።

ከአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ጥር 10 በጃንሜዳ በተከበረው የከተራ በዓል ዕለት የስርቆት ወንጀት የፈፀሙ 5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይ 3 ሞባይል ስልክ በኤግዚቢትነት ተይዟል።

በተመሳሳይ ጥር 11 በበዓሉ ዕለት ፀበል ለመረጨት የነበረውን ግፊያ እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 8 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከተያዙት ተጠርጣሪዎች መካከል ሁለቱ በቁጥር በርከት ያለውን ሰልክ መስረቃቸውን የጠቀሰው የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አንደኛው 9 ስልኮችን በኪሱ፣ አንደኛው ደግሞ 8 ሞባይል ስልኮችን በሆዱ ደብቀው የተገኙ ናቸው።

ሞባይል ስልክ የተሰረቀባቸው ግለሰቦች በጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያው ቀርበው በማመልከታቸው ከተያዙት ስልኮች መካከል የተወሰኑት ባለቤቶቻቸው የተገኙ ሲሆን ሌሎቹን አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቀርቦ መጠየቅና ማረጋገጥ እንደሚቻል ተገልጿል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰአት ድረስ በአጠቃላይ 13 ተጠርጣሪዎች እና 20 ሞባይል ስልክ የተያዘ ሲሆን በዓሉ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እና ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ህብረተሰቡ እና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ከፀጥታ አካላት ጋር ቆመው እያሳዩት ላለው ተባባሪነት የአዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል።
(Addis Ababa polic ኢንስፔክተር ተዘራ አብሽር)

Exit mobile version