ዜና ሌብነት – ደህንነትን የሌብነት ዜና ዳር ዳር እያለው ነው፤ በማይወራረድ ብር ዘረፋ መኖሩ ተሰምቷል

ሌብነትን እንዲያመክን የተቋቋመው የፋይናንስ አገለግሎት ደህነንት ሃላፊ በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸው ይፋ መሆኑን፣ ቀደም ሲል በብሄራዊ ደህንነት የሎጂስቲክ ዋና መምሪያ ምክትል ዳይሬክተር ላይ የተከፈተውን ክስ ተከትሎ በአገር መረጃና ደህንነት አገልግሎት የማይወራረድ በሚባል ወጪ ከፍተና ሃብት እየተዘረፈ መሆኑ ሙሉ መረጃ ለአቶ ተመስገን ጥሩነህ መድረሱ ተሰማ።

የአገር ደህንነትንና መረጃ አገልግሎትን ዳር ዳር እያለ ያለው የሌብነት ዜና አቶ ተመስገን ለሚመሩት የጸረ ሙስና ብሄራዊ ኮሚቴ መፍተኛው እንደሆነ የሚጠቁሙ፣ “የማይወራረድ” በሚል አገርን ለመጠበቅ ተብሎ የሚፈሰውና የሚዘርፈው ገንዘብ ከዋናው የደህንነት ስራ ጋር ግንኙነት የለውም።

ለጊዜው ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡት ክፍሎች እንደሚሉት ይህ የማይወራረድ በሚል የሚበላው ሃብት የተለያዩ ቅርንጫፎች የተበጁለትና በውጤቱም እዚህ ግባ የሚባል ፋይዳ የሌለው፣ ታዋቂ ሰዎችን የያዙ አጨብጫቢዎች የሚንቦጫረቁበት ነው።

አቶ ተመስገን ቅድሚያ ምክትላቸው አቶ ሲሳይን ማብራሪያ እንዲጠይቁ የሚገደዱበትና መረጃና ጥቆማ እንደደረሳቸው ያመለከቱት እነዚህ ክፍሎች ምን አልባትም አቶ ሲሳይ በዚሁ ጉዳይ ላይ በቅርቡ ጥያቄው ሊቀርብባቸው እንደሚችል አመልክተዋል። በደህነት ስር በህግ እንዲዋቀር የተደረገው የፕሮፓጋንዳ ስራ በዋናነት ቀዳሚ ማብራሪያ ከሚቀርብባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ስለመሆኑ ፍንጭ አለ። በዚህ ተግባር የፓርላማ የግል አሸናፊ “ብልጽግናዎች” በአስተባባሪነት እንደሚሰሩ መረጃ አለ። ሰዎቹ በስም የተጠቀሱ ቢሆንም በተለይ አንደኛው በስማቸው እየተነገደባቸው ሊሆን ይችላል በሚል ከማተም ተቆጥበናል።

በማይታወቁ ድርጅቶችና ስሞች የሚከፈለው የማይወራረድ ገንዘብ ከፈተኛ መሆኑንን መረጃዎች ያስረዳሉ። አንዳንዴም ብር እያለቀ በላይ በላይ የሚጠየቅበት አግባብ መኖሩን ለጉዳይ ቅርብ የሆኑ እየገለጹ ነው። ይህ አጠቃላይ ተቋሙን የሚያጎድፍና ለአገር ካለው ታላቅ ፋይዳ አንጻር እንደ ዕንቁላላ የሚያዝ ድርጅት በዚህ ደረጃ እንደ ልኳንዳ ቤት በማይወራረድ ሂሳብ ሲበለት ማየት እጅግ አሳዛኝ እንደሆነ ያመለከቱት ክፍሎች ጉዳዩ በፓርላማ ለተቅላይ ሚኒስትር አብይ እንዲቀርብ አቅሙ ካላቸው ጋር እየሰሩ መሆኑን አመልክተዋል። እስከዛ መቆየት የምያቻልበት ደረጃ ከደረሰ ግን በሪፖርት መልክ ሊያቀርቡላቸው እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። የፍርድ ቤት ዜናውን ከስር ያንብቡ።

See also  ለተሳካ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር አሁንም ቁልፍ ጉዳይ ነው እንላለን (ኦፌከ)

የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ተቋም የሎጀስቲክ ዋና መምሪያ ም/ዳሪክተር እነ ተስፋዬ ደሜ በተጠረጠሩበት ከ20 ሚሊዮን ብር  በላይ የሙስና ወንጀል ክስ የመመስረቻ ጊዜ ተፈቀደ።

በተጠርጣሪዎች ላይ ዓቃቢህግ ክስ እንዲመሰርት የ10 ቀን ክስ የመመስረቻ ጊዜ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ተፈቅዷል።

የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ተቋም የሎጀስቲክ ዋና መምሪያ ም/ዳሪክተር አቶ ተስፋዬ ደሜ ጨምሮ ሌሎችም ተጠርጣሪዎች በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

ተጠርጣሪዎቹ  ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ተቋም  ትዕዛዝ ባልሰጠበት ሁኔታ ሲሚንቶ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል በማስመሰል የሲሚንቶ ወጪ በማድረግ  ለተቋሙ ሳይቀርብ  ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ለግል ጥቅም በማዋል ወንጀል መተጠረጠራቸውን ተከትሎ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና በፍትህ ሚኒስቴር በሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳሪክቶሬት ጀነራል ሲያከናውን የነበረው ምርመራ መጠናቀቁን ተከትሎ ዓቃቢህግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ የመመስረቻ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ለዓቃቢህግ ክስ መመስረት የሚያስችለውን የ10 ቀን ክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል።

ታሪክ አዱኛ

Leave a Reply