Site icon ETHIO12.COM

የአውቶቡስ ግዢ በገለልተኛ ኦዲተር ይጣራ – አዳነች አቤቤ ዋ!

“የአዲስ አበባ መስተዳድር የአውቶቡስ ግዢ በገለልተኛ ኦዲተር ይጣራ። ገለልተኛ አጣሪ ኦዲተር ይቋቋም” ይቋቋም በሚል አቶ ሙሼ ሰሙ የጻፉት አስተያየትና ያነሷቸው ነጥቦች ምላሽ ሊሰጣቸው የሚገባቸዋ መከራከሪያዎች ናቸውና “አዳነች አቤቤ ዋ” የሚል ሃረግ ጨምረን አትመነዋል። በፋና ቲቪ የቀረበው የማይሞግትና አመክንዮ ያላቸው ጭብጦችን ያላካተተ የካድሬዎች ማስተባበያ በመሆኑ ከስር አቶ ሞሼ ሰሙ ያነሱትን ጥያቄዎች በማከል አዲስ አበባ ህዝብ የመረጣችሁ ብትሹ በድርጅታችሁ፣ በትሹ በገሃድ ይህ ጉዳይ ከነሙሉ ማስረጃው አደባባይ እንዲወጣ ልትገፉ ይገባል። አለያ እናንተም ሌቦች ትሆናላችሁ። በተለይ አዳነች አቤቤ። ጽሁፍን ከስ ያንብቡ!!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዢ የፈጸመባቸው አውቶብሶች ዋጋ እጅግ አወዛጋቢ ከመሆኑ የተነሳ አስተያየት ለመስጠት እንኳን የተጸየፍኩት አጀንዳ ነበር። የአውቶብሶቹ ዋጋ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ የከተማው ነዋሪ ያስደነገጠ፣ ግራ ያጋባና ዘረፋ ለይቶለት ነፍስ ዘርቶ ስጋ ነስቶ በቅ ብሏል ያሰኘ አነጋጋሪ ክስተት ሆኖ ሰንብቷል።

የአውቶቡሰሰ ግዢውን በሚመለከት ከተለያየ ገለልተኛ አካላት በሚቀርብላቸው መረጃ መሰረት የከተማችን ነዋሪዎች በከፍተኛ ደረጃ የመዘረፍና የመነጠቅ ስሜት አድሮባቸዋል። ተመዝብሯል የሚባለው የአውቶብሱ ግዢ የተፈጸመው ላባቸውን አንጠፍጥፈውና ከልጆቻቸው ጉሮሮ ነጥቀው ለጋራ ልማት ከሚገብሩት ግብር ላይ ተዘግኖ ስለሆነ ቁጭታቸው ፍትሐዊና ጥያቂያቸውም መልስ ከገለልተኛ አካል የሚሻ ጉዳይ ነው ።

የከተማዋ አስተዳደርም መረጠኝ ለሚለው ነዋሪ ታማኝነቱ የሚረጋገጠው ከቀረበለት ጥያቄ እራሱን ከመጋረጃ በስተጀርባ ደበቆ ወፈ ሰማይ ካድሬ በማሰማራት ሀቁን በርብርብ በማድበስበስና ሕዝብን ለማሸማቀቅ በመሞከር ሊሆን አይገባም።

ጥያቄው ከሕዝብ የመነጨ የሕዝብ ጥያቄ ነው። ገለልተኛ አጣሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ የጨረታ ሂደቱ፣አሸናፊው የተመረጠበት መስፈርት፣ ተገኘ የተባለው የውጭ ምንዛሪ ምንጭ፣ የአውቶብሶቹ ዋጋና የጨረታ ኮሚቴው ገለልተኝነት ወዘተ ኦዲት ሊደረግ ይገባል። ሂደቱ ኦዲት ተደርጎና ሀቁ ተጣርቶ ውጤቱ በግልጽ ለሕዝብ መቅረብ አለበት።

ይህ ሳይሆን ቀርቶ መርጦናል የምትሉት ሕዝብ ላቀረበው ፍትሐዊ ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለትና በካድሬ ትርክት ጥያቄውን ለማድበስበስ መሞከር ጥርጣሬውን በሐቅ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ከማረጋገጥና ብሶትና ጥላቻውን ከማባባስ ውጭ ፋይዳ ቢስ ጥረት ነው።

ይህ ደግሞ ለዘመናት የለመድነው “የምን ታመጣላችሁ” ማን አለብኝነት ስለሆነ ጊዜ ይፍጅ እንጂ ትናንት በሌላው ላይ የጠቆመ ጣታችሁ ተራውን በራሳችሁ ላይ ጠቁሞ በሙስና እንደሚፋረዳችሁና ታሪክ እራሱን እንደሚደግም ጥርጥር የለኝም ?!

በመሰረታዊነት የሚነሱና ሕዝብን ለበቂና አስተማማኝ ጥርጣሬ ከሚዳርጉ መነሻዎች በጥቂቱ

-ቻይና ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባላት ኢኮኖሚያው ትብብርና (Bilateral ) የሁለትዬሽ የንግድ ግንኙነት መሰረት ቀጥታ ከአምራቹ ጋር ተደራድሮ አውቶብሶቹን መግዛት እየተቻለ ከሁለተኛ አቅራቢ መገዛቱ ?

Mushe Semu

Exit mobile version