Site icon ETHIO12.COM

ለፍትህ ሽግግር ምስረታ በሚዘጋጁ መደረኮች ህዝብ በንቃት አንዲሳተፍ መንግስት ጥሪ አቀረበ

የሽግግር ፍትህ ስርዓትን መተግበር ለሰብአዊ መብቶች መከበርና ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ እጅግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ ገለጹ፡፡

በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት የተፈጸሙ ጉልህ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ቁርሾዎች አግባብነት ባለዉ ሁለንታናዊ የተቀናጀና አሳተፊ የሽግግር ፍትህ ሂደት መፍታት ጠቃሚ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊ አዉዱ ይህ እውን እንዲሆን ያመለክታል ሲሉ ዶክተር ለገሰ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተከሰቱ ጉልህ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ በደሎች፣ ዝንፈቶች፣ ቁርሾዎችና ኢ-ፍትሃዊነቶችን እዉነትን፣ ፍትህን፣ ሰላምንና እርቅን መሰረት ባደረገ ሁሉን አቀፍ የሽግግር ፍትህ ስልት እንዲፈቱ ማድረግ ለዘላቂ አዎንታዊ ሰላም ግንባታ፣ ለዘላቂ ልማት፣ ለማህበራዊ ትስስርና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ሚናዊ አይተኬ መሆኑንም ነው ያመላከቱት፡፡

ይህ ስኬታማ እንዲሆን አሳታፊ፣ ተጎጂዎችን ማእከል ያደረገ፣ የዓለም አቀፍ ልምዶችና መርሆዎችን ያከበረና የሀገራችንን ነበራዊ ሁኔታን መሰረት ባደረገ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲመራ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

ለዚህም ሲባል የሽግግር ፍትህ የፖሊሲ ማዕቀፍ አማራጮችን የሚያመለክት ረቂቅ ሰነድ በፍትህ ሚኒስቴር በኩል ተዘጋጅቶ ለህዝብ ዉይይት መቅረቡን ነው ዶክተር ለገሰ ቱሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የገለጹት፡፡

በቀረቡ አማራጮች ላይ ተመሳሳይ የአላማ አንድነት እና አረዳድ ለመፍጠርና ግብዓት ለማሳሰብ እንዲቻል በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ከሃምሳ ባለይ ከተሞች ምክክሮች ማካሄድ ተጀምረዋል ነው ያሉት፡፡

የሁሉም ዜጎች ንቁ ተሳትፎ በእጅጉ አስፈላጊ በመኾኑ በየከተሞቹ በሚፈጠሩ መድረኮች በመገኘት የድርሻችንን እናበርክት ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Exit mobile version