Site icon ETHIO12.COM

ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም !

እኚ እናት ወ/ሮ ዘንባቤ ጫላ ይባላሉ ። ለበርካታ አመታት በመድኃኒት ፋብሪካ በመስራት ባጠራቀሙት ገንዘብ ከ11 አመት በፊት ቤት ሰርተው ትዳር መስርተው ይኖሩ ነበር ። ሆኖም ትዳራቸው ሰምሮ ከአጋራቸው ጋር አብሮ ለመኖር ልጅ መውለድ ባለመቻላቸው ምክንያት እና ባል ከሌላ ለሚወለዱ ልጆቹ ከጀርባ በኩል ያለው ቤት ይሰጣቸው በሚል አለመግባባት ወደ ፍቺ ያመራሉ ። ባል ያለፋበትን ፣ ያልደከመበትን እሳቸው ዘመናቸውን ሙሉ የደከሙበትን ከትዳር በፊት የሰሩትን ንብረት ይገባኛል ፤ ሲል ፍርድ ቤት ከሶ የድርሻውን በመውሰድ ቀሪውን ደግሞ በጉርብትና አልኖርም በማለት ወይዘሮ ዘንባቤ ሸጠው ሁለት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ቤት በመግዛት አንዱን በማከራየት በክራዩ ገቢ ኑሮቸውን ይደጉሙ ጀመር ።

ከለታት አንድ ቀን በሀይማኖት ከሚመስሎቸው ጓደኛቸው አንድ ሀሳብ መጣ ። ይህው “ቤት ውስጥ ብቻዎትን ከሚኖሩ ከጎን ያለችውን ሶስት በአራት የሆነችውን ክፍል ለምን አከራይተው አንድም ገቢ ያገኛሉ ሁለትም የሚያናግሮት ፣ የሚጫውቶት ሰው ያገኛሉ ። ” ትልና ሀሳብ ታቀርባለች ። እውነት ነው ። ብለው በጓደኛቸው ሀሳብ የተስማሙት ወ/ሮ ዘንባቤ ተከራይ አግኝቼልሻለሁ በማለት ሀሳቡን ያቀረቡ ጓደኛቸው በቸርች የምታውቃትን ሴት እንድትከራይ ያደርጋሉ ።

ወ/ሮ ዘንባቤ ቸርች በመሄድ የአምልኮ ስርዓት ይፈፅሙ የነበረ ቢሆንም ተከራይታ የገባችው ሴት እኔ አገልጋይ ነኝ በማለት ቤት ውስጥ ታገለግላቸው ጀመረ ። ትፀልይላቸዋለች ፣ መልዕክት ታመጣላቸዋለች ፣ ዘይት ትቀባቸዋለች ፣ ትንቢት ትተነብይላቸው ጀመረ ። ወይዘሮ ዘንባቤ ሁሉን እውነት ብለው በመቀበል ቸርች መሄድን እርግፍ አድርገው በመተው በቤታቸው የሚሆነውን ነገር ለቤተሰቦቻቸው ሳያማክሩ ይቀጥላሉ ።

ወይዘሮ ዘንባቤ ከለታት በአንዱ ቀን እንዲህ ሲሉ ለምትፀልይላቸው ተከራያቸው ውስጣቸው ያለውን ሚስጥር ያካፍላሉ ። ” ስሞት እሩቡን ለቤተክርስቲያን እንዲሰጥልኝ እፈልጋለሁ ። ” ሲሉ ለቤተሰቦቻቸው ያልተናገሩትን የራስ ሚስጥርን በየዋህነት ላመኖት አገልጋይ ተከራይ ሀሳባቸውን ያካፍላሉ ።

አገልጋይ ነኝ ባዬ ይቺን ፍንጭ ትይዝና ዘወትር ምሽት ላይ “አንቺ ትሞቻለሽ ፣ የሞት ድምፅ እየሰማሁ ነው ። ” በማለት ከጌታ የተሰጠ መልዕክ ነው ። በሚል በወይዘሮ ዘንባቤ ላይ የፍራቻ ፣ የድንጋጤ ስሜትን መዝራት ትጀምራለች ። እናም እንዲህ ትላቸዋለች ያው “እኔ የእግዚያብሔር አገልጋይ ነኝ ስለዚህ ስትሞቺ ለኔ ብትሰጪኝ ለቤተክርስቲያን እንደሰጠሽ ይቆጠራል ። ” ትላቸዋለች ይሄኔ ሁሉን እውነት ነው ብለው የተቀበሉት እኚ ወይዘሮ አንዱን ቤት ሸጠው ለተከራያቸው ቅሊንጦ አካባቢ በለ አንድ ኮንዶሚኒየም በስሞ ይገዙላታል ። በተረፈው አምስት መቶ ሺ ብር ደግሞ ለእሳቸው ኮዬ ፈጬ እስቱዲዬ ይገዙና ያከራያሉ ።

በዚህ ያላበቃው የአገልጋያቸው ጉድ” ክራይ ለመቀበል ኮዬ ድረስ ከሚሄዱ ለኔ ሙሉ ውክልና ይስጡኝና እኔ ቤቱን አስተዳድረዋለሁ ።” ብላ ሙሉ ውክልና ትወስድና ቆዬ ፈጬ የገዙትን ቤት በ150 ሺ ብር እንደተሸጠ አድርጋ አካውንታቸው ላይ እንዲገባ ታደርጋለች ።

መልሳም መረጃና ማስረጃ እንዳይኖርባት ይሄንኑ 150 ሺ ብር በካሽ ሃምሳ ሃምሳ ሺ ብር እያወጡ በእጆ እንዲሰጦት ታደርግና ወደ ራሷ አካውንት ታስገባለች ።

የሰውን ለብ እና እንባ እንደ ተራ ነገር የቆጠረችው አገልጋይ ተብዬ ወይዘሮ ዘንባቤን ባዶዎቸውን ማስቀረቷ ሳያንስ አሁን ያሉበትን ቤት በስጦታ እንዲሰጦት በማድረግ ቤቱን በስሞ አስደርጋለች ።

በአሁን ሰዓት አገልጋይ ተብዬ ሶስት በአራት በሆነችው ቤት ውስጥ እየኖረች ሲሆን ወይዘሮ ዘንባቤ ደግሞ ዋናው ቤት ላይ እየኖሩ ይገኛሉ ። ነገር ግን ቤቱ በስጦታ መልክ ለአገልጋይ ተብዬ በህጋዊ መንገድ ተሰጥቷታል።

የህግ ባለሙያዎች ይሄን ጉዳይ ከህግ አንፃር እንዴት ይታይ ይሆን ሙያዊ ሀሳባችሁን አካፍሉን ።

የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዬች ፣ ፓስተሮች ፣ መጋቢዎች ለሀይማኖታችሁ ቀናኢ የሆናችሁ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ትላላችሁ ?

ወዳጄ ፣ ጓደኛዬ ጋዜጠኛ አለምሰገድ ታደስ ሁሌም አስገራሚ ታሪኮችን በሬዲዬ በእርቅ ማዕድ ፕሮግራም እና በኢዬሀ ሚዲያ ዩቲዩብ ቻናል ለምታካፍለን አስተማሪ ታሪኮች አክብሮቴ ባለህበት ይድረስልኝ ።
Tariku zewdu

Exit mobile version