Site icon ETHIO12.COM

ለ185 ቀናት በጠፈር ላይ የቆየዉ ሩሲያዊው በኢትዮጵያ ልምዱን እያካፈለ ይገኛል

ለ185 ቀናት በጠፈር ላይ የቆየዉ ሩሲያዊው ጠፈርተኛ ሰርጌ ሰቨርቺኮቭ በህዋ ሳይንስ ያካበተውን እውቀት እና ልምድ ለኢትዮጵያ ምሁራን እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አጋርቷል፡፡

የሩሲያን የህዋ ሳይንስ መልካም ልምድ መቅሰም የሚያስችል የልምድ ልውውጥ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል፡፡

መርሐ ግብሩ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ፣ በኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና በአዲስ አበባ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን የዘርፉ ምሁራን እና የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በልምድ ልውውጡ ተካፍለዋል፡፡

የስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለዘርፉ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኗ አስረድተዋል፡፡

ለተጀመረው ስራም የሩሲያ ልምድ እና አጋዥነት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል፡፡

የጠፈርተኛው ልምድ ማጋራትም ኢትዮጵያ ነገ በርካታ የህዋ ሳይንስ ተመራማሪ እንድታፈራ ያነቃቃል ብለዋል።

ዕውቁ የሩሲያዊ ጠፈርተኛ ሰርጌይ ኩድ ስቨርቺኮቭ ከጠፈር ላይ የወሰደውን የዳሎልን ምሥል በአዲስ አበባ ተገኝቶ ለኢትዮጵያውያን ማስረከቡ ይታወሳል።

ሰርጌይ ኩድ ስቨርቺኮቭ ከጠፈር ላይ የወሰደውን የዳሎልን ምሥል በአዲስ አበባ ተገኝቶ ለኢትዮጵያውያን ማስረከቡ ይታወሳል።

በአባቱ መረቀ – ethio fm 98.1

Exit mobile version