Site icon ETHIO12.COM

የትግራይ መሪ ጌታቸው አረዳ ከአዲስ አበባ መልስ ሃያ ሰባት ካቢኔ ሰየሙ፤ ጀነራሎቹ ምክትል ሆነዋል

ገና ከመነሻው ተቃውሞ ያጣደፋቸው የቀጦርነቱ ወቅት የትህነግ አፈ ቀላጤ አቶ ጌታቸው ረዳ ሃያ ሰባት አባላት ያሉትን ካቤኔ ሾመው በይፋ የስልጣን ርክክብ አድርገዋል። በአዲሱ የክልሉ አመራር ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደና ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ በምክትል ፕሬዝዳንት ተደራቢ ስልጣን ቁልፍ ቦታዎችን ይዘዋል።

ከተቋቋመ ሁለት ሳምንት ያስቆጠረው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባላቱን በይፋ ያስተዋወቀው ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 27፤ 2015 በመቐለ ከተማ ባካሄደው ስነስርዓት ነው። በዚህ ስነ ስርዓት ላይ የክልሉን መንግስት ሲመራ የነበረው የቀድሞ ካቢኔ፤ የአስፈጻሚነት ስልጣኑን በጊዜያዊ አስተዳደሩ ለተቋቋመው አዲሱ ካቢኔ ማስረከቡን የትግራይ ቲቪ አመልክቷል።

አዲሱ ካቢኔ ስብጥር 51 በመቶ ከህወሓት ሲሆን ተቃዋሚው ባይቶና ፓርቲ ሁለት ቢሮዎችን በኃላፊነት የመምራት ዕድል አግኝቷል። ከትግራይ ኃይሎች በካቢኔው ውስጥ የኃላፊነት ቦታ ያገኙት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ብርጋዴር ጄነራል ተኽላይ አሸብር፣ ሌተናን ጄነራል ፍሰሃ ኪዳኑ እና ሜጀር ጄነራል ዘውዱ ኪሮስ እንደሆኑ የሹመት ዝርዝሩን ያሰራጩ ሚዲያዎች መረጃ ያመለክታል። ምሁራንም እንደተካተቱበት ተመልክቷል።

በዚህ መሰረት

አቶ ጌታቸው ከአዲስ አበባ ቆይታቸው በሁዋላ የአስተዳደር አካላቱን መሰየማቸው በጉዳዩ ላይ ከፌደራል መንግስት ጋር መክረው ይሁንታ እንዳገኙ አመልካች እንደሆነ አብሮ ተሰምቷል። በትግራይ የአቶ ጌታቸውን ሹመት በመደገፍና በመቃወም እስከውጭ አገር ያለው ደጋፊ ዘንድ መከፋፈል አለ። መከፋለፈሉ ቢኖርም መንግስት ቀደም ሲል አፈ ቀላጤ እያሉ ሲያበሻቅጡት ለነበረው አቶ ጌታቸው ድጋፍ ስለሚያደርግ የሚፈጠር ነገር እንደማይኖር ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ እየገለጹ ነው።

Exit mobile version