የትግራይ መሪ ጌታቸው አረዳ ከአዲስ አበባ መልስ ሃያ ሰባት ካቢኔ ሰየሙ፤ ጀነራሎቹ ምክትል ሆነዋል

ገና ከመነሻው ተቃውሞ ያጣደፋቸው የቀጦርነቱ ወቅት የትህነግ አፈ ቀላጤ አቶ ጌታቸው ረዳ ሃያ ሰባት አባላት ያሉትን ካቤኔ ሾመው በይፋ የስልጣን ርክክብ አድርገዋል። በአዲሱ የክልሉ አመራር ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደና ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ በምክትል ፕሬዝዳንት ተደራቢ ስልጣን ቁልፍ ቦታዎችን ይዘዋል።

ከተቋቋመ ሁለት ሳምንት ያስቆጠረው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባላቱን በይፋ ያስተዋወቀው ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 27፤ 2015 በመቐለ ከተማ ባካሄደው ስነስርዓት ነው። በዚህ ስነ ስርዓት ላይ የክልሉን መንግስት ሲመራ የነበረው የቀድሞ ካቢኔ፤ የአስፈጻሚነት ስልጣኑን በጊዜያዊ አስተዳደሩ ለተቋቋመው አዲሱ ካቢኔ ማስረከቡን የትግራይ ቲቪ አመልክቷል።

አዲሱ ካቢኔ ስብጥር 51 በመቶ ከህወሓት ሲሆን ተቃዋሚው ባይቶና ፓርቲ ሁለት ቢሮዎችን በኃላፊነት የመምራት ዕድል አግኝቷል። ከትግራይ ኃይሎች በካቢኔው ውስጥ የኃላፊነት ቦታ ያገኙት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ ብርጋዴር ጄነራል ተኽላይ አሸብር፣ ሌተናን ጄነራል ፍሰሃ ኪዳኑ እና ሜጀር ጄነራል ዘውዱ ኪሮስ እንደሆኑ የሹመት ዝርዝሩን ያሰራጩ ሚዲያዎች መረጃ ያመለክታል። ምሁራንም እንደተካተቱበት ተመልክቷል።

በዚህ መሰረት

 • ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ – ምክትል ፕሬዝዳንት እና የሰላምና ጸጥታ ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
 • ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ – በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታዜይሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
 • አቶ በየነ ምክሩ – የኢኮኖሚ ልማት ሽግግር ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
 • ዶ/ር ሓጎስ ጎደፋይ – የእቅድ፣ ገቢና የሀብት አስተዳደር ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
 • ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሂወት – የማህበራዊ ልማት ሽግግር ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
 • ወ/ሮ ያለም ጸጋይ – የመሰረት ልማት ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
 • ብ/ ጄነራል ተኽላይ አሸብር – የመልሶ ግንባታና ማቋቋም ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
 • ዶ/ር አልጋነሽ ተሰማ – የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ስልጠና ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
 • አቶ አማኑኤል አሰፋ – ቺፍ ካቢኔ ሴክሬተሪያት
 • ዶ/ር እያሱ አብርሃ – የእርሻ ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ
 • ዶ/ር ገብረህይወት ዓገባ – የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ
 • አቶ ሞገስ ገብረእግዚአብሄር – የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ
 • አቶ ታደለ መንግስቱ – የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ
 • ወ/ሮ ምሕረት በየነ – የፋይናንስና ሀብት ማስተባበር ቢሮ ኃላፊ
 • ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ – የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
 • ዶ/ር አማኑኤል ሃይለ – የጤና ቢሮ ኃላፊ
 • አቶ ሓድሽ ተስፋ – የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ
 • ሌ/ጄነራል ፍስሃ ኪዳኑ ፋንታ – የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ
 • ዶ/ር ከላሊ አድሃና – የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ
 • አቶ ሓይሽ ሱባጋዳስ – የወጣቶች ቢሮ ኃላፊ
 • ወ/ሮ ገነት አረፈ – የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ
 • ሜ/ጄነራል ዘውዱ ኪሮስ – የማህበራዊ ጉዳይ እና መልሶ ማቋቋም ቢሮ ኃላፊ
 • ወ/ሮ አልማዝ ገብረጻድቅ – የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ
 • ወ/ሮ ፈለጉሽ አሳምነው – የመሬት እና ማዕድን ቢሮ ኃላፊ
 • ወ/ሮ ፍረወይኒ ገብረእግዚአብሄር – የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
 • ዶ/ር አጽብሃ ገብረእግዚአብሄር – የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
See also  "በህወሓት ልክ መኖርና በህወሓት ስምሪት መነሁለል ለዚህ ትውልድ ስድብ ነው" ዶክተር አብርሃም

አቶ ጌታቸው ከአዲስ አበባ ቆይታቸው በሁዋላ የአስተዳደር አካላቱን መሰየማቸው በጉዳዩ ላይ ከፌደራል መንግስት ጋር መክረው ይሁንታ እንዳገኙ አመልካች እንደሆነ አብሮ ተሰምቷል። በትግራይ የአቶ ጌታቸውን ሹመት በመደገፍና በመቃወም እስከውጭ አገር ያለው ደጋፊ ዘንድ መከፋፈል አለ። መከፋለፈሉ ቢኖርም መንግስት ቀደም ሲል አፈ ቀላጤ እያሉ ሲያበሻቅጡት ለነበረው አቶ ጌታቸው ድጋፍ ስለሚያደርግ የሚፈጠር ነገር እንደማይኖር ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ እየገለጹ ነው።

Leave a Reply