Site icon ETHIO12.COM

በኦሮሚያ 100 ሺህ ዘመናዊ የአርሶና አርብቶ አደሮች መኖሪያ ቤቶች ሊገነቡ ነው

የአርሶ እና አርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል በዚህ ዓመት ፅዱ ኦሮሚያ በተሰኘው ፕሮግራም 100 ሺህ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን እደሚገነቡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አወሎ አብዲ ተናግረዋል፡፡

የኦሮሚያ ስራ ዕድል ፈጠራ እና ክህሎት ቢሮ ፅዱ ኦሮሚያ በተሰኘው ፕሮግራም የሚገነቡ ቤቶችን ስራን ስኬታማ ማድረግ በሚቻልበት ሒደት ዙሪያ ከባለድርሻ አከላት ጋር በአዳማ እየመከረ ይገኛል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አወሉ አብዲ በሀገሪቱ ሁሉን አቀፍ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የገጠሩን ማህበረሰብ መኖሪያ ቤት ማዘመን ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በዚህ አመት በተመረጡ ቦታዎች 100 ሺህ ቤቶችን ለመስራት በተያዘው እቅድ መሰረት የኦሮሚያ ስራ እድል ፈጠራ እና ክህሎት ቢሮ: ቴክኒክ ና ሙያ ማሰልጠኛ ብሎም ዩኒቨርስቲዎች በቴክኖሎጂ ብልፀጋ: ብዜት ና በስራ እድል ፈጠራ ሊሰሩ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

የገጠሪቱን ማህብረተሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመረው ፅዱ ኦሮሚያ የተሰኘው ፕሮግራም በሰሜን ሸዋ ዞን ዋጫሌ ወረዳ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ይፋ መደረጉ ይታወሳል፡፡

ፅጌ ደረሰ OBN

Exit mobile version