Site icon ETHIO12.COM

መከላከያ በጃዊ የጥፋት ሃይሎች ሴራ አከሸፈ፤ ታጣቂዎቹ ትጥቅ ለመፍታት ተስማሙ

በጃዊ ወረዳ በፈንደቃ ከተማ የተቀነባበረ የጥፋት ሃይሎች ሴራ በመከላከያ ሠራዊቱ መክሸፉን ኮሎኔል መልካሙ በየነ ገለፁ።

ኮሎኔል መልካሙ በየነ እንዳሉት በከተማው የታጠቁ ሃይሎች በመግስት እና በሕዝብ ተቋማት ላይ ውድመት እና ዘረፋ ለማድረስ ቢንቀሳቀሱም በአካባቢው የሚገኝ የሜካናይዝድ ክፍለጦር በፍጥነት ወደ አካባቢው በመገስገስ የተቀነባበረውን የጥፋት ሴራ መቆጣጠር ተችሏል።

የጥፋት ሃይሎች በተቀናጀ መልኩ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን በሕገ ወጥ በመታጠቅ በመንግስት እና በህዝብ ተቋማት ላይ ጥቃት ማድረስ ብሎም በስኳር ፋብሪካው የሚገኙ የውጭ ዜጎች ተረጋግተው ስራቸውን እንዳይሰሩ ማድረግ የጥፋት ሃይሉ እቅድ እንደነበር ኮሎኔል መልካሙ በየነ ገልፀዋል፡፡

በአካባቢው በአሁኑ ሥዕት የሜካናይዝድ እና እግረኛ ክፍለጦሮች ግዳጃቸው በአግባቡ እየፈፀሙ ሲሆን በወረዳው በተለያዩ ጊዜ የሚከሰቱ የጥፋት ሴራዊችን በዘላቂነት ለማስወገድ ያፈነገጡ የጥፋት ሃይሎች በሰማዊ መንገድ ትጥቅ እንዲፈቱ በአገር ሽማግሌዎች እና በሃይማኖት አባቶች እንዲሁም ከተለያዩ አካላት ጋር መግባባት ተደርሷል፡፡

በሌላ ዜና በጃዊ ወረዳ ለሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለበአል መዋያ የሚሆን 06 የእርድ ሰንጋ በስጦታ መልክ ከፈንደቃ ከተማ ነዋሪዎች ተበርክቶላቸዋል፡፡

ለሰራዊቱ የተደርገውን ድጋፍ በመረከብ ምስጋና ያቀረቡት ሻምበል ባምላኩ ጨመረ የተደረገው ድጋፍ ህዝቡ ለሠራዊቱ ያለውን መልካም ነገር የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

የአካባቢው ማሕበረሰብ በግዳጅ ቀጠና ከሚያደርግልን ድጋፍ በተጨማሪ ሰራዊቱ በበአል ወቅት በቤተሰብ ናፍቆት ሳይጎዳ በግዳጅ ቀጠናው ደስተኛ ሆኖ በአልን እንዲያሳልፍ ታሳቢ የተደረገ ነው ሲሉ ሻምበል ባምላኩ ተናግረዋል።

የፈንደቃ ከተማ ምክትል አስተዳዳሪ በበኩላቸው ለጀግናው ሰራዊታችን የተደረገው የሠንጋ ድጋፍ ሕዝባዊ ወገንተኝነታችንን እና ከስራዊታችን ጎን መሆናችንን የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ኩራባቸው ግርማ

Exit mobile version