ETHIO12.COM

የተረጋጋች ኢትዮጵያ የኢሳያስ ስጋት!! የጃንጃዊድ ሚሊሻ መሪ ሄምቲን እስከመደገፍ

“ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ኢትዮጵያ ላይ የማይረሳ ወንጀል ሰርተዋል፤ አሁንም አላቆሙም፤ የኤርትራ ህዝብ ሊያስተውልና ከቀድሞ ችግሩ ሊማር ይገባል”

ኤርትራን ከ1983 ዓም ጀምሮ እየመሩ ያሉት ፐሬዚዳንት ኢሳያስ የተረጋጋች ኢትዮጵያን ማየት አይፈልጉም። ይህ ሳይታበል የተፈታ እውነት ጊዜና ሁኔታዎችን በመቀያየር ከሚገለጽበት አግባብ በቀር ኢትዮጵያን እረፍት አልባ ማድረግ የሚለው አጀንዳቸው የጸና ነው። ምክንያቱም ኢትዮጵያ ካረፈች የእሳቸው ህልውና አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ስለሚያሰሉ፣ ካላቸው በቀጠናው ታላቅ መሪ የመሆን የማይጨበጥ ህልማቸው ከሚቀዳ ሊሆን የማይችል ዕብለት እንደሆነ በርካቶች ይናገራሉ።

ኢሳያስ ትህነግ መከላከያ ሰራዊት ላይ ክህደት ሲፈጽም በቀጥታ ድጋፍ ማድረጋቸው በኢትዮጵያ ለውጡን ተከትሎ ከተፈጠረውና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ካሸለመው የሰላም ስምምነት መነሻነት ብቻ ሳይሆን ትህነግ የገነባው ሃይል ስጋት በመሆኑ እሱን ከማድቀቅ አንጻርም ነው።

ትህነግ የኢጋድ አገራትን አስተባብሮ ኤርትራ በማዕቀብና በመገለለ ጨለማ እንዲውጣት ያደረግ ድርጅትና መንግስት ስለነበር ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ሊያጠፉት ወይም በሚችሉት ደረጃ ሊበቀሉት ዘወትር ዝግጅት ነበራቸው። እናም ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው ትህነግን ተበቅለውታል። የቻሉትን መሳሪያ ወስደዋል። ስጋት መሆን በማይችልበት ደረጃ ቢያደርሱትም የፕሪቶሪያው ስምምነት መደረጉ ግን አልተዋጠላቸውም። ለዚህም ይመስላል ባለተለመደ ሁኔታ በተደጋጋሚ ሚዲያ ላይ በመውጣት ስምምነቱን በይፋ የተቃወሙት። ይህንኑ ቃለ ምልልሳቸውን ወደ አማርኛ በመመለስ በየገጻቸው ያቀረቡት እንዳስተጋቡት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከትህነግ ጋር የተደረገው ስምምነት ላይ ተቃውሞ ብቻ ሳይሆን አዛኝ መስለው ህዝብ ስምምነቱን እንዲቃወም በሚጋብዝ መልኩ ነው።

መንግስት ይፋ እንዳደረገው ጦርነቱ በሰላም ሲቋጭ የትግራይ ህዝብ እንደ ህዝብ መወሰን ባለበት ጉዳይ ውስጥ የመግባት ዕቅድም ፍላጎትም የለውም። ትህነግን ማፍረስም ሆነ ማስቀጠል የትግራይ ህዝብ ውሳኔ እንጂ የማንም ውሳኔ እንዳልሆነ ያስታወቀው መንግስት፣ በተመሳሳይ ትህነግ ስጋት የመሆንደረጃው በየትኛውም ደረጃ ከዜሮ በታች እንደሆነ ድንበር አካባቢዎችን በሙሉ የአገር መከላከያ በመረከቡ ከጎረቤት አገራት ጋር የሚፈጠር አንዳችም ስጋት እንደሌለም አመልክቷል። እንግዲህ መንግት ይህን ዋስትና ከሰጠ ኢሳያስን ምን አሰጋቸው? የሚለው ጉዳይ ገኖ ይወጣል።


ብሊንከን “በግጭቱ የተሳተፈ” ያሉት የኤርትራ ጦር መውጣቱን አረጋገጡ፤ ሁሉ አቀፍ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ተፈቀደ

መንግስት እያዘጋጀና እያሰራበት ላለው የሽግግር ፍትህና አገራዊ ምክክሩ አሜሪካ አስፈላጊውን ድጋፍና እርዳታ እንደምታደርግ በይፋ አስታውቀዋል። በግጭቱ የተሳተፈው የኤርትራ ጦር ለቆ መውጣቱን አመልክተዋሎኦ


ትህነግን ወልደው፣ አሳድገውና አስታጥቀው ለስልጣን ያበቁት ኢሳያስ፣ አገራቸው ኤርትራ በወቅቱ አንድ እግር የቡና ዛፍ ሳይኖራት ከአፍሪካ ግንባር ቀደም ቡና ላኪ ሆና የመመዘግቧ ዜና፣ በከፍተኛ ደረጃ ለአንድ ጎረቤት አገር በማይፈቀድ ደረጃ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ሰርገው የመግባታቸው ጉዳይ “በቃ” ሲባል ጦነት መቀስቀሱን የሚያስታውሱ፣ አሁን ከሰላም ስምምነቱ በሁዋላ መንግስት ፊቱን በህገወጥ ንግድ ላይ እንዲያተኩር ማድረጉ እንዳላስደሰታቸው መረጃዎች እየወጡ ነው።

ከአሜሪካ እስከ አዲስ አበባ በተዘረጋ መረብ የሚካሄደው አይን ያወጣ የዶላር አጠባ፣ ኮንትሮባንድና የቅባት ዕህል ዝውውር ላይ ያለውን አካሄድ ለማምከን መከላከያ ስምሪት መውሰዱ፣ ከዚህም ጋር ተያይዞ ኤርትራ ውስጥ የሚሰለጥኑ ታጣቂዎች ጉዳይ መልክ እንዲይዝ ኢትዮጵያ መጠየቋ፣ በአማራ ክልል ከኤርትራ ጋር የሚያገናኘውን ድንበር መከላከያ ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠረው የማድረግ ስራ መጀመሩ በኤርትራ በኩል ቅሬታ ማስነሳቱን ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ እየገለጹ ነው።

አንዳንድ “ጽንፈኛ” ከሚባለው የአማራ ሃይል ጋር ግንኙነት መፍጠራቸውን፣ እነማን ይህን ግንኙነት እንደሚመሩት ስም ጠቅሰው የሚናገሩ እንደሚሉት፣ መንግስት ከትህነግ ጋር ያደረገው የሰላም ስምምነት በአገሪቱ በውል የሚታይ ሰላም እያጎናጸፈ ከመሆኑ ጋር ተዳምሮ የተጀመሩት አሰራርን የማጥበቅ፣ ግንኙነትን ህግ በሚፈቅደው የማድረግ፣ ትግራይን እንደ አገር የኢትዮጵያ አካል አድርጎ የመንቀሳቀስ አካሄድ መጀመሩ ወዘተ በዚህ አግባብ ከቀጠለና የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ መኖሪያቸው ከተመለሱ አገሪቱ አስተማማኝ ሰላም ስለምትዘረጋ ቀጣዩ ጉዳይ ኢሳያስን ሰላም እንደነሳቸው ምልክቶች አሉ።

አክቲቪስት መስለው የኤርትራን መንግስት አቋም በኢትዮጵያዊያኖች ሚዲያ በተደጋጋሚ የሚያሰራጩ እንደሚያስታውቁት፣ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር የጀመረችው ወይም ያደሰችው ግንኙነት ስህተት ነው። ትክክልም አይደለም። አምስት ሚሊዮን የማይሞላ ህዝብ እንዳላት ኤርትራ 120 ሚሊዮን የተሸከመች አገር በሯን ጠርቅማ እንድትኖርም እየመከሩ ነው። ከትህነግ ጋር ዳግም የተጀመረው ወዳጅነት ለኤርትራ ስጋት እንደሆነም እየገለጹ ነው። ጉዳዩ ከዩቲዩብ ወሬ ባያልፍም በተደጋጋሚ በኢትዮጵያዊያን መነገሩ ግን ትርጉሙን ያጎላዋል። “ኢትዮጵያዊያኑ” ጉዳዩን ከኤርትራ ህዝብና ከኢትዮጵያ ክዝብ ጥቅምና ጉዳት አንጻር ዘርዝረው አለማስረዳታቸው ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ጦር ጠብ መንጃ ካወረደ በሁዋላ በጅምላ በረሃ ላይ የጨፈቸፉና ያስጨፈቸፉትን ኢሳያስ አፉወርቂን የኢትዮጵዮጵያ መጻኢ ዕድል ተንባይ፣ ወሳኝና፣ አመላካች አድርገው ማቅረባቸው ብዙዎችን አስገርሟል። ከሁሉም በላይ ምድር ላይ ባሉ መለኪያዎች ሁሉ ከኢትዮጵያ መንግስት የሚሻል ስብዕናም ሆነ መልካም ተሞክሮ የሌላቸውን፣ ያለ ህገመንግስትና ህግ አገር የሚመሩና የአገሪቱን አምራች ሃይል እንዲሰደደ ያደረጉን መሪ የኢትዮጵያ ጉዳይ ባለቤት ለማድረግ የሚኬድበት አግባብ ምክንያቱም በወጉ ሊጠና እንደሚገባ የሚጠቁሙ ጥቂት አይደሉም።

President Isaias Afwreki in the morning hours of today, 13 March, received and held talks at the State House with Gen. Mohamed Hamdan Dagalo, Vice Chairman of the Sudan’s Sovereign Council.

እንግዲህ ነገሮች በዚህ መልክ እየሄዱ ሳለና መንግስት ልዩ ሃይል የሚባለውን ህግ የማይደግፈው አደረጃጀት ወደ ህጋዊ ማዕቀፍ ለማስገባት እንቅስቃሴ ሲጀመር ከሱዳን አዲስ ዜና የተሰማው። የጃንጃዊድ ሚሊሻ ወይም  ራሱን አዘምኖ የፈጥኖ ደራሽ የሚለው ልዩ ኃይል አዛዥ ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎና የሱዳን መንግስትን የሚመሩት ብጀነራል አል-ቡርሃን መካከል በገሃድ ጦርነት የተጀመረው። ከዜናው ጎን ለጎን ደግሞ የሐምዳን ዳጋሎ (ሔምቲ) ከወር በፊት ኤርትራ ለጉብኝት ከተመው መቆየታቸው ከኢትዮጵያ አንጻር ታላቅ ፖለቲካዊ ፋይዳ ያለው ጉዳይ እንደሆነ አስተያየት እየተሰጠ ነው። ኤርትራ ፕሬስ ከሱዳን ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ወዳጅነት ለማጠናከር በሚል ግንኙነቱን በወቅቱ ግልጾታል። ይህ ግብኝት የተደረገው የአገሪቱ ጦር አዛዥ ጀነራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃን የሉዓላዊ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት እና የአገሪቱ መከላከያ ኃይል አዛዥ ከኢትዮጵያ ጋር በሁሉም አግባብ ተስምምተው ለመስራት፣ የድንበር ውዝግቡንም በህግ አግባብ ለመጨረስና በህዳሴ ግድብ ላይ ኢትዮጵያን በይፋ እንደሚደግፉ፣ በተለይም የአረብ ሊግ የያዘውን አቋም በግሃድ እንደሚቃወሙ ባስታውቁ ማግስት ነው።

ኤርትራ በርካታ ሚሊሻ አስለጥና እንዳስታተቀች የሚነገርለት ሐምዳን ዳጋሎ (ሔምቲ) በይፋ ይህን ድጋፍ ማግኘቱ ብቻ ሳይሆን፣ በአማራ ስም የሚነቀሳቀሱና አማራ የራሱ መከላከያ እንዲገነባ የሚሰብኩና ተከታዮቻቸውም ልክ እንደ ኢሳያስ ለሐምዳን ዳጋሎ (ሔምቲ) ድጋፍ መስጠታቸው ነገሩን “እንዴት እንዴት..” የሚል ቅኝት አስቀኝቶታል። አካሄዱስ ለየትኛው ህዝብ ይተቅማል የሚል የብልህ ጥያቄም እያስነሳ ነው።

ሐምዳን ዳጋሎ (ሔምቲ) የሚመሩት አርኤስኤፍ የሚባለው ኃይል የተመሰረተው እአአ 2013 እንደሆነ ቢነገርም፣ አማጺያንን በዳርፉር ሲዋጋ የነበረው ጃንጃዊድ ሚሊሻ ነው። ሄምቲ ከሱዳን ተሻጋሮ በሊቢያና በየመን ጦርነት የተሳተፈ ጠንካራ ኃይል ገንብተዋል። ቡድኑ በሱዳን የሚገኙ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ስፍራዎችን ይቆጣጠራል። ይህ ቡድን በተሳተፈባቸው ውጊያዎች በከፍተኛ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ይከሰሳል። እአአ 2019 ላይ 120 ተቃዋሚዎችን በመግደልም የሄምቲ ኃይል ተጠያቂ ይደረጋል። ከአገሪቱ ጦር ቁጥጥር ውጭ ያለው ይህ ኃይል አገሪቱ እንዳትረጋጋ ምክንያት ነው ሲባል እንደቆየ ቢቢሲ ዋቤ ጠቅሶ ዘግቧል። እንግዲህ ሽፍታን መደገፍና መንግስት እንዲሆን ማገዝ ያስፈለገው ለምንድን ነው? ይህ እንደ አገርም፣ እንደ ጠያቂ ዜጋ በጥልቀት የሚታይ ጉዳይ ነው።

በግመል ንግድ ቱጃር ለመሆን ትምህርታቸውን ከአንደኛ ደረጃ ማቋረጣቸው ከግል ማህደራቸው የሚነበብላቸው የሽፍቶች መሪ ጃንጃዊድ የተሰኘውን ጨፍጫፊ ቡድን ከአጎቱ ጋር በመሆን የመሰረተ ሲመሰርት ዛሬ ላይ 100 ሺህ የሚደርስ እስከ አፍንጫው የታጠቀ ሃይል እንዳለው ይነገራል። እኚህ ፊደል ጦሩ ጀነራል ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር በነበራቸው የመጨረሻ ግንኙነት ምን እንደመከሩ መረጃዎች ባይወጡም ዓላማቸው “ጀነራል አል-ቡርሃን የሄምቲ ጦር ስልጣን ለመያዝ እየጣረ ነው ሲሉ ሄምቲ ደግሞ ‘ወንጀለኛ’ የሆኑት አል-በሩሃን ‘ይገደላሉ’ አልያም ‘ሕግ ፊት ይቀርባሉ’ ሲሉ ለአል ጀዚራ እንዳስታወቁት መንግስት መቀየር ነው።

አሁን በርካቶችን እያነጋገር ያለው ጉዳይ በሱዳን አሁን ያለው መንግስት ወድቆ  ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ የሚመሩት መንግስት ወደ ስልጣን ቢመጣ “ኢትዮጵያና ሱዳን የሚዋሰኑበት 1600 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ድንበር ዙሪያ ምን ለማድረግ ታስቧል?” የሚለው ነው። መንግስትም ሆነ የአገር መከላከያ አዛዦች በተደጋጋሚ እንደሚሉት ኢትዮጵያ አሁን ላይ የገነባቸው ሰራዊት ማናቸውንም ስጋቶች እንደ አመጣታቸው ማስተናገድ የሚችል መሆኑ፣ ከጎረቤትም ሆነ ከውስጥ ጭነቀት የሚፈጥር ሃይል አለመኖሩ ቢገልጽም ኤርትራ ውስጥ የሚሰለጥኑ ሃይላት መኖራቸው ምን አልባትም ኤርትራና ኤትዮጵያን እንዳያጋጭ ስጋት የገባቸው በርካታ ናቸው።

የትግራይ ሃይሎች ያዘጋጁት ሃይል ጨምሮ ከክልል የልዩ ሃይላትን ወደ መከላከያ በማስገባት ክንዱን እያፈረጠመ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በአይር ቅጭትና በምድር ሃይል በጥብቅ ክትትል እያደረግ መሆኑንን ደጋግሞ አስታውቋል። ኢትዮጵያ በሱዳን ጦርነት እጇ እንዳለባት የሚሰራጩ ዜናዎችን አክርሮ በመቃወም የሚሆነውን እየተከታተለ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ምንም ሆነ ምን የገነባው ሃይል ያሳሰባቸው ፕሬዚዳንት ኢሳያስን የተረጋጋች ኢትዮጵያን መኖር የለባትም ከሚለው የቆየ ዕምነታቸው ጋር በተያያዘ በዚህ ጦርነት ውስጥ እጅቻቸውን ማስገባታቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በህዝብ ደረጃ የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝብ በዘር ፖለቲካ አቀንቃኞች አማካይነት ለመከራና ለስደት መዳረጋቸውን ያስታወቁ ወገኖች ” ያለፈውን ባለመርሳት ህግን አክብሮ መኖር፣ ህግን ጠብቆ መጎራበት፣ ህግን ተገን ያደረግ ግልጽ ወዳጅነት እንዲደረግ ከሁሉም ወገን ግፊት ያስፈልጋል” ባይ ናቸው።

መንግስት በግልጽ በየትኛውም አገርም ሆነ መሪ ላይ አስተያየት ባይሰጥም፣ አሁን ላይ ያለው የመከላከያ አቅም በአጭር ውጊያ፣ በአነስተኛ መስዋዕት፣ ማናቸውንም ኦፕሬሽኖች ማከናወን የሚችል መሆኑንን በቅርቡ ግጭቱን ተከትሎ መገምገሙ ተሰምቷል። በየትኛውም ደረጃ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ምልክት ከታየ የሚፈለገውን ምላሽ ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁም ታውቋል።

በኢትዮጵያ ልዩ ሃይል የሚባለውን አደረጃጀት ወደ መስመር ባማስገባት የብሄር ታርጋ ያላቸውን ተቋማት ወደ ኢትዮጵያዊ ቀለም የመቀየሩ ስራ መጠናቀቁን ተከትሎ እንደሚሰማው ከሆነ በርካታ የኮንትሮባንድ መስመሮች እየተዘጉ ነው። በዶላር አተባ ላይ ስምሪት ወስደው የሚነቀሳቀሱ ተይዘዋል። እግራቸውን በመንግስት ባንኮች ውስጥ ከተው ከገደብ በላይ ብር በማዛወር ዶላር ሲያከማቹና በፍራንኮ ቫሎታ ፈቃድ በርካሽ ነግደው በጥቁር ገበያ ዶላር በመሰብሰብ በዲፕሎማት ቦርሳ ሲያግዙ የነበሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ያስነሳው ቅሬታ እንደምታው ቀላል ባለመሆኑ መንግስት ከወትሮው በላይ ኮስተር ሊል እንደሚገባው በርካቶች እየጠቆሙ ነው።

Exit mobile version