Site icon ETHIO12.COM

ያልተገረዛችሁ ተገረዙ!! አሉ ጌታቸው ረዳ

መገረዝ የዘመኑ፣ የዛሬ፣ እንደውም የአሁን አንገብጋቢ ጥሪ ነው። “ተገረዙ” ያሉት በስድብና በነውጥ አስተባብሪነታቸው ወደር የማይገኝላቸው የዛሬው ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸ ረዳ ናቸው። ጌታቸው ረዳ “ተገረዙ” ያሉት ያን ነገር አይደለም። ምላስን ነው። እንግዲህ ዛሬ “ነበር” ስለሆነ ጨዋታው በዛው ሂሳብ ነው።

ጠቅላዩን የስድብ ናዳ ሲያወርዱባቸው ከነበሩ በርካቶች ፊት የሚሰለፉት አቶ ጌታቸው ነበሩ። አቶ ጊታቸው አንድበታቸው ክፉ፣ ትርክታቸው መርዛማ፣ አቀራረባቸው በክፋት የተጎነጎነ፣ ከአገር ውስጥ “ፍልፍል” ሚዲያዎች ጀምሮ የዓለም ሚዲያዎች የተነፈሱትን ሁሉ የሚቀባበሉላቸው ስለነበር ናኝተው ነበር። በዚህ ምላሳቸው የተሳlaቸው ብልጽግና በመርዳሳ በኩል ተደጋጋሚ የድሮን ስጦታ ልኮላቸው እንደ ጦስ ዶሮ ተርፈዋል። ትርፍ ህይወት እንዳሉት እሳቸው!!

ያበደው ጥያቄ አለው። ስሜነህ ባይፈርስ የአቶ ጌታቸው አፈ ቀላጤ ሆኖ ለመታየት ያሸረገደበት የቪዲዮ ቅንብር ትግራይ አማካሪ ሆኖ የተሾመ እንጂ በሙያው ሊሰራ የሄደ አይመስልም። ወርቁ አይተነውን ስለ ናሳና የአሜሪካን የውጭ ፖሊስ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሲጋብዝ ቦሰና እንደፈረንጆቹ ” ስሜነህ ዛሬ ምን አጭሶ ነው” ብላ ነበር ። ያብደው ደግሞ “ስሜንህ ምንም ይሁን ምን ወርቁ አይተነውስ አያፍርም፟ እንዴት ሰው የማያውቀውን ይዘለብዳል …” ብሎ ነበር። በነገራችን ላይ ምርት እንዳይጀምር ወይም እንዳያመረትታስቦ የተገነባውን በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃል የተሰየም ፋብሪካ መጥራት አቅቶት ” የብቸናዋ ..” ብሎ ሲማጸን … አይ ጊዜ ….

ለማንኛውም አቶ ጌታቸው የአፍ ፣ የምላስ፣ የአንድበትና የአስተሳሰብ ግርዛት እንደሚያሻ ዛሬ አይተው በማያውቁት መድረክ ላይ ተሰቅለው ተማጽነዋል። የትግራይን ህጻናት ስቃይና መከራ ማንን ተጠያቂ እንደሚያደርጉ ባይታወቅም ዘርዝረዋል። አሳባቸው የጦርነትን ክፋት ለማስረዳት ቢሆንም ” ማን ቀሰቀሶ፣ ማን አሳጨደ፣ ማን አስወቃ… ለሚለው ጥያቄ ግን መልስ የለም። መገረዙ ጥሩ ነው። ይህን ሁሉ ህዝብ አሳጭዶ መሸለም … ታደሰ ወረደም ተሸልመዋል። ጻድቃንም … የትግራይ ህዝብ ይቅር ካለ ደግ ነው … የሽግግር ፍትህ ለካ አለ!! ዕድሜ ይስጠን!! ቦሰና ሁሌም ” ትህነግ ግን ምን ፈልጎ ነው የተዋጋው” ትላለች!!

አንድ ጎልማሳ አፉን አረፋ እስኪደፍቀው ድረስ በጩኸት ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ላይ የስድብ ውግዘት ያወረዳል። ስድቡ የሚነዝር ነው። የቃላት ምርጫ፣ የሰሚ ምን ይላል አፍረት የለም። ብቻ ዶክተሩን ያወርድባቸዋል። “ምን ሆኖ ነው?” ሲባል የሚያውቁት ሁለት ዲግሪ እንደነበረውና ሁለቱም ዲግሪዎች በዘመኑ ቋንቋ “ከወፍጮ ቤት የተገዙ” የሚባሉት በመሆናቸው ናቸው።

ከሁለት ዲግሪ ባለቤትነት ባዶ መሆን፣ በቤቱ ግድግዳና በየማህበራዊ ሚዲያው የሰቀላቸው ምስሎች፣ ምስሎቹ ስር የተለቀለቁት ውዳሴዎች፣ በምሁራን ሰፈር ገብቶ የደርበው ሊቀ ሊቃውንትነት … ድምር “ሁሉም ዜሮ” የሆነበት ጎልማሳ አረፋ ያስደፈቀው ጉዳይ ይኸው ነበር። እዚህ ላይ እናቁመው። ስለም ይብዛላችሁ። ያበደው ነኝ ከዛ ሰፈር!! አንዷ የጀነራል ሚስት ከሲቪል ሰርቪስ ዲግሪ ይዛ አውሮፓ ስደት ገባች። ስሟን መሳፍ አትችልም። ያብደው ፈንዳ… እንደተበድለች ሆና ስደት ከመውጣቷ በፊት የአንድ ሚኒስትር አማካሪ ነበረች አሉ። እንግዲ “ነበር” ጨዋታው …

የዶክተር ዳኛቸው አሰፋ እህት ወይም የስጋ ክፋይ ወይዘሮ ገነት ዘውዴ በመለስ ዜናዊ መንበረ ሹመት በመመሪያ የተከሉት የትውልድ አቀንጭራ ፖሊሲ ሃያ ስምንት ዓመት ትውልድ ካነከተ በሁዋላ ለውጡን ተከትሎ የትምህርት ሚኒስትር የሆኑት ዶክተር ብርሃኑ ነጋ መነጋገሉት። ትውልዱን የበላውን መጋረጃ በረገዱት። ጠረኑ አገር ያወደውና ውድቀታችንን ያሳየን ድንቁርና የብሄራዊ ፈተና ውጤት ገሃድ አወጣው። ውጤቱ ከመቶ ተማሪ ሶስት ተማሪ የማይልፍበት ደረጃ ላይ እንደተሰቀልን መርዶ አረዳን። ለካ በየቢሮው ስሙን መጻፍ የማይችል ጎልዳፋ የዚህ አቀንጭራ ፖሊሲ ውጤት ነው በሚል መግባባትም ላይ ተደረሰ። ያብደው አሁን ደግሞ ቀዘዘ።

ዛሬ ኢትዮጵያ ላይ የሚሆነው ሁሉ ከላይ ባለው ማዕቀፍ ውስጥ የሚታይ ወይም ሊታይና ሊሰላ የሚገባው ነው። መቼም በኢትዮጵያዊያን ስነ ልቡና ውቅር ያደገ፣ጭንቅላት ያለው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሰው ገሎ፣ ሰቅሎ በድንጋይ እየወገረ ቪዲዮ አይቀርጽም። ተቀርጾም በማህበራዊ ገበያ ራሱን ለታሪክና ለአንድ ቀን ፍርድ አያስቀምጥም። ግን የሆነው በተቃራኒው ነው። ከምንም በላይ ግን የሚያስገርመው ይህን ዘግናኝ ጉዳይ “ሰበር” ብለው ብር የሚያጥቡበት ሚዲያ የሚባሉ መናጆዎች ናቸው። ከሚለቃቅሙት ገንዘብ በላይ አንዱን ተናዳጅ፣ ሌላውን አናዳጅ አድርገው በጅምላ ህዝብን ለማፋጀት የሚሄዱበት ርቀትና ፍጥነት ነው። ብርሃኑ ነጋ ገበናውን የገለጡት ትውልድ!!

“ምን አለሽ ተራና ምን አለ ዛሬ …” አለች ቦሰና ” ቢያዩዋቸው ቢያዩዋቸው ሁሉም አንድ ናቸው” ግጥም ስትሰጥ ነው። ያበደው ጭድ ተራ ገባ። ምን አለሽ ተራ የነተበ፣ የተነደለ፣ አካሉ የጎደለ እቃ ያለ አፍረት ይሸጣል። አንድ እግር ካልሲ፣ የተቀደደና ካካው ያልታጠበ ቡታንታ… ንፍጡ የደረቀ መሃረብ፣ እራፊ ነገር … የደረቀ አር ከሰል ሆኖ ለገበያ ይቀርባል። እራፊ ሸጦ ጉርሻ መግዛት ባህል ነው ኑሮ!!

ምን አለ ዛሬም ያው ምን አለሽ ተራ ነው። ቦሰና “ተገረዙ” አለቻቸው። ቦሰና “አይሰለቻቸውም” ትላለች። ሁሉ ልክ እንደምን አለሽ ገበያ የማያድግ እራፊና ብስባሽ የሚነግድ ተቋም!!

መርምሮ፣ አስቦ፣ አውርዶና አውጥቶ ማውገዝ፣ መተቸት፣ መቃወም ያለና የሚደገፍ ነው። የምን አለ ዛሬ አጠባ ግን … አጣቢዎቹ ሳይሆን የሚታጠቡት ያሳዝናሉ። ቦሰና አንዴ አሜሪካ ነበረች። አንድ ወዳጇ የስንብት ራት ጋብዟት አንድ ሬስቶራንት ተቀምጣ ሁለት እናቶች ጮሁ። “አፈር ብሉ፣ ህዝብ እያባላችሁ ክትፎ ትበላላቹ፣ የድሃ ልጅ እያስጨረሳችሁ እናንተ ትከታላችሁ። አፈር ብሉ። ደም ጠጡ … ወላዲት አምላክ …” እናቶቹ ተለምነው በገላጋይ ወጡ…

ጌታቸው ረዳ ክልላቸው ስፖንስር የሚያደርጋቸውን ሚዲያዎች መዝጋታቸውን በተዘዋዋሪ አውጀዋል። ተገረዙ ብለዋል። ቸዋታው የተለመደው የካድሬ ይሁንም ሌላ መገረዝ ግድ ነው። ቦሰና ግን እስከ ወዲያኛው አትገርዝም። ለምን የሚል ጥያቄ ላላችሁ ያበደው ጥሪ አይቀበልም። ቦሰና እንደተፈጠረች ናት። ትመቻለች። ማስቲካ!!ሰላም ሁኑ። ጊዜው የቦሰና ነው አሁን!! ከቦሰና ጋር ፑል!!


Exit mobile version