Site icon ETHIO12.COM

የአውሮፓ ህብረት ተደመረ “ኢትዮጵዮጵያ በአፍሪቃ ቀንድና በቀይ ባህር የአውሮፓ ቁልፍ ስትራቴጂክ አጋር ናት”

ኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላም ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ዛሬ ውሳኔ ማሳለፉን በይፋዊ ገጹ ባወጣው አቋሙ አስታውቋል።

ኢትዮጵዮጵያ በአፍሪቃ ቀንድና በቀይ ባህር ቀጠና የአውሮፓ ቁልፍ፣ ስትራቴጂክ አጋር መሆኗን አስረግጦ ያስታወቀው የህብረቱ መግለጫ በኢትዮጵያ መንግስትና አምጾ በነበረው ትህነግ መካከል ዘላቂ ሠላም ለማስፈን የተደረሰውን ሥምምነት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ ድግም ገልጿል።

ምክር ቤቱ የአውሮፓ ኅብረት ኤኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በቀይ ባሕር ቀጣና ለአውሮፓ ኅብረት ቁልፍ ስትራቴጂያዊ አጋር ናት” ማለቱ ኢትዮጵያስ ከገነባቸው የመከላከያ ሃይልና በተለይም ከባህር ሃይሏ ዳግም መደረጃት ጋር ተያይዞ ታላቅ ፖለቲካዊ አጀንዳ ያለው እንደሆነ ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ አስቀድመው የተናገሩት ማረጋገጫ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድም ቀደም ብለው ጠንካራ መከላከያ ሲገነባ ዛሬ ኢትዮጵያ ላይ የተነሱት በሙሉ ለምነው እንደሚመለሱ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

የአውሮፓ ኅብረት ኢትዮጵያ ዘላቂ ሠላም ለማረጋገጥ የምታደርጋቸውን ጥረቶች፣ የጥረቶቹን እድገትና የሰላም ማስፋፍቱን ሂደት አግንኗል። በተግባር ለታየው ለዚሁ ጥረት ቀደም ሲል በጭፍንንና በልዩ አጀንዳ ኢትዮጵያ ላይ በሩን ዘግቶና ድጎማ ነፍጎ የነበረው የአውሮፓ ህብረት በሚያስፈልገው ሁሉ ኢትዮጵያን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑንም ያስታወቀው “ሙሉ በሙሉ” በሚል ሃረግ ነው። የአውሮፓ ኅብረት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚፈልግ እና ግንኙነቱን ወደ ስትራቴጂያዊ አጋርነት ለማሳደግ እንደሚሠራም አስታውቋል።

በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተከሰቱ ያሉ ውጥረቶች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ጉዳይ በትኩረት እየተከታተለ መሆኑን በማንሳት፥ ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ ጥረት እንደሚያደርግም አመልክቷል።

መንግስት የቀደመውን የዲፕሎማሲ መንገድ በጣጥሶ አዲስ መንገድ በመከተል ሲወቀስበት የነበረውን ዲፕሎማሲ አጠንክሮ በመስራት የዓለም ታላላቅ አገራት ታላላቅና ቁልፍ መሪዎች አዲስ አበባ ሲመለላለሱ መሰንበታቸው ይታወሳል።

መንግስት ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ቀይ ባህር የነበራትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት ለማስቀጠል ግልጽና ጥርት ያለ አቋም በመያዝ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ያበላሹትን ለማቃናት ግልጽ አጀንዳ ይዞ እየሰራ እንደሆነ አመልክተን መዘገባችን ይታወሳል። ይህ የመንግስት አቋም የዛሬ የቀይ ባህር አለቆች ነን በሚሉ የሚወደድ ባይሆንም አሁን የተጀመረው ሁሉን አቀፍ ሰላም የማስፈን ስራ ሲጠናቀቅ የወደብ አጀንዳ ዋናው ጉዳይ እንደሚሆን ምልክቶች በሚታዩበት በአሁኑ ወቅት ይህ ጥሪና ሃላፊነት ለኢትዮጵያ መቅረቡ ጉዳዩ ሩዝቬልት “በፖለቲካ በድንገት የሚሆን ነገር የለም። ከሆነም እንዲሆን ተፈልጎ ነው” እንዳሉት ተመሳሳይ እንደምታ እንዳለው መግለጫውን ያዩ ፈጥነው አስተያየት ሰጥተውበታል።

Exit mobile version