ETHIO12.COM

“የሕገ ወጥ ቡድን አዝማቾቹና ዘማቾቹ በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ይገኛሉ”

ከጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ

የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የራሳቸውን አደረጃጀት ፈጥረው መንግሥትን በሕገ ወጥ መንገድ ለመተካት ያሰቡ አካላትን ተልዕኮ ለማክሸፍ የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ ቀጥሏል።

የሀገሪቱን ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት በኃይል ለማፍረስና እኩይ የፖለቲካ ፍላጎት ለማሳከት ከፍተኛ አመራሮችን በመግደል፣ በኅብረተሰቡ ወስጥ ሽብርና ፍርሃትን በመፍጠር እኩይ ፍላጎታቸውን ለማሳካት በሕገ ወጥ መንገድ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ጽንፈኛ የሽብር ቡድኖችን እንቅስቀሴና ድርጊት እያመከነ ነው።

በዚህም መሠረት ባለፈው ጊዜ ከወሰዳቸው ርምጃዎች በተጨማሪ በዛሬው ዕለት ጽንፈኛው ቡድን ሰሜን ወሎ ዞን ተኩለሽ ጫካ ቆፍሮ ያዘጋጀው ስቶር ውስጥ የቀበራቸውን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እና ተተኳሾችን መያዙን የጸጥታና የደኅንነት ገልጠዋል።

ይህ ሕገ ወጥ ኃይል ወደ ሰላም መንገድ እንዲመጣ የቀረበለትን አማራጭ በመርገጥ፣ በጥፋት ኃይልነት ለመቀጠል ያቀደው መንገድ በጸጥታና የደኅንነት አካላት እየከሸፈበት ይገኛል።

1 / 10

ከሀገር ውስጥና ከውጭ በገንዘብና በፕሮፓጋንዳ ተደራጅቶ፣ የሽብር ተግባር ለመፈጸም የተመሠረተው ይህ ሕገ ወጥ ቡድን፣ አዝማቾቹና ዘማቾቹ በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ይገኛሉ። ለዚህ የሽብር ተግባር ያከማቿቸው የጦር መሣሪያዎችም በጸጥታ አካላት እየተያዙ ናቸው።

በትናንትናው ዕለት ከተያዙት ሕገ ወጥ መሣሪያዎች በተጨማሪ በዛሬው ዕለት ከላይ የተገለጡት የተደበቁ መሣሪያዎች መገኘታቸው ተገልጧል።

የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ጽንፈኞችን ለሕግ ለማቅረብና የሽብር ተልዕኳቸውን ለማክሸፍ የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጧል።

ህብረተሰቡ እያሳየ ያለውን የፅንፈኛችን የጥፋት ሴራ የማከሸፍ እና ለፀጥታ አካለት የሚያደረገውን የመረጃ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል የጸጥታ ግብረሃይሉ ጥሪ አቅርቧል።

Exit mobile version