Site icon ETHIO12.COM

ቴክሳስ የገበያ ማዕከል አንድ ታጣቂ ዘጠኝ ሰዎችን በጥይት ገደለ፣ የቆሰሉም አሉ

“ለመግለጽ የሚከብድ ሃዘን” የተባለለት የቴክሳስ የጅምላ ጭፍጨፋ ማንንም አልመረጠም። ሕጻናት ሳይቀር በጥይት ተገድለዋል። ሙሉ በሙሉ ጥቁር በመልበስ ማንነቱን የሸፈነው ታጣቂ መሳሪያ እንደ አሻንጉሊት መሽመት ልቅ ስለሆነ ይመስላል ሁሉንም ዓይነት የውጊያ መጠቀሚያ ታጥቆ እንደነበር ተመልክቷል።

በተያዘው ዓመት በአሜሪካ በተቀነባበረ ሁኔታ የጅምላ ግድያ በሳምንት አንድ ጊዜ እንደሚፈጸም ኤፒ የአገሪቱን የመረጃ ቋት፣ አሜሪካ ዛሬና የሰሜን ምስራቅ ዩኒቨርስቲ በጥምረት ይፋ ያደረጉትን ሪፖርት ጠቅሶ ይፋ አድርጓል። ይህ መረጃ ይፋ የሆነው ፖሊስ በቴክሳስ ግዛት አለን ከተማ በገበያ አዳራሽ ውስጥ ፖሊስ እንዳረጋገጠው ዘጠኝ ንጽሁሃን መገደላቸውን ተከትሎ ነው። የጅምላ ግድያ ፈጻሚው ጥቃቱን ያደረሰው ብቻውን እንደሆነና ወዲያው እዛው መገደሉ ታውቋል።

በአሜሪካዋ የቴክሳስ ግዛት ውስጥ በምትገኘው አለን ከተማ አንድ ታጣቂ በገበያ አዳራሽ ውስጥ በፈጸመው ጥቃት በዚህ ጥቃት ሲገደሉ፣ በገበያ አዳራሹ ውስጥ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ድጋፍ ከገበያ ማዕከሉ እንዲወጡ መደረጉን በስፍራው የነበሩ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

ከቀናት በፊት ቴክሳስ ውስጥ አንድ ታዳጊ መገደሏ ይታወሳል። 105 ሺህ ህዝብ በሚኖርባትና ከዳላስ 32 ኪሎሜትር ርቃ በምትገኘው የአለን ከተማ የደረሰውን አስደንጋጭ የጅምላ ሽፍሸፋ አስመልክቶ የእሳት አደጋ መከላከያ ኃላፊ ጆናታን ቦይድ እንዳረጋገጡት ከሞቱት በተጨማሪ ሰባት ሰዎች ቆስለዋል። ሶስቱ ክፉኛ ተጎድተዋል። ሁሉም ህክምና ላይ ሲሆኑ አንዱ በህክምና ኡየተረዱ ሳለ ህይወቱ ማለፉ ታውቋል። ህጻናት ጭምር በተገደሉበት የዚህ ግድያ ፈጻሚ ግድያውን ባከናወነበት የገበያ ስፍራ ፖሊሶች በጥይት ተገድሏል።


Exit mobile version