Site icon ETHIO12.COM

በምዕራብ ጎጃም ለደስታ በተተኮሰ ጥይት ሙሽራው ከእነ አባቱ ህይወታቸው አለፈ

በምዕራብ ጎጃም አስተዳደር  ዞን በቋሪት ወረዳ ወይበኝ ቀበሌ ልዩ ቦታው በተለምዶ አነሳት እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ በባህሉ በወጉ መሰረት ልጃችንን ለልጃችሁ ተባብለው ሙሽሪትና ሙሽራው ሊጣመሩ የሙሽራው ቤተሰብና የሙሽሪት ቤተሰብ በስጋ ዝምድና ሊጣመሩ ቤት ባፈራው እንደአቅም ድግስ በመደገስ የሩቁና የቅርቡ ወዳጅ ዘመድ ልጃችንን ስለምንድር ልጃችንን መርቁልን ማለት የተለመደ ስርዓትና ወግ ነው፡፡

ታዲያ በዕለተ እሁድ ከሩቁ ከቅርብ የተጠራው ቤተዘመዱ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሙሽራው መምጫ ሰዓት ደረሰ ሙሽራው ከነሚዜወቹ ደረሱ የሙሽሪት ቤተሰቦች በጣም ደስ አላቸው እልልታውን አቀለጡት ሙሽራው ሙሽሪትን በቤተሰብ አስመርቆ ወደቤቱ ሊመለስ ሲል ሞቅ ያለ ጭፈራ ሆታ ተነሳ በጭፈራው መሃል ቅልጥ ያለ የጥይት ተኩስም ተተኮሰ በድንገት ጭፈራ ሲጨፈር የነበረው ሰው ፀጥ አለ በጭፈራው መሃል በተተኮስ ጥይት ሙሽራው እና የሙሽራው አባት ወዲያውኑ ህይታቸው ያልፋል፣ አንድ የሴት ሚዜ አና ሰርጉን ለማድመቅ የተገኙ 4 ሰወች በድምሩ አምስት ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን በተደረገላቸው ህክምና ህይወታቸው መትረፉን የወረዳው የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ረ/ኢ/ር ተመስገን ሙሉነህ ተናግረዋለወ። የወንጀል ድርጊት የተሳተፉትን በቁጥጥር ስር አድርገው ምርመራ እያጣሩ መሆኑን ገልፀዋል።

መረጃው የምዕ/ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ነው።

Exit mobile version