Site icon ETHIO12.COM

ሚራክል መኒ በማለት የሃሰት አስተምሮት ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ታገዱ!

ጋድስ ላይት ግሎሪ ኢንተርናሽና ቤተክርስቲያን የተባለውና በኢዮብ ጭሮ /ጆይ ጭሮ/ ዋና መሪነት በሚመራው ቤተ ክርስቲያን በተፈጸሙ ጥፋቶች ዙሪያ ከግለሰቡና ከቤተ ክርስቲያኗ ቦርድ አባላት ጋር በተደረገው ውይይት መሠረት ስህተታቸውን አርመው ለመቀጠል በጽሁፍ ማሳወቃቸውን ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል።

እስራኤል ዳንሳ የተባሉ ግለሰብ በተደጋጋሚ በፈጸሟቸው ጥፋቶች ዙሪያ በተደጋጋሚ ውይይት ተደርጎ ለነበረባቸው ስሁት አካሄድ ስህተት የተባለውን ሁሉ እንደሚያርሙ በሚዲያቸው ወጥተው ይቅርታ እንደሚጠይቁ በማሳወቃቸው፥ ጉዳያቸውም በፍርድ ቤት የተያዘ ስለሆነ፥ ከፍርድ ቤት ውሳኔ በኋላ ካውንስሉ በመተዳደሪያ ደንቡና በአባላት የሥነ ምግባር መመሪያ መሠረት ተጨማሪ ውሳኔ የሚሰጥ ሆኖ ከአስተምህሮና ልምምድ ጋር በተያያዘ ለተነሳባቸው ጥያቄ መታረማቸውንና መስተካከላቸውን መግለጫው ከተሰጠበት ከግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ሁለቱም ለሁለት ወራት በራሳቸው ሚዲያ በግልጽ እንዲያሳውቁ ሆኖ ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ካውንስሉ ያለ ተጨማሪ ውይይትና መግለጫ ቀጣይ እርምጃ እንደሚወስድ በመግለጫው ገልጿል።

“የሲዳማ ብቸኛው ነጻ አውጭ” እና ሲዳማን ለማሻገር ብሎም ነጻ ለማውጣት የተደራጀ ትግል እናደርጋለን በማለት አንድ አገልጋይን ለመሾም በሚል ተጽፎ በማህበራዊ ድረ ገጽ በመዘዋወር ላይ ያለ ደብዳቤ የወንጌላዊያን አማኞችን ገጽታ የሚያጠለሽ መሆኑ መግለጫው ጠቅሶ ይህን ስም የያዘ ተቋም ከየትኛውም የካውንስሉ አባል ቤተ ክርስቲያንም ሆን ህብረት ጋር ግኑኝነት የሌለው መሆኑን አሳውቋል።

Via: ዳጉ ጆርናል

Exit mobile version