ETHIO12.COM

ወልቃይት ጠገዴ” ነጻ ወጥተናል” ሲል ፍትህና ካሳ እንደሚገባው ገለጸ

በወልቃይት ጠገዴ የተለያዩ ከተሞች ህዝብ አደባባይ በመውጣት አቋሙን አስታወቀ። “ተወራሪ እንጂ ወራሪ አይደለንም” በማለት ፍትህን ጠይቀዋል። ግፍ የፈጸሙ ለፍርድ እንዲቀርቡ ድምጻቸውን አሰምተዋል። ከትግራይ ሕዝብ ጋር ምንም ችግር እንደሌለባቸው አመልክተዋል።” ተወራሪ እንጂ ወራሪ አይደለንም” ሲሉም ያለፈውን በደላቸውን ዘርዝረው በመፈክር መልክ አሳይተዋል።

ሰሞኑንን የዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ያሰራጩትን ሪፖርት ተከትሎ በተካሄደው ሰልፍ “የወልቃይት ጠገዴ አማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት የፈፀሙ በህግ ይጠየቁ” ሲሉ ተጎጂዎችንና የተጎጂ ቤተሰቦችን ከፊት በማድረግ ድምጻቸውን አሰምተዋል። እውነታውን የሳተውን የተቋማቱን የሀሰት ሪፖርትን እንደሚቃወሙም ገልጸዋል።

“የዘር ፍጅት ከፈፀመብን ህወሓት እንጅ ከትግራይ ህዝብ ጋር ችግር የለብንም” ሲሉ ድምጻቸውን ያስተጋቡት የወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች ” ከትግራይ ህዝብ ጋር ጥሩ ጎረቤት ሆነን እንኖራለን” ብለዋል። “የዘር ፍጅት ፈፅመው የሸሹት ወንጀለኞች እንጅ ተፈናቃይ አይደሉም” አይደሉም ሲሉ ፍትህን ጠይቀዋል።

አምነስቲ “በምዕራብ ትግራይ በትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረው የጅምላ ግፍ ይፈጸማል” ሲል መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። አምነስቲን ጨምሮ ሌሎች እንደ ሂይውማን ራይትስ ዎች አይነት ተቋማት “ምእራብ ትግራይ” በሚሉትና ወልቃይት ጠገዴ የትግራይ ተወላጆች ተለይተው ለጥቃት መጋለጣቸውንንና ግፍ እየተፈጸመባቸው መሆኑን አትመው ነበር።

ለዚሁ ይመስላል “ተጨፍጫፊ እንጅ ጨፍጫፊ፣ ተበዳይ እንጅ በዳይ፣ ተወራሪ እንጅ ወራሪ፣ ተፈናቃይ እንጅ አፈናቃይ አይደለንም” ሲሉ ተቋማቱ ላወጡት መግለጫ በሰላማዊ ስለፍ ምላሽ የሰጡት።

ሰልፈኞቹ በተለያዩ ከተሞች “አማራ ነን አልን እንጅ አማራ እንሁን ብለን አልጠየቅንም፣ ወንጀለኞች ለህግ ይቀርባሉ እንጅ በተፈናቃይ መልክ እናስፍር አይባልም፣ከትግራይ ጋር ደንበራችን ተከዜ ነው፣ ነፃ ወጥተናል። በህግ ይረጋገጥ። ” የሚሉ መፈክሮችን አሳይተዋል።

በማይካድራ በተካሄደው ሰፊ ህዝብ በወጣበት ሰልፍ ትህነግ በሚያተዳድርበት ወቅት አስራአንድ የቤተሰብ አባላት የተነጠቁበት ቤተሰብ የጉዳታቸው መጠን በሚያሳይ መልኩ ከፊት ሆነው ፍትህን ሲጠይቁ በምስል ታይቷል።

በኢትዮጵያ ከየትኛውም ቦታ፣ ክልልና አካባቢ የተፈናቀሉ ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ብልጽግና በፓርቲ ደረጃ ሙሉ አቋም መያዙ ይታወሳል። በተመሳሳይም ወንጀለኞችን ተጠያቂ የሚያደርግ የፍትህ ማስፈጸሚያ ደንብ እየተዘጋጀ መሆን መገለጹ አይዘነጋም።

በወልቃይት ጠገዴ የተለያዩ ከተሞች የተሰሙት መፈክሮችና ህዝብ ትህነግ ክልሉን ሲመራ በነበረበት ወቅት ለፈጸመው በደል አባላቱ ወይም ወነጀል ፈጻሚዎቹ በህግ እንዲጠየቁ ይፈልጋል። ወንጀለኞችንና የትግራይን ህዝብ ነጣጥለው እንደሚመለከቱም አስታውቀዋል። ከትህራይ ጋር ያላቸው ድንበርም ተከዜ መሆኑ ገልጸዋል።

በትግራይ በተመሳሳይ ወደ ቀደመው ቀያቸው መመለስ እንዳለባቸው በተለያዩ ከተሞች በስለፍ ጥያቄ ማቅረባቸው አይዘነጋም። “ምን አድርገናቸው ነው የማይመሱን” ሲሉ ለቢቢሲ የተናገሩ ችግራቸውን ዘርዝረዋል።

ለመላው ኢትዮጵያዊያን መከራ የነበረውና በተለይ ትግራይ፣ አማራና አፋር ክልልን ስቃይ ውስጥ የጣለው የትህነግ ወረራና ወረራውን ለመቀልበስ በተካሄደ ጦርነት ከፍተኛ ውድመት መድረሱ ሲዘገብ ቆይቷል። በተለይም በሰብአዊ ፍጡራን ላይ ያደረሰው ጉዳት በሪፖርት ሊጠቃለል የማይችል ጠባሳ ነው።

“ወልቃይት ጠገዴ የግፍ መሬት” ሲሉ ቀደም ሲል የገለጹ በአማርኛ መዝፈን፣ መማር፣ ባንዲራ መያዝ… የመሳሰሉ ለመስማት የሚከብዱ በደሎችን ነዋሪዎች ሲገልጹ እንደነበር ይታወሳል።

የትግራይ ሰላማዊ ነዋሪዎች ጋር ምንም ችግር እንደሌለባቸው ያስታወቁት ነዋሪዎች የሰላም ምስክር እንደሆኑ የሚገልጹ” ህዝብ የሚሳተፍበት የመግባባት አውድ ተፈጥሮ፣ ራሱ ህዝቡ መላ እንዲፈልግ ቢደረግ ይሻላል” ሲሉ ይመክራሉ።

Exit mobile version