Site icon ETHIO12.COM

ሙስጣፌ ዑመር ብልጽግናን በታሪክ ለሙስሊሞች ነጻነትና መብት አሉ፤ ይህን በማለታቸው እየተሰደቡ ነው

ገዢው ፓርቲ ብልጽግና ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሰጠውን ዓይነት ነጻነትና መብት የትኛውም መንግስት ከሰጠው የላቀ መሆኑንን መካድ እንደማይቻል የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ዑመር አስታወቁ። ይህን ያስታወቁት በግል የቲውተር ገጻቸው ላይ ነው። በግል የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ ወቀሳና ስድብ እንደሚከተላቸው ይጠበቃል ተብሏል።

“ብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ታሪክ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሰጠውን ነፃነትና መብት ማንም መንግስት አልሰጠም:: ባጋጣሚ በሚፈጠሩ ችግሮች  ምክንያት ብቻ እውነታውን ትቶ ሌላ ስዕል ለመሳል መሞከር የማይታመን ነው ሲሉ በቲውተር አካውንታቸው በእንግሊዝኛ ቋንቋ በፓርቲያቸው ላይ እየቀረበ ያለውን ተቃውሞ እና ወቀሳ ተከላክለዋል::

“እውነታ” ሲሉ ሙስጣፌ እንዳስታወቁት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተሰሚነት፣ ነጻነት፣ የእምነት መብት ያገኙትና ተሰሚነትን የተጎናጸፉት በአገሪቱ ታሪክ ከየትኛውም መንግስታት ይልቅ በብልጽግና ወቅት መሆኑንን አንስተው ” ለዚህ እውነታ አጋጣሚ የተፈጠሩ ሁነቶችን ተንተርሶ የተለየ ስዕል ለመስተት መሞከር የማይታመን ነው” ብለዋል።

ወደ አመራር ከመጡ አፍታም ሳይቆዩ ተወዳጅ እንደሆኑ የሚመሰከርላቸው ሙስጠፌ በሚመሩት ክልል ሁሉን አቻችለው በመምራት የሚታወቁ መሪ በመሆናቸው “ሌሎች ከሳቸው ትምህርት ይውሰዱ” በሚል በውጭም በአገር ውስጥም ያሉ የሚያወድሷቸው ናቸው።

በአዲስ አበባ “መስጊድ ፈረሳን እንቃወማለን” በሚሉ የዕምነቱ ተከታዮች ከጸጥታ ሃይል ጋር ግጭት ፈጥረው የሰው ህይወት ማለፉና፣ ከጸጥታ ሃይሎችም ላይ ጉዳት መድረሱ መዘገቡ ይታወሳል።

መንግስት ታጋሽ ሆኖ ረብሻውንም ሆነ ተቃውሞውን ሰው ሳይጎዳ መቆጣጠር ይገባው ነበር በሚል ወቀሳ መሰንዘሩን ሳያስተባብሉ፣ በደፈናው መንግስት ልክ ሙስሊሙን ህብረተሰብ ለይቶ እንደጎዳ በማስመሰል አጀንዳውን ለጠለፉት ወገኖች ምላሽ የሰጡት ሙስጣፌ ” ለሙስሊሙ የተደርገውንም ማሰብ ይገባል” የሚል ይዘት ያለው አስተያየት መሰንዘራቸው፣ ካላቸው ተሰሚነት አንጻር አጅንዳውን ለመጥለፍ ለሚሯሯጡ እንቅፋት እንደሆነ አስተያየት ተሰጥቷል።

በማህበራዊ ገጾች እነደታየው “የሶማሌ ክልል መሪ ሙስጣፊ ሰሞኑንን የስድብ ናዳ እንደሚያስተናግዱ የጠበቃል” የሚሉ በርክተዋል። በኢትዮጵያ መቃወም እንጂ መደገፍ ውግዝ መሆኑ በርካቶችን የሚያሳቅቅ ጉዳይ እንደሆነ በአደባባይ የሚገለጽ ጉዳይ እንደሆነ ይታወቃል።

መንግስትን በሚደግፉ ላይ ፍረጃ፣ ለሌላ ያልተገባ እርምጃ አሳልፎ የመስጠት፣ ቤተሰብን ሳይቀር ማዋረድ አሁን ላይ የተለመደ ጉዳይ በመሆኑ አቶ ሙስጣፌም ከዚህ የተለየ እንደማይጠብቃቸው መረጃውን ካሰራጩት ክፍሎች ግርጌ እየተጠቆመ ነው።

“ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ” በሚል ስድብ የሳቸውን ቲዊት ካጋሩት ጀመሮ ” ቅሌታም፣ አብይን በስልጣን ለማቆየት ስትል ነው፣ ግብዝ፣ ዋጋ ቢስ…” በሚል ሰደበዋቸዋል። “ትክክለኛ” ሲሉ አድነቀው፣ ድፍረታቸውን አወድሰው ቲውታቸውን ያጋሩም አሉ። ” ውሾቹ ይጮሃሉ” ሲሉ በጀመሩት የግልጽነት አግባብ እንዲቀጥሉ ያበረታቱም አሉ።

Exit mobile version