Site icon ETHIO12.COM

የስንዴ ዋጋ አሻቀበ – የሩስያ ውሳኔ ተከትሎ 8.2 ከመቶ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል

ሩሲያ ከስንዴ አቅርቦት ስምምነት መውጣቷን ተከትሎ በአለም ዓቀፉ ገበያ የስንዴ ዋጋ ማሻቀቡ ተገልጿል፡፡ ሩሲያ በጥቁር ባህር በኩል የዩክሬን የጥራጥሬ ምርቶች ለዓለም ገበያ እንዲቀርብ የተደረሰው ሥምምነት ‘አፈጻጸሙ ጉድለት አለበት’ በሚል ሥምምቱን ቀደም ሲል ማቋረጧን አስታውቃለች፡፡

ይህን ተክትሎም የስንዴ ዋጋ በአውሮፓ ገበያዎች የናረ ሲሆን ካላፉት ቀናት አንፃር ሲነፃፀር 8 ነጥብ 2 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ተመላክቷል፡፡ ጭማሪው ከሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት በኋላ ከፍተኛ በመሆን ተመዝግቧል ነው የተባለው፡፡

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን  ሩሲያ በስንዴ አቅርቦቱ ስምምነት ዙሪያ የምታነሳቸው ጥያቄያዎች ከተስተካከሉ ወደ ስምምነቱ በፍጥነት እንደምትመለስ አረጋግጠዋል።

የዩክሬን የግብርና ሚኒስትር ማይኮላ ሶልስኪ እንደገለፁት÷ በኦዴሳ ወደቦች ላይ በተደጋጋሚ በተፈፀመ ጥቃት 60 ሺህ ቶን እህል ወድሟል።

በተጨማሪም የማጓጓዣ መሰረተ ልማቶች መወደማቸውን ገልፀዋል፡፡

አሜሪካ በበኩሏ የስንዴ ምርት የሚዘዋወርበት የኦዴሳ ወደብ ላይ እና በሲቪሊያን መርከቦች ላይ ለሚፈፀሙ ጥቃቶች ሩሲያ ዩክሬንን ተጠያቂ ማድርጓን ኮንናለች፡፡

ሩሲያ ከስንዴ አቅርቦት ስምምነቱ ከወጣች በኋላ የእህል አቅርቦት የሚደረግባቸውን የዩክሬን ወደቦች ኢላማ አድርጋለች መባሉን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል፡፡

Exit mobile version