Site icon ETHIO12.COM

አፋር “የአንድነታችን አርማ የሆነው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ስም የሚያጎድፍ ማንኛውም አካል አንታገስም”

ኃይልን የመጠቀም ብቸኛ መብት የመንግስት ስለመሆኑ የዘነጉት ትጥቅ ያነገቡ ጽንፈኛና እብሪተኛ ቡድኖች አላማቸው ሀገራችን ከጦርነትና ከድቀት አዙሪት እንዳትወጣ በመሆኑ ለሀገራችን እና ለአማራ ህዝብ ዘላቂ ሰላም ሲባል ጽንፈኛ ቡድኖች ላይ በሚወሰደው የህግ ማስከበር እርምጃ ላይ የአፋር ህዝብና መንግስት የበኩሉን አስተዋጽዖ ያደርጋል፡፡ ጽንፈኛው ኃይል የአማራ ክልል ሕዝብን ለማሰቃየት የተፈጠረ ኃይል እንጂ የአማራ ክልል ወኪል አይደለም።

ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ

ለፈተና የማትበገር ሀገር ኢትዮጵያ !

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ሺህ ዓመታት ታሪክ ያላት የራሷን ሉዐላዊነት ማስጠበቅ የቻለች ሀገር ናት። ታሪካዊ ጣላቶቿንም ቢሆን የውስጧን ሠላም ለማናጋት የሚፈልጉ ከውጭና ከውስጥ ኃይሎች ጋር በመመሳጠር ብዙ ጥረት አድርገዋል። ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ኩራትና መከታ የሆነው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፍላጎታቸውና ተልእኳቸውን እንዳይሳካ አድርጓል።

ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን በሀገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሠላምና ፀጥታ ችግር በአጋጠመ ጊዜ የተሰጠውን የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በብቃት እና በጀግንነት በመፈጸሙ እውቅና ያገኘ ሠራዊት ነው፡፡

ትናንት በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች የሠላምና ፀጥታ መደፍረስ ባጋጠመው ጊዜ ፈጥኖ በመድረስ የዜጎችን ህይወት ታድጓል፡፡ ከራሱ እስትንፋስ በላይ ለሀገርና ለህዝብ ቅድሚያ የሚሰጠው ጀግናዉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በሪፎርሙ በአዲስ መልክ እንዲደራጅ ተደርጓል።

በሰው ኃይል፣ በሎጂስቲክ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የታጠቀ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሆኗል። ጠንካራ መከላከያ ተገንብቷል። መከላከያ የሀገር መከታ የአንድነታችን አርማ ነው። መከላከያን መንካት የሀገርን ሉዐላዊነት መንካት ነው። የአንድነታችን አርማ የሆነው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ስም የሚያጎድፍ ማንኛውም አካል የማንታገሰው መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

የአማራ ህዝብ ባለፉት ሁለት አመታት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ከደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ሳይወጣ ይህ የሠላም እና የፀጥታ ችግር በመከሰቱ ማዘናችንን እየገለጽን በአሁኗ ኢትዮጵያና ብልጽግና መራሽ መንግስት በትጥቅ ትግል የሚመለስ ጥያቄ አይኖርም። በሰከነ መንገድናበውይይት ቢሆን እንጂ።

ጽንፈኛ ቡድኖች በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሱ ላሉ መከራና ስቃይ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ በእጅጉ ያዝናል፡፡ የአማራ ሕዝብ መብቶችና ጥቅሞች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጥቅሞች ጋር የተያያዙ መሆናቸውን መረዳት ያስፈልጋል።

ኃይልን የመጠቀም ብቸኛ መብት የመንግስት ስለመሆኑ የዘነጉት ትጥቅ ያነገቡ ጽንፈኛና እብሪተኛ ቡድኖች አላማቸው ሀገራችን ከጦርነትና ከድቀት አዙሪት እንዳትወጣ በመሆኑ ለሀገራችን እና ለአማራ ህዝብ ዘላቂ ሰላም ሲባል ጽንፈኛ ቡድኖች ላይ በሚወሰደው የህግ ማስከበር እርምጃ ላይ የአፋር ህዝብና መንግስት የበኩሉን አስተዋጽዖ ያደርጋል፡፡ ጽንፈኛው ኃይል የአማራ ክልል ሕዝብን ለማሰቃየት የተፈጠረ ኃይል እንጂ የአማራ ክልል ወኪል አይደለም።

የአፋር ህዝብና መንግስት ከአማራው ወንድም ሕዝብና መንግስት እንዲሁም ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ይሄንን ሀገር አፍራሽ ኃይል እንደሚታገለው እያሳወቅን የተፈጠረውን የፀጥታ መደፍረስ መንግስት ባስቀመጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ሁሉም ነገር መስመር ይዞ የአማራ ህዝብ የተረጋጋ ኑሮ እንዲኖር እና ወደ ቀድሞው አስተማማኝ ሰላም እና ፀጥታ እንዲመለስ የአፋር ህዝብና መንግስት

የበኩሉን ድርሻ ይወጣል፡፡

አፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ነሐሴ 1/2015 ሠመራ

Exit mobile version