ETHIO12.COM

“ማርሽ ቀያሪው ጎንደር ኢትዮጵያዊነቱን አስመሰከረ” የሻለቃ ዳዊት ሃይል እንደ ባህር ዳርና ደብረ ብርሃን ጎንደርንም ተሰናበተ

ጎንደር እንደ ሌሎቹ የአማራ ክልል ከተሞች ሰላም መጎናጸፏ ያስደሰታቸው ያሉትን ያህል “ለምን መከለከያ ላይ አልተኮሳችሁም፣ ሰርጎ የገባውን የሻለቃ ዳዊት ሃይል አልደገፋችሁም” በሚል የተናደዱም አሉ። በርካቶችን ያስገረመው ግን ጎጃም የተወለደው ይህ እንቅስቃሴ ጎንደሮችን ” ባንዳ” ማለቱ ነው።

ጎንደር በኢትዮጵያ ፖለቲካ “ማርሽ ቀያሪ”ይባላል። የሚያደርገውን እንደሚያውቅ የሚነገርለት ጎንደር አንዳንድ እንክርዳዶች ካልሆኑ በቀር በደቦ ስለማይነዳ ትህነግ ለይቶ በኢኮኖሚ በጋራም በግልም ጎልተው እንዳይወጡ፣ ታሪካዊቷ ከተማ እንዳታድግ ሲጫናት እንደኖረ ምስክሮቹ ብዙ ናቸው።

ሰዓቱና ወቅቱን ጠብቆ “የኦሮሞ ደም የእኔም ደም ነው” በማለት የትግል ችቦውን ሲያበራ የትህነግ አከርካሬ መድቀቁን የሚገልጹ ” የበቀለ ገርባ ደም የእኔም ደም ነው” በሚል ኦርሮሚያ የተጀመረውን ትግል እንዴት ቤንዚን እንደረጩበት የሚያስታውሱ ለጎንደር በሳል የትግል አካሄድ አድናቆት መስጠታቸው ይታወሳል።

በወለጋ “በገፊና ጎታች” የፖለቲካ ድርማና ስልታዊ ጥቃት በአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት ሲደርስ፣ በጅምላ ኦሮሞን ማውገዝና መስደብ ሲጀመር፣ ጎንደር ” ጸባችን ክልሉን ከሚመራው ኦህዴድ ጋር ነው” በሚል የትግሉንና የተቃውሞውን መስመር ማስተካከላቸው ሌላ የበሳል ትግል አራማጅነታቸው ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል።

አሁን ደግሞ ” ኢትዮጵያ የአማራ ብቻ ናት” በሚል ጽንፍ የወጣ መፈክር አማራን ከሌላው ህዝብ ጋር አጋጭተው የተቀጠሩበትን አላማቸውን ለማስፈጸም ሲቋምጡ ለነበሩት ሻለቃ ዳዊትና የሚዲያ ተወዛዋዦቻቸው ጎንደር አጭር መልስ መስጠቱ ተሰምቷል። ጎጃም ተጠንስሶ እየሰፋ የመጣውንና ከጎረቤት አገር ድጋፍ የሚደረግለትን የሻለቃ ዳዊት የትግል ጥሪ ” እዛው በጸበልህ” ያሉት የጎንደር ፋኖዎች ” ባንዳ” በሚል እየተሰደቡ ነው።

ጎንደርን ፣ የቴዎድሮስን አገር፣ ጎጃም የተወለደው ዓላማውና ፍላጎቱ ግልጽ ያልተቀመጠ ንቅናቄ ሲሳደብ፣ ” ባንዳ፣ አህያ” ሲል መሳደብና ማውገዝ የጀመረው በትናንትናው ዕለት ” አብይ ተተኳሽ አልቆበታል። አልቆለታል። ጎንደር ትግሉን ተቀላልቀል። በሁዋላ ታለቅሳለህ፡ በሚል ዘመድኩን በቀለ የሚባለውና ራሱን የትግሉ አዝማችና መመሪያ ሰጪ አድርጎ በርካቶችን እየነዳ ያለ የጀርመን ነዋሪ ነው።

ራሱን መንፈሳዊ ዲያቆን አድርጎ የሚያሳየው፣ በምግባሩ የተመረጡ የብልግና ቃላቶችን የሚጠቀመውና አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚገባ ስድብ የሚቀናው አቶ ዘመድኩን / ዘመዴ፣ የጀርመን ፖሊስ አሳልፎ ለኢትዮጵያ ሊሰጠው ጉዳዩ በሂደት ላይ እንዳለ ራሱ መናገሩ ይታወሳል።

አመሻሽ ላይ ” የተወሰነ ጉዳት ደርሶብን ጎንደርን ለቀን ወጥተናል” ሲል የጎንደርን ፋኖ ” የብአዴን ፋኖ፣ ሆዳም ፋኖ” በሚል ዛቻ በንዴት የዘለፈበትን ጽሁፍ በቴሌግራም ገጹ ላይ አኑሯል። ጎንደር ለአገር መከላከያ ክብር ሰጥቶ፣ አልሞና አስቦ የያዘው አቋም ቢያሰድበውም ከተማውን ከሚወደው የመከላከያ ሃይል ጋር ሆኖ አስከብሯል። ለመከላከያ ያሳየው ክብር ለመላው ኢትዮጵያዊያን ክብር ሆኖ በድጋሚ ተመዝግቦለታል። በጎንደር ሙሉ በሙሉ ሰላም መሆን ከተበሳጩት መካከል ቀደም ሲል ኢሳት ይሰራ የነበረው መሳይ መኮንን ይገኝበታል።

መሳይ የጎንደር ታሪካዊ ቅርሶች ወድመዋል ነው ያለው። የጎንደር ምስክሮች እንደነገሩት ጠቅሶ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ” አብይ የአማራን ታሪካዊ ቅርስ እያወደመ ነው” ሲል የጎንደርን ነጻ መሆን በብስጭት አምኗል። ይህን ከማለቱ አንድ ቀን በፊት “ባህር ዳር ሙሽሮቿን ለመቀበል ተዘጋጅታለች” ሲል የጎንደር ጉዳይ የተበላ እቁብ እንደሆነ አስታውቆ ነበር። በዚያው ሞቅታው አንከር ሚዲያ ብቻውን እየተዋደቀ ነውና በጎፈንድ እርዱት ብሎ ጥሪ እይቀረበ 25 ሺህ ዶላር ደርሶ ነበር።

መሳይ የግንቦት ሰባትን መቶ ወታደሮች ሊጎበኝ አስመራ ሄዶ ፐሬዚዳንት ኢሳያስን ቃለ ምልልስ ካደረገ በሁዋላ እሳቸውን እስኪያመልክ ድርሶ ሲያስተላልፍ የነበረውን ፕሮፓጋንዳ ያስታወሱ ” መሳይን ማመን” ማለት ከጀመሩ ሰነባብተው ነበር። መሳይ “ጎንደርን ለመያዝ ከየቦታው ሃይል ሰብስቦ የመጣው የአገዛዙ ሰራዊት መግባት አቅቶት አድፍጦ እየጠበቀ ሌሊቱን አሳልፏል። የፋኖ ታጣቂዎች የተሰዉ አባላትን የቀብር ስነስርዓት ሲፈጽሙ አርፍደዋል። ጎንደር የያዘችውን ይዛ ለሌላ ድል እጇን እያሟሸች ነውመከላከይ አቅቶታል ማለት ነው” ብሎ በጻፈ አንድ ቀን ሳይሞላ ነው ጎንደር ቅርⶃቿ ወደመ ያለው። ደረጀ ሃብተወልድ የሚባለው የትግል ባልደረባውም ከኒዘርላንድ ሆኖ ” አዲስ አበባ ቤቴ ሸተተችን” ሲል በደብረ ብርሃን የሚመጣው ሃይል አራት ኪሎ እንደሚገባ አስታውቆ ነበር።

የኮማንድ ፖስቱ በአጭር ጊዜ ክልሉን ወነበረበት እንመልሰዋለን ባለው መሰረት የቀናው ይምስላል። ህዝብ መካከል በመመሸግ ተኩስ የገጠመው የሻለቃ ዳዊት ሃይል ለበርካቶች ንጹሃን ግድያ ምክንያት እንደሆነ ነዋሪዎች እያመልከቱ ነው። “አንዋጋም” ያሉ ላይና በመደበኛ ጥበቃ ላይ የነበሩ መረሸናቸው ተሰምቷል። ከእስር ቤት እንዲያመልጡ የተደረጉ ቀደም ሲል የከሰሷቸውን ተበዳዮች በመፍለግ እርምጃ እንደወሰዱባቸው ታውቋል። ከቀበሌ ጀምሮ የአገልግሎት ምስጫዎችና የመንግስት ተቋማት፣ የግለሰብ ንብረት ተዘርፏል። እንዲወድም የተደረገም አለ።

ኮማንድ ፖስቱ በደረሰበት ከተማ እያረጋጋና ህዝብ እያወያየ የበደሉን መጠንና ዝርፊያውን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ካሜራዎች ዝግጅታቸውን እይጨረሱ ነው። “ተታለን ነው” ያሉ ምርኮኞች እውነቱን ለህዝብ ለመግለጥ በዝግጅት ላይ ናቸው። አማራ የደረሰበትን በደል ለማስቆምና ፍትህ ለመጠየቅ በሚል ተጀምሮ ደም አፋሳሽ የሆነው፣ ስልጣንን መድረሻው ያደረገውና ” አማራ ብቸኛ የኢትዮጵያ ባለቤት ነው” በሚል መፈክር የርስ በርስ ደም መፋሰስ እንዲነሳ በመጋበዝ የተቋጨው ትግል አድሮ በርካታ አስገራሚ ጉዳዮች እንደሚሰሙበት ይጠበቃል። አሁን ላይ ባለው መረጃ ጎንደር፣ ባህር ዳር፣ ደብረ ብርሃን፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ወልደያ፣ ቆቦ፣ ላሊበላ … ሁሉም የተረጋጉ መሆናቸው ታውቋል። በክልሉ በአብዛኛው በሚባል ደረጃ የሰላሙ ሁኔታ መሻሻል እንዳሳየ ለመረዳት ተችሏል። ኮማንድ ፖስቱ ስራው ይቀጥላል ብሏል። ክልሉም ይህንኑ ረጋግጧል።

የአማራ ማስ ሚዲያ በፋኖ ቁጥጥር ስር ዋለ የተባለውና በቢቢሲ የተዘገበው ሃሰት እንደሆነና መጥነኛ የቴክኒክ ችግር አጋጥሞ ወደ መደበኛ አገልግሎቱ እንደተመለሰ ለማወቅ ተችሏል። ይህን ያስታወቀው ራሱ ሚዲያው ነው።


Exit mobile version