ባህር ዳርና ደብረ ብርሃን ሙሉ በሙሉ ነጻ ሆኑ፤ ጦርነት የገጠመው ግንባሩ “ያሰብነው አልተሳካም” አለ

– የንቅናቄው አመራር እንደሆኑ የሚታወቁ አስመራ መግባታቸው ተሰምቷል፤ የአስመራ መንግስት ከንቅናቄው ጀርባ እንዳለበት በቂ መረጃና ማስረጃ አለ፤ የአስመራው መንግስት ኮንትሮባንድና ዶላር አጠባ ላይም በስፋት ይሳተፋል

  • የኮማንድ ፖስቱም ሆነ የክልሉ አመራሮች በይፋ ያሉት ነገር የለም
  • ቢቢሲ ነዋሪዎች ነገሩኝ ብሎ አሁን ድረስ በከተሞቹ ውጊያ መኖሩን ቢጠቅስም ከባህር ዳር በቀጥታ መረጃ ያደረሱን እንዳሉት መከላከያ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ነው። ጎንደር አልፎ አልፎ ከሚሰማ ተኩስ ውጪ መከላከያ አብዛኛውን አጽድቷል

ሰሞኑንን ባህር ዳርን፣ ጎንደርንና ደብረ ብርሃንን በተመሳሳይ ወቅት ከመቆጣጠር አቅዶ የነበረውና በከተሞቹ ዳርቻና ሰርጎ በመግባት ከመካከል ሆኖ ቀደም ከከተማዎቹ ጸጥታ አካላት ጋር ውጊያ ገጥሞ የነበረውና ራሱን የአማራ ህዝብ ግንባር ከተጠቀሱት ከተማዎች ሙሉ በሙሉ መልቀቁን ገልጾ በማህበራዊ ገጹ አመልክቷል። ትናንትና ደብረ ብርሃንን የከበበው መከላከያ እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ ሃይሉ እየሸሸ መሆኑን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።

የአስቸኳይ አዋጁ አተገባበር በአራት ምድብ ግብረሃይል ተከፍሎ መከላከያ እርምጃ መውሰድ እንደጀመረ በየአቅጣጫው ሁኔታዎች መቀያየራቸው ከየአቅጣጫው የሚወጡ መረጃዎች ቢያመልክቱም፣ እንቅስቃሴውን የሚደግፉ መገናኛዎች፣ የማህበራዊ ገጽ አውዶችና ራሳቸውን አንቂ ያደረጉ፣ በዋናነት በሻዕቢያና ሁለት ኢትዮጵያዊያን የሚደገፈው የመረጃ ቲቪ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን በፋኖ እጅ መውደቃቸውን፣ “መከላከያ አልዋጋም ብሎ መሳሪያ እያስረከበ ነው፣ በብዛት እየተማረኩ ነው” የሚሉ ቪዲዮዎችን በማሠራጨት የድል ዜና ሲያሰሙ ነበር።

አገር አማን ብለው በጥበቃ ስራ ላይ የነበሩ “ተነጣይ ሃይሎች” ወይም በቁጥር ጥቂት የሆኑ የመከላከያ አባላትን በጅምላ በመክበብና መሳራሪያቸውን በመንጠቅ፣ ልብሳቸውን በማስወለቅ፣ መሬት ላይ በማስተኛትና ጸያፍ ቃላትን በመጠቀም ሲያሰቃዩ የሚያሳዩ ምስሎችን በመጠቀም ” መከላከያ አበቃለት” በሚል እስከ ማለዳው ድረስ የድል ዜና ሲሰራጭ ነበር። የአካባቢ ነዋሪዎች ነገሩን በሚል ገጻቸው ላይክ እንዲደረግ የሚማጸኑ የዩቲዩብ አምደኞች “አሁን ድረስ ደብረብርሃን፣ ባህር ዳርና ጎንደር በፋኖ እጅ ነው። መከላከያ እየገባ ነው። የሁመራ አውሮፕላን ማረፊያ ወታደር እየተራገፈ ነው” ሲሉ አርፍደዋል።

“ይሁን እንጂ ራሱን የአማራ ህዝባዊ ግንባር፣ ወይም የፋኖዎች ጥምረት የሚለው ሃይል “ይሁን እንጂ ራሱን የአማራ ህዝባዊ ግንባር፣ ወይም የፋኖዎች ጥምረት የሚለው ሃይል “ለጊዜው ባህር ዳርና ደብረ ብርሃን ላይ እንዳሰብነው ስላልሆነ ለቀን ለመውጣት ተገደናል” የሚል ማረጋገጫ በማህበራዊ ገጹ አሰራጭቷል።

See also  የኬሪያና የጃዋር ድብቁ ግንኙነትና አዲሱ የቤት ውስጥ እስር

በባህር ዳር በሚቋቋመው አዲስ መንግስት ለሹመት የታጩ ባህር አስቀድመው ገብተው ነበር። ይሁንና አሁን ላይ መከላከያ እያካሄደ ባለው ማጥራት እየተያዙ መሆኑን ጉዳዩን የሚከታተሉ አመልክተዋል። በተመሳሳይ ጎንደር ከተማን ከቦ እያጸዳ ያለው መከላከያ በተመሳሳይ ስራውን ወደ ማተናቀቁ መቃረቡ ተሰምቷል። በአማራ ክልል የተጣለውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያስፈጽመው ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ሕግ የማስከበር ሥራውን በማከናወን ክልሉን ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው በአጭር ጊዜ እንዲመለስ ማስታወቁ አይዘነጋም።

ይህ በእንዲህ እያለ ” ኢትዮጵያን የፈጠረ፣ ያጸናና ለዓለም ያስተዋወቀው ብቸኛው የኢትዮጵያ ባለቤት አማራ ነው” በማለት ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችን ያስቀየመ መግለጫ የሰጡት የንቅናቄው መሪ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ረዳት የመዋቅሩ አካል የሆኑ አስመራ መግባታቸውን ተሰምቷል። ጉዳዩ ከመሳሪያ እርዳታ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ግምታቸውን ያስቀመጡ እንዳሉት መንግስት ዝምታን መርጦ እንጂ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ እጅ ከጦርነቱ ጀርባ ስለመኖሩ ከበቂ በላይ ማስረጃና መረጃ እንዳለው ጉዳኡን የሚከታተሉ አስታውቀዋል። አስፈልጊ ሲሆን ይፋ እንደሚያደርጉ አመልክተዋል። አያይዘውም የኢሳያስ መንግስት ያሰማራቸው የውጭ ምንዛሬ ሰብሳቢዎችና ኮንትሮባንድ አስተላላፊዎች ሆነው እየሰሩ መሆኑን እነዚሁ ክፍሎች አመልክተዋል።

ለበርካታ ዓመታት በማዕቀብ ስር የቆየችው፣ ምርጫና ህገ መንግስት የማታውቀው ኤርትራን የሚመሩት ኢሳያስ አፉወርቂን ሽሽት ከስምንት መቶ ሺህ በላይ የኤርትራ ተወላጆች በኢትዮጵያ ከነሙሉ ክብራቸው እየኖሩ መሆኑ ይታወቃል።Leave a Reply