Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ ወደብ እያነፈነፈች ነው፤ መንግስት አለሳልሶ “አማራጭ ወደብ” የሚለው የባህር በር ጉዳይ አጀንዳነቱ ሰፍቷል

ባለፉት ወራቶች ከምን ጊዜውም በላይ ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት መሆን እንዳለባት የሚያስረግጡ ዜናዎች እየተሰሙ ነው። ይህ የኢትዮጵያዊያን ሁሉ ቁጭትና የትህነግ የሃፍረት ታሪክ የሆነው ኢትዮጵያን የባህር በር አልባ ያድረገ የክህደት ውሳኔ “እንዴትና መቼ ይስተካከላል?” የሚል ጥያቄ በስፋት የሚነሳበት እንደሆነ ይታወሳል። አሁን ላይ ኢትዮጵያን በጦርነት የማመሳቀሉ አጀንዳ ከዚህ ጋርም ተያያዥነት እንዳለው እየተገለጸ ነው።

ኢትዮጵያ አሰብን የማስመለስ ህጋዊ መብት እንዳላት ከሚገልጹ ምሁራን በተጨማሪ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ኢትዮጵያ አሰብን መረከብ እንዳለባት የሚሰማው ድምጽ አሁን ላይ እየገፋ ነው። አንድ ሚሊዮን የሚልቁ የኤርትራ ተወላጆችን አቅፋና ደግፋ ያለ አንዳች ልዩነት የምታስተዳድረው ኢትዮጵያ፣ ለዚህ አገልግሎቷ እንደውጭ አገር ዜጋ የኤርትራ ተወላጆችንም ሆነ የአስመራውን መንግስት የምትጠይቀው ስባሪ ሳንቲም፣ ግብር፣ ወይም እንደ ሌሎች የውጭ ዜጎች አንድም የአገልግሎት ክፍያ ወይም የውጭ ምንዛሬ የክፍያ አግባብ ስለማትጠይቅ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ አሰብን የመጠቀም መብት ልታገኝ እንደሚገባ የሚከራከሩም አሉ። እየጋመ የመጣው የአፋር ሃይሎች የአሰብ ወደብ የባለቤትነት ጥያቄንም የሚያነሱ አሉ።

” ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የምታነሳውን ጥያቄ ሊደግፉ ይገባል” ሲሉ የፍትህ ዕይታን የሚጠይቁም አሉ። እነዚህ ዜጎችን የአፋር ምድር ላይ የሚገኘውን የኢትዮጵያን ህጋዊ ንብረት የሆነውና በትህንግ አመራሮች ሴራ ለሻዕቢያ የተሸለመውን አሰብን ወደብ ኢትዮጵያ የአፋርን ንቅናቄ የራስዋ በማድረግ ልታንቀሳቅሰው እንደሚገባ ያምናሉ። አሁን ላይ ኤርትራ እያሰለጠነች የምታሰማራቸውና እዛም እዚህም ጦርነት የሚከፍቱ ሃይሎች የአሰብ አጀንዳ እንዲኮላሽ፣ አገሪቱ ስትበጣበጥ የአሰብን አጀንዳ እንድትልቅ ለማድረግ በመሆኑ መንግስት መለሳለሱን አቁሞ የአፋር ሃይሎችን አጀንዳ ማጉላት ይገብዋል ባይ ናቸው።

ይህ በማህበረሰብ ደረጃ የሚነሳና እዛም እዚህም በተለያዩ አውዶች የሚሰማ ፍላጎት ነው። በመንግስት ደረጃ ግን የባህር በር የማግኘት ጉዳይ መንገዱ ይፋ ባይሆንም ቁርጥ አቋም የሆነ ይመስላል። ኢትዮጵያ እየገነባች ያለው ዘመናዊ የባህር ሃይል የዚሁ አመላካች ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ “ኢትዮጵያ በቀይባህር ፖለቲካ ተጽዕኖ ፈጣሪ አገር ትሆናለች” በሚል መሪዎቿ በተደጋጋሚ ማስታወቃቸው ነገሩን ያጠናክረዋል።

ከሁሉም በላይ ግን ከቀናት በፊት ኢትዮጵያና ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ (UAE) ያደረጉት ስምምነት ኢትዮጵያ ስሙ አልታወቅም እንጂ ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ስለመሆኗ አመልካች እንደሆነ “ገብቶናል” የሚሉ ከቅርብና ሩቅ እየገለጹ ነው። የተባበሩት ኤመሬትስ መንግስት ሙሉ ካቢኔ፣ በሌላ አነጋገር ሙሉ የንጉሳዊውን ቤተሰብ በአንድ አውሮፕላን ይዞ ለስራ ወደ ሌላ አገር ሲጓዝ ይህ በታሪክ የመጀመሪያ እንደሆነ ተመልክቷል። አያድርገውና አንድ ነገር ቢሆን አገሪቱ ምን ልትሆን እንደምትችል አስልተው “እንዲህ ዓይነት ውሳኔ ወስነው ኢትዮጵያ የመጡት የምር የሚሰራ ነገር ቢኖር ነው” በሚል ይገልጻሉ።

ከዚሁ ጉዞ ጋር ተያይዞ ከተፈረሙት አስራ ሰባት ስምምነቶች አንዱ የንግድና ሎጂስቲክ ጉዳይ ነው። ከደህንነት ስምምነቱ ቀጥሎ ቀልብ የሳበውና በንግድና ሎጂስቲክ ስምምነቱ ስር ከDP World ጋር በቅንጅት ይሰራል) እንዲሁም በአፍሪካ ግዙፍና ዘመናዊ የባህር ሃይል ባለቤት ለማድረግ እየተሰራ ነው። ይህ ከመቶ ሃምሳ አገራት ከመቶ ሺህ በላይ ሰራተኞችን ይዞ የዓለምን የወድ ንግድ ትራንስፖርት የሚያሳልጠው ድርጅት ከኢትዮጵያ ጋር በሎጂስቲክ ለመስራት መስማማቱ አሁንም ኢትዮጵያ ወደብ የምታገኝበትን አጋባብ መቃረብ አመላካች እንደሆነ አድርገው የሚወስዱ፣ የዘመናዊ ባህር ሃይል ግንባታውም የዚሁ ማረጋገጫ ነው ባይ ናቸው።

ከዚህ በላይ ግን የቀይ ባህር ፖለቲካ ውስጥ ኢትዮጵያ ዘው ብላ ልትገባ ከጫፍ መድረሷን የሚያሳየው ሲዊዝ ካናልን ሳይጠቀሙ በቀጥታ ወደ ህንድ ውቅያኖስ በመዝለቅ መዝለቅ የሚያስችለው የኤላት ወደብ ጉዳይ ነው። የምስራቅ ቀይ ባህር ክንፍ ወይም አካል የሆነውን ይህንን የእስራኤል ወደብ ከአስራ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በሚልቅ ወጪ አዘምኖ ንግዱን ለማሳለጥ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስና እስራኤል ውል ማሰራቸው ይታወሳል። ዝርዝሩ ባይቀርብም ኢትዮጵያ እዚህ ፕሮጀክት ውስጥ እንዳለችበት ይሰማል። ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ እንደሚሉት ይህ ሲዊዝ ካናልን ፋይዳ የሚገድለው ኤላት ወደብ ላይ ኢትዮጵያ ተሳትፎዋ ሰፊ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በልዩ አቀባበል እስራኤልን በጎበኙበት ወቅት ለጠቅላይ ሚኒስትር ኔትናሁ የአረብ ኤምሬስት ፕሬዚዳንት ቀና፣ ብልህና አብሮ በመስራት የሚያምኑ መሆናቸውን ጠቅሰው አብረው በረካታ ስራዎችን መስራት እንደሚችሉ ብዙም ዝርዝር ውስጥ ሳይገቡ መናገራቸውን የሚያስታውሱ፣ እርሾው ከዛ እንደሚጀምር ይጠቁማሉ።

ከላይ ከተነሱት ነጥቦች መነሻ ከአርብ ኤምሬትስ ታዋቂና ግዙፍ DP World የሎጂስቲክ አሳላጭ ድርጅት ጋር አብራ ለመስራት ኢትዮጵያ መስማማቷ፣ በአፍሪካ ውስጥ ቀዳሚ የጭነት መርከቦች ባለቤት፣ ተወዳዳሪ የወደብ አቅራቢ ሃገር ለመሆን ከያዘችው ዕቅድ ጋር የተጋባ ሆኖ ተገኝቷል። ከዚሁ ጋር የመንግስት መገናኛዎች ኢትዮጵያ አማራጭ ወደቦችን ለመጠቀም እየሰራች መሆኗን አመልክተዋል። በዜናው “አማራጭ ወደቦች” በሚል ሌላ የንግድ ኮሪደር እና የኬኒያውን ላሙ ወደብን ጨምሮ አማራጭ ወደቦችን በማየት ከሚመለከታቸው ሀገራት ጋር እየሰራች መሆኑን ቢግለጽም፣ ሌላ የተባሉት አማርጭ ወደቦች አልተብራሩም።

The Port of Eilat is the only Israeli port on the Red Sea, located at the northern tip of the Gulf of Aqaba. The Port of Eilat was opened in 1947 and is today mainly used for trading with Far East countries. It allows Israeli shipping to reach the Indian Ocean without having to sail through the Suez Canal.

ኢትዮጵያ ትልቅ አገር እንደምሆኗና እያደገ የመጣውን ፍላጎቷን፣ የወጪ እቃዎችን ለማጓጓዝ የጅቡቲ ወድብ ላይ መቸከሉ ከውጪም ሆነ ከስፋት አንጻር አዋጪ እንዳልሆነ መንግስት በይፋ አመልክቷል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት የሚሸከም የተቀላጠፈ የወጪና ገቢ ንግድ ሎጂስቲክስ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከህዝብ ብዛት ባሻገር በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ፈጣንና ግዙፍ ኢኮኖሚ ቢኖራትም የወጪና ገቢ ንግዷ በዋናነት በጅቡቲ ወደብ በኩል ይከናወናል፡፡ ይህም እያደገ ከመጣው የተቀላጠፈ የሎጅስቲክ አግልግሎት ፍላጎት አንጻር ትልቅ ማነቆ መፍጠሩ ነው የተገለጸው፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት የሚሸከም የተቀላጠፈ የወጪና ገቢ ንግድ ሎጂስቲክስ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

እስካሁን 96 በመቶ የሚሆነው የወጪና ገቢ ንግድ በጅቡቲ በኩል እንደሚደረግ ገልፀው፤ ይህም ከሚፈጠረው መጨናነቅ ባሻገር ከጊዜና ወጪ ረገድም ትልቅ ችግር መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ አማራጭ ወደቦችን መጠቀም የሚያስችሉ ስራዎች እያከናወነች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህም የበርበራ ኮሪደር እና የኬኒያውን ላሙ ወደብን ጨምሮ አማራጭ ወደቦችን በማየት ከሚመለከታቸው ሀገራት ጋር እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል።

በቅርቡ በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዶክተር ዓለሙ ስሜ የተመራ ልዑክ በመልማት ላይ የሚገኘውን የላሙ ወደብ ለመጠቀም ከኬኒያ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረጉን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ ሁለቱን ተጨማሪ ወደቦች መጠቀሟ ኢትዮጵያን፣ ኬኒያንና ደቡብ ሱዳንን በትራንስፖርት የሚያስተሳስረው ‘ላፕሴት’ ለተሰኘው ፕሮጀክት መሳለጥ ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው አመላከተዋል።

የላሙ ኮሪደር ወደ ስራ መግባትም የኢትዮጵያ የገቢና ወጪ ንግድን በማሳለጥ በኩል ትልቅ ሚና እንደሚኖረውም ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ብልፅግናዋን ለማረጋገጥ እና እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚ ለማስተናገድ የሎጂስቲክስ ስርዓት ማዘመንና ማስፋት ላይ በትኩረት እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።

የብዝሀ ወደብ አጠቃቃም ለማስፋትም ቀጣይ ዲፕሎማሲያዊ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የላፕሴት ፕሮጀክት በአማራጭ የወደብ አጠቃቀምን ከማሳለጥ በተጨማሪ አፍሪካን እርስ በርስ በንግድ ለማስተሳሰር ግብ ይዞ ወደ ትግበራ ለገባው የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ስኬት ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።

የሞጆ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያን ጨምሮ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ መሰረተ ልማትን በመዘርጋት ኢትዮጵያ የሎጂስቲክስ ማዕከል እንድትሆን እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በጎረቤት ሀገራት በኩል የሚገነቡ መሰረተ ልማቶች ሲጠናቀቁ በጋራ የመበልፀግ፣ አፍሪካን የማስተሳሰር እንዲሁም ለኢትዮጵያም ትልቅ የገበያ ዕድል ለመፍጠር ሁነኛ ፋይዳ እንዳለው ነው ያነሱት።

የባቡርና የመንገድ መሰረተ ልማት ዝርጋታን ጨምሮ በላብሴት ሰባት ፕሮጀክቶች እንደሚገነቡ ገልጸው፤ ኢትዮጵያ እስከ ሞያሌ ያለውን ፈጣን መንገድ ጨምሮ የበኩሏን ሃላፊነት መፈጸሟን ተናግረዋል።


Exit mobile version