ETHIO12.COM

ሐማስ ታጋቾችን ለመልቀቅ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠየቀ፤ ዓለም ሰብአዊነት ነጥፎባታል ከ5ሺ በላይ የሰው ልጅ አልቋል

ጋዛ 3 ሺህ 478 ሰዎች አጥታለች። 12 በላይ ቆስለዋል። በዌስት ባንክ 69 ሲሞቱ፣ 1300 ቆስለዋል። ከእስራኤል ወገን ደግሞ 1400 ሰዎች ሲሞቱ 3ሺህ 800 ያህል ቆስለዋል። መረጃውና አሃዙ በየደቂቃው፣ ሰዓቱና ቅጽበት ሁሉ ይለዋወጣል። የሰው ልጅ ይረግፋል። በጥማትና ጠኔ ያልቃል። በመድሃኒት እጥረት ይሰቃያል። መራራት የሚባለው የሰውነት መለያ ሞቶ እርኩስነት በተሞላው እርምጃ ከሁሉም ወገን ንጹሃንና ህጻናት ያልቃሉ። ዓለም የዩክሬንን የውክልና ጦርነት በመገረም እልቂቱን እያየች ባለበት ሰዓት የተጀመረው ይህ ጦርነት “ቀጥሎስ” እያስባለ ነው።

ሃማስ ሲጀምረው “እስከዛሬ በእስራኤል ለተገደሉ ሁሉ የደም ምላሽ ነው” ያለው ጥቃት ከእስራኤል ወገን ምላሽ መሰተት ከጀመረ በሁዋላ በሺዎች ሞተማዋል። በመቶ ሺህ ተፈናቅለዋል። መሰረት ለማት፣ መጠለያ ጎጆ፣ ተዘርዝሮ የማያልቅ ሰባዊና ቁሳዊ ውድመት ደርሷል። የሚቆም አይመስልም። ሌሎች አገሮችም ተንደርድረው ጦርነቱን እገሃድ እየተቀላቀሉ ነው።

አስልታ በመሳሪያ ሃይል ታላላቅ የሚባሉት አገር የተቀላቀለችው ኢራን በግልጽ ሃማስ የወሰደውን እርምጃ “አርኪ” ካለችበት ቅጽበት ጀመሮ ከጀርባ ስትረዳ መኖሯ ቀርቶ በገሃድ ለፍልስጤም አጋርነቷን ጦርነቱን በመቀላቀል ለማሳየት ወስናለች። ሌሎችም እንዲነሱ ጥሪ እያቀረበች ነው። በሌላ አቅጣቻም ሂዝቦላ በስፋት ጥቃት ለመሰንዘር ዝግጅቱን አጠናቆ፣ ሲለውም ሮኬት እያስወነጨፈ ማሟሟቅ ይዟል።

አሜርካ እሳት የሚተፉትን መርከቦቿን አከታትላ ላካለች። ሂዝቦላና ፑቲን እንዲያሸንፉ አይፈቀድም ስትል በባይደን በኩል ፎክራ ወደ እስራኤል የሚላክ ሚሳይል ማክሸፍ መጀመሯ ተሰምቷል።

ባለጡንቻዎቹ ቻይናና ሩሲያን ማስጠንቀቂያና ማሳስቢያ እይሰጡ ያሉበት ይህ አውዳሚ ጦርነት የሰሜን ኮሪያንም አንደርድሮ ከቷል። በዚህ ሁሉ ጡዘት ውስጥ የሰብአዊ ድጋፍ መመናመን እጅግ አሳሳቢ መሆኑ ገኖ ቢወጣም ጭካኔና እልቂትን የመረጡት መሪዎች አረር ማዝነባቸውን አስቀድመዋል።

ሐማስ ከእስራኤል አግቶ ከወሰዳቸው ከሁለት መቶ በላይ ታጋቾች መካከል የተወሰኑ እስረኞችን በመልቀቅ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ንግግር እየተካሄደ መሆኑ ተዘገበ።

ቢቢሲ ከምንጮቹ እንደተነገረው በሐማስ ታግተዋል ተብለው ከሚታመኑት 203 ሰዎች መካከል አብዛኞቹን ለማስለቀቅ የሚደረገው ንግግር መቀጠሉን እና ሐማስ በምትኩ አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ መጠየቁ ተገልጿል።

ነገር ግን እስራኤል እስካሁን በቀረበው ሃሳብ አለመስማማቷ ተነግሯል።

በዓለም አቀፍ አሸማጋዮች አማካይነት እየተደረገ ያለው ድርድር ትኩረቱን ጋዛ ውስጥ ተይዘው በሚገኙት በታጋቾች ላይ አድርጎ እየተካሄደ ይገኛል። የዚህን ንግግር ዝርዝር በተመለከተ ከሁለቱም ወገን በይፋ የተሰጠ ማረጋገጫ የለም።

በእገታ ስር ያሉት ሁሉም ሰዎች ሐማስ እጅ ያሉ አለመሆናቸው የተነገረ ሲሆን፣ የተወሰኑት በሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ቁጥጥር ስር ናቸው ተብሏል።

ጋዛ ውስጥ በእገታ ላይ ያሉት ሰዎች ሁኔታ የእስራኤል ጦር አዛዦች ወደ ጋዛ ዘልቆ በመግባት ሊያደርጉት ያሰቡትን ዘመቻ ካወሳሰቡባቸው ምክንያቶች አንዱ ነው።

ታጋቾቹን ከወታደራዊ እርምጃ ይልቅ በድርድር እንዲለቀቁ ማድረግ በሕይወት ወደ አገራቸው የመመለስ ዕድላቸውን ከፍ ያደርገዋል።

መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ሐማስ እስራኤል ውስጥ ዘልቆ በመግባት በፈጸመው ድንገተኛ ጥቃት ከ1400 በላይ ሰዎችን መግደሉ የተዘገበ ሲሆን፣ 200 የሚሆኑ ሰዎችንም አግቶ ወደ ጋዛ ሰርጥ መውሰዱን የእስራኤል ጦር ሠራዊት አስታውቋል።

ሠራዊቱ ባወጣው አዲስ መግለጫ ላይ የታጋቾቹን ዝርዝር ሁኔታ ይፋ አድርጓል። በዚህም መሠረት ከታገቱት 203 ሰዎች መካከል ከ20 በላይ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ናቸው።

ከአስር አስከ ሃያ የሚደርሱት ደግሞ ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ ሲሆን፣ ከታጋቾቹ መካከል አብዛኞቹ በሕይወት መኖራቸውን የገለጸው የእስራኤል ሠራዊት፣ የሟቾች አስከሬን እንደ ታጋች ወደ ጋዛ መወሰዳቸውንም ጠቅሷል።

በጋዛ በርካታ ክርስቲያኖችን ያስጠለለው የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን በአየር ጥቃት ተመታ

በጋዛ የሚገኝ እና በርካታ ክርስቲያኖችን አስጠልሎ የነበረው የግሪክ የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን በአየር ጥቃት ተመታ።

ጥቃቱን በተመለከተ ሐማስ ባወጣው መግለጫ የቅዱስ ፖርፊየስ ቤተ-ክርስቲያን ያጋጠመው ከፍተኛ ፍንዳታ በሕንጻው ላይ ከባድ ጉዳት ማስከተሉን እና በርካቶችን መጉዳቱን አስታውቋል። ሐማስ ጥቃቱ የተፈጸመው በእስራኤል ጦር ነው ብሏል። የእስራኤል መከላከያ ኃይል ግን ቤተ-ክርስቲያኑን ዒላማ አለማድረጉን ይገልጻል።

ጦሩ ለፈንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ እንደገለጸው የተዋጊ ጄቶቹ ጥቃት የታጣቂዎችን የሮኬት እና ሞርታ ጥቃት ትዕዛዝ መስጫ ማዕከለን መምታታቸውን ተከትሎ በአካባቢው ያለችው ቤተ-ክርስቲያን ግድግዳ ወድሟል ብሏል።

ቢቢሲ በቤተ-ክርስቲያኗ እና በሰው ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን ማወቅ ባይችልም ኤኤፍፒ ያጋራቸው ምስሎች በእምነት ቤቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

የእየሩሳሌም የኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ጥቃቱን አጥብቀው በማውገዝ ባወጡት መግለጫ ለፍንዳታው ምክንያት የሆነው የእስራኤል የአየር ጥቃት ነው ብለዋል።

የሠላማዊ ዜጎች መጠለያ በሆኑት በአብያተ ክርስቲያናት እና በተቋሞቻቸው ላይ የሚፈጸመው ጥቃት “ቸል ሊባል የማይችል የጦር ወንጀል ነው” ብለዋል በመግለጫቸው።

ቅዱስ ፖርፊየስ ቤተ-ክርስትያን ከ12ኛው ክፍለ ዘመን በፊት የተመሠረተ ሲሆን፣ ባለፈው ማክሰኞ በከባድ ፍንዳታ ተመትቶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተገደሉበት አል አህሊ ሆስፒታል በቅርብ ርቀት ይገኛል።

ዓለም ‘ሰብዓዊነቷን እያጣች ነው’ – የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት – ተመድ

በእስራኤል እና በሐማስ መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት ምክንያት መካከለኛው ምስራቅ “በገደል አፋፍ ላይ ነው” ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊ የሆኑት ፊሊፕ ላዛሪኒ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የተመድ የፍልስጤም ስደተኞች የእርዳታ ኤጀንሲ ኮሚሽነር የሆኑት ላዛሪኒ “ዓለም አሁን ሰብዓዊነቷን እያጣች ነው” ብለዋል። ግጭቱ ወደ ሌሎች ቦታዎችም ሊስፋፋ እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል።

በጋዛ ያሉ ሰላማዊ ሰዎች ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ ያነሱት ላዛራኒ፤ በአካባቢው የሰብዓዊ እርዳታ ኮሪደሮች እንዲከፈቱም ጥሪ አቅርበዋል።

ሐማስ በእስራኤል ላይ ያደረሰውን ጥቃት ያወገዙት ላዛራኒ፤ “አሰቃቂው እና አረመኔያዊው እልቂት እስራኤል ውስጥ ድንጋጤን ፈጥሯል” ሲሉ ተናግረዋል።

“ይህ ክስተት ግን ጦርነቱ ያለ ምንም ገደብ እንዲካሄድ ምክንያት አይሆንም። ተጨማሪ ሠላማዊ ዜጎችን መግደል ለቀጣይ ሠላም ጠቃሚ ነው ብዬ አላምንም” ብለዋል።

በጋዛ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ በተፈፀመ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገደሉ

ሃማስ ጥቃቱን እስራኤል ነው የፈፀመችው ብሏል።

የእስራኤል መከላከያ ደግሞ ” ኢስላሚክ ጂሃድ ” የተባለው ቡድን እስራኤል ላይ ያስወነጨፈው ሮኬት ዒላማው ሳይሳካ ቀርቶ የተፈጠረ ነው ብሏል።

ትላንት ጋዛ ውስጥ በሚገኘው “አልአህሊ ባፕቲስት ሆስፒታል ” ላይ በደረሰ የአየር ጥቃት በትንሹ 500 ሰዎች መገደላቸውን በጋዛ  የሚገኘው ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሃማስ ጥቃቱን እስራኤል ነው የፈፀመችው ብሏል። ጥቃቱን ” የጦር ወንጀል ነው” ሲል ገልጾ ” ሆስፒታሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ የታመሙ እና የቆሰሉ ሰዎች ነበሩበት ብሏል።

የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ፤ በጋዛ የሚገኘው ሆስፒታል የተመታው ባያልተሳካ የ ” እስላሚክ ጂሃድ ” ቡድን ሮኬት ነው ብሏል።

ያልተሳካ ሮኬት ያስወነጨፈው ይኸው ቡድን ለሆስፒታሉ መመታት ተጠያቂ ነው ሲል ገልጿል።

” እኛ ሆስፒታሉ ላይ ጥቃት አልፈፀምንም ” ብሏል።

የ ” ፍልስጤም እስላሚክ ጂሃድ ” ድርጅት የእስራኤል ክስ ሀሰተኛ እና ምንም መሰረት የሌለው የተለመደ ቅጥፈት ነው ብሏል። እስራኤል ከተለመደው ጭፍጨፋ ተጠያቂነት ለማምለጥ በፍልስጤማውያን እና ‘ ኢስላሚክ ጂሃድ ‘ ላይ ጣቷን ለመጠቆም የፈጠረችው ሀሰተኛ ፈጠራ ነው ሲል ገልጿል።

” ፍልስጤም እስላሚክ ጂሃድ ” እኤአ 1981 የተመሰረተ ሲሆን በጋዛ እና ዌስት ባንክ ውስጥ ይንቀሳቀሳል።

በሌላ በኩል ፤ የፍልስጤም ፕሬዜዳንት ማሃሙድ አባስ በሆስፒታሉ ላይ በተፈፀመው ጥቃት እና በጠፋው የሰው ህይወት ምክንያት የ3 ቀን ሀዘን አውጀዋል።

በሆስፒታል ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ሀገራት እና ተቋማት እያወገዙ ይገኛሉ። በተለያዩ ከተሞችም እስራኤልን የሚያወግዙ ሰልፎች እየተደረጉ ይገኛሉ።

ዓለም ለጋዛ ሆስፒታል ለደረሰው ጥቃት ምን ምላሽ ሰጠ ?

እስራኤል የአየር ጥቃቱን ፈፅማለች ብለው የከሰሱና ያወገዙ ፤ በጉዳቱ ሀዘናቸውን የገለፁ ፦

🇪🇬 የግብፅ ፕሬዝዳንት
🇯🇴 የዮርዳኖስ ንጉስ
🇸🇾 የሶሪያ ፕሬዝዳንት
🇨🇺 የኩባ ፕሬዝዳንት
🇮🇶 የኢራቅ መንግስት
🇸🇦 የሳዑዲ አረቢያ መንግስት
🇹🇷የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
🇻🇪 የቬንዙዌላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
🌍 የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሃላፊ
🇮🇷 የኢራን ፕሬዝዳንት (እስራኤል ብቻ ሳትሆን አሜሪካም ጭምር ከእስራኤል ጋር ሀላፊነት ትወስዳለች ብለዋል)

ጥቃቱን ያወገዙ ነገር ግን ማንንም ያልወቀሱ ፤ ይልቁንም ምርመራ እንዲደረግ የጠየቁ ፦

🇪🇺 የአውሮጳ ዲፕሎማሲ ኃላፊ
🇫🇷 የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት
🇳🇱 የኔዘርላንድስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
🇪🇸 የስፔን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
🇬🇧 የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት
🇯🇵 የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
🇺🇸 አሜሪካ ማንም ሳትከስ ነገር ግን ስለ ተፈጠረው ሁኔታ ተጨማሪ መረጃዎችን ሰበስባለሁ ብላለች።

” ማስረጃ አቅርቢ ” – ሩስያ

🇷🇺 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስራኤል በጥቃቱ ላይ የለሁበትም ካለች የሳተላይ ምስሎችን በማስረጃነት ታቅርብ ብሏል።

በጋዛ 100 የእርዳታ ተሽከርካሪ መድረስ እንዳለበት ተመድ ገለጸ

የእርዳታ ተቋሞች እንዳሉት፣ ጋዛ በአንድ ቀን ውስጥ ከ20 በላይ እርዳታ የያዙ የጭነት መኪናዎች መድረስ አለባቸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከእስራኤል ጉብኝታቸው ትላንት ከተመለሱ በኋላ ለጋዛ በቀን 20 መኪና እርዳታ ለማስገባት ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ እርዳታ ኃላፊ ማርቲን ግሪፍትስ እንዳሉት፣ በአንድ ቀን ውስጥ 100 የሚጠጉ እርዳታ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ጋዛ መድረስ አለባቸው።

ግብጽ ወደ ጋዛ የሚያሻግር ድንበሯን መልሳ ለመክፈትና የእርዳታ መኪኖቹን ለማሳለፍ ተስማምታለች። ዝግጅትም እየተደረገ ይገኛል።

ለፍልስጤማውያን እርዳታ እንዲደርስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች እንደቀጠሉ ነው። የግብጽ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አል-ሲሲ የዮርዳኖሱን ንጉሥ አብደላህ ዛሬ ይቀበላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ግብጽ እና ዮርዳኖስ ከእስራኤል ጋር ለዓመታት ሰላም ሆነው ቆይተዋል። ከዚህ ቀደም በነበሩ ግጭቶች የአሸማጋይነት ሚናም ነበራቸው።

መረጃው፣ ከአልጀዚራ፣ ቢቢሲና ቲክቨሃ የተወሰደ ነው


Exit mobile version