Site icon ETHIO12.COM

አጫጭር ዜናዎች ለመረጃ

ትግራይ ክልል

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን ውይይት በመቀሌ ከተማ አካሄደ፡፡

በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በግጭት ምክንያት ለተጎዳው የሴቶችና ህፃናት መዋቅርን ለማጠናከር ለባለሙያዎችና የስራ ሂደት ኃላፊዎች ስልጠና መስጠት ተጀመረ።

አፋር ክልል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከልዑካን ቡድናቸው ጋር የልማት ሥራዎችን ለመገምገምና የበጋ ስንዴ ምርት ሥራን አፋር ክልል አሰጀምረዋል።

በአፋር ክልል በዱብቲ ወረዳ ኅብረተሰቡ በ8 ሺህ ሔክታር መሬት ላይ የበጋ ስንዴ ለማምረት ዝግጅት መድረጉ ተገልጿል፡፡

የአፋር ክልል ገቢዎች ቢሮ በጋቢ ረሱ ዞን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ በተገኙበት የሩብ ዓመት ግምገማ አካሂደዋል፡፡

አማራ ክልል

በአማራ ክልል አንጻራዊ ሰላም መምጣቱን ተከትሎ ተጥሎ በነበረው የሰዓት እላፊ ገደብ ላይ ማሻሻያ መደረጉን ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል፡፡

ደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት 9 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ተኪ ምርት ማምረቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

በጦርነቱ ጉዳት በደረሰባቸው ዞኖች ከተጀመሩ ትምህርት ቤቶች 23ቱ መጠናቀቃቸውን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

በአማራ ክልል በመኸር ወቅት ከታረሰው 83 ሺህ 334 ሄክታር መሬት አምስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ኩንታል የሩዝ ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

በአማራ ክልል ግማሽ ሚሊዮን አርሶ አደሮች በቡና ልማት እየተሳተፉ እንደኾነ ተገልጿል። በክልሉ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር በመሥኖ መልማት የሚችል መሬት እንደሚገኝም የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያሳያል።

በአማራ ክልል በ2015/16 የምርት ዘመን ከ75 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በጥጥ ሰብል መሸፈኑን ግብርና ቢሮ ገለጸ።

በተያዘው በጀት ዓመት በመስኖ ከ40 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማምረት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል።

ኦሮሚያ ክልል

በምርት ዘመኑ 464 ሺህ 821 ሄክታር መሬት ላይ የማሽላ ሰብል ለማልማት ታቅዶ ከእቅድ በላይ 639 ሺህ 105 ሄክታር መሬት መልማቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

በኦሮሚያ ክልል በ2016 በጀት ዓመት የመጀመርያ ሩብ ዓመት 27 ነጥብ 67 ቢሊዮን ብር የሚገመት የዜግነት አገልግሎት መከናወኑ የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ገለጸ።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሐረር ህይወት ፋና ሁሉን አቀፍ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የገነባውን የካንስር ሕክምና መስጫ ማዕከል በአርቲስት አሊ ቢራ ስም ሠይሟል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ኢሬቻ በሰላም ተከብሮ መጠናቁን አስመልክቶ በዓሉ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲከናወን ኃላፊነታቸውን ለተወጡ ሁሉም አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በምዕራብና በምስራቅ ወለጋ ዞኖች ህብረተሰቡና የጸጥታ ሃይሉ ተቀናጅተው በሰሩት ስራ በአካባቢው ሰላም ላይ ውጤት መገኘቱን የዞኖቹ የአስተዳደርና የጸጥታ ጽሕፈት ቤቶች አስታወቁ።

ከሦስት ዓመታት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት ‘ገበታ ለሀገር’ በሚል ስያሜ ከተጀመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል በኦሮሚያ ክልል፤ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ውስጥ የተጀመረው የወንጪ-ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት ተጠናቅቆ በዚህ ወር መጨረሻ ይመረቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ገለጹ፡፡

ሶማሌ ክልል

በጅግጅጋ ከተማ በ16 ሚሊየን 949 ሺህ 251 ብር የመካከለኛና የዝቅተኛ መስመር የመልሶ ግንባታ የማስፋፊያ ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

”ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ቃል በጅግጅጋ ማዕከል ሲሰጥ የነበረው የ2ኛ ዙር የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ስልጠና ማጠቃለያ መርሀ ግብር በስኬት ተጠናቀቀ

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሕገ-ወጥ የወርቅ አምራቾችና አዘዋዋሪዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ። አቶ አሻድሊ ሀሰን በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የወርቅ አምራች ማኅበራትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ርዕሰ-መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በአብራሞ ወረዳ በመኸር እርሻ የለማን የስንዴ ማሳ ጎብኝቷል፡፡

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል በማካሄድ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ የቤኒሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ፓርቲ (ቤህነን) ገለጸ፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ የሳታላይት ቴሌቪዥን መደበኛ ስርጭትን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በይፋ አስጀምረዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ በ7 ቋንቋዎች ጥራትና ታዓማንነት ያለው አስተማሪ፤ አዝናኝ እና አሳዋቂ መረጃዎችን በቴሌቪዥን እና በሬዲዮ ዘርፉ ለህብረተሰቡ ለማድረስ እየሠራ መሆኑንአስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከጀርመን ቀይ መስቀል ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሰረታዊና ሰብዓዊ ድጋፎች ማድረጉን አስታውቋል።

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልም ሆነ ከክልሉ ውጭ ያሉ አመራሮች ለአካባቢው እድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ጥሪ አቀረቡ፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአዲስ ምዕራፋ ፣አዲስ ተስፋ፣ ለአዲስ ክልል በሚል መሪ ቃል የተከናወነው ይፋዊ ምስረታ ማብሰርያና ማስተዋወቂያ መርሃ -ግብር በስኬት ተጠናቋል። በብልጽግና ፖርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ እንደገለጹት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ የማብሰሪያና ክልሉን የማስተዋወቂያ መርሐ ግብር በሰላም ተጀምሮ በሰላም መጠናቀቁን ተናግረዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የ2015 በጀት አመት አፈጻጸምና ቀጣይ ዕቅድ ላይ በሆሳዕና ከተማ ከስትሪንግ ኮሚቴ ጋር መክሯል። የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የኦዲት ስርዓትን በማጠናከር የሚሰበሰበው ገንዘብ ለታለመለት አላማ ማዋል እንደሚገባ ተገልጸዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ የማብሰሪያና ክልሉን የማስተዋወቂያ መርሐ ግብር ላይ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አጋርነታቸውን አሳይተዋል። በዚህም መሰረት የተለያዩ የገንዘብ ድጋፎች አድርገዋል።

በሆሳዕና ማዕከል ከእዳ ወደ ምንዳ በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሔደ ባለው 2ተኛ ዙር የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራር ስልጠና ተሳታፊዎች እንደገለጹት የተጣለብንን ሀገራዊ ሀላፊነት በብቃት ለመወጣት ተዘጋጅተናል ብለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ጤና ቢሮ በወቅታዊ የጤና ጉዳዮች ላይ በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ ከዞንና ልዩ ወረዳ አመራሮች ጋር መክሯል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ይፋዊ የምስረታ በዓል በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል በስነ ስርዓቱ ላይ የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድራን እና በርካታ እንግዶች ታድመዋል፡፡

ጋምቤላ ክልል

በጋምቤላ ክልል በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አንድ ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት እየተሠራ እንደሚገኝ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ገለጸ።

አክሽን አጌንስት ሀንገር “Action Against Hunger” የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በጋምቤላ ክልል በጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 8 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

በጋምቤላ ክልል የዘላቂ መሬት አያያዝ ፕሮግራም (RLLP-2) በላሬና በጂካዎ ወረዳዎች በ14 ንዑስ ተፋሰሶች ላይ ለመስራት ቦታዎች ተከልለው ካርታ እንዲዘጋጅላቸው መደረጉን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የአለም የእይታ ቀን “ፍቅር ለአይናችን በስራ ቦታችን” በሚል መሪ ቃል በጋምቤላ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።

ሀረሪ ክልል

በክልሉ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ። በአባድር ወረዳ ለጤና ጣቢያ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል። በክልሉ በሁሉም ወረዳዎች የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተያዘው ግብ ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ ነው።

በሐረሪ ክልል የሚታየውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ለማቃለል በ356 ሚሊዮን ብር ተጨማሪ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆኑን የክልሉ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት አስታወቀ።

የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በክልሉ በታይዋን የንግድ ማዕከል ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ፣ በዘንድሮ ዓመት በክልሉ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሐረሪዎች ስፖርት እና ባህል ፌስቲቫል እና የጁገል አለም አቀፍ ቅርስ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እንክብካቤና መልሶ ማልማት ላይ መክሯል።

ሲዳማ ክልል

ለተከታታይ 12ቀናት በሀዋሳ ማዕከል ከ’ዕዳ ወደ ምንዳ’ በሚል መሪ ሀሳብ ስካሄድ የከረመው ሀገራዊ የአመራር ሥልጠና ማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ጽ/ቤት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ተጽዕኖ ዙሪያ ውይይት አካሄደ።

116ኛየሲዳማ ክልል ከ68 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ ለማልማት የዝግጅት ሥራዎች እያከናወነ መሆኑን የክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።ውን ዓመት የመከላከያ ሰራዊት ቀን በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ በድምቀት ተከበረ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ከሲዳማ ክልል መልካም አስተዳደር ቅሬታ ሰሚ ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት ለክልሉ መንግስት ቅሬታ ሰሚ ባለሙያዎችና የዘርፉ ሃላፊዎች እንዲሁም ለባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከ11 ሺ በላይ ሄክታር መሬት በሩዝ ምርት መሸፈኑ ተገለጸ።

”ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሃሳብ በሚዛን አማን የስልጠና ማዕከል እየተሳተፉ የሚገኙት የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ለበጎ ዓላማ እና ለህክምና አገልግሎት የሚውል የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፀጋዬ ማሞ ከቤንች ሸኮ ዞን የጊዲ ቤንች ወረዳ ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሄደዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ የፍትህ ዘርፍ ተቋማት የ3 ዓመት ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ፍኖተ ካርታ እና የድርጊት መርሃ-ግብር ላይ ከመዋቅሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር በቦንጋ ከተማ አካሄደዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት 18ኛውን የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በድምቀት ለማክበር ከወዲሁ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ የስልጠና ማዕከል በሁለተኛ ዙር ለብልፅግና ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።

የዲላ ደንቦስኮ ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጅ ከ1ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የሥራ ማስጀመሪያ ማሽነሪዎችና ቁሳቁሶችን ለማህበራቱ ድጋፍ አድርጓል፡፡

በያዝነው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ላይ 142 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን በጌዴኦ ዞን የዲላ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከ8 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ለጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ድጋፍ አድርጓል።

“አጋርነት ለማህበረሰብ እድገት” በሚል መሪ ቃል 4ኛ ዙር የማህበረሰብ ምክክር መድረክ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል፡፡

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የጌዴኡፋ ቋንቋን በተለያዩ ቋንቋዎች ያለማንም አጋዥ በድምጽ ለመለማመድ የሚያስችል ኘላትፎርም ለተጠቃሚዎች ይፋ አድርጓል።

በገነት ኃ/ማርያም

ጥቅምት 18 ቀን 2016 ዓ.ም


Exit mobile version