Site icon ETHIO12.COM

የዲጂታል መለያና የዲጂታል ግብይት በኢትዮጵያ በስፋት ሳይዳረስ ከወዲሁ ጥርሱን እየሳየ ነው፤ የኢትዮጵያን ማንነት የገዙ ተጨንቀዋል

37 የንግድ ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወሰደ

የዲጂታል ግብይትና የመታወቂያ ስርዓት በኢትዮፕያ ለማስፈን መንግስት ቁርጠኛ አቋም መያዙን ተከትሎ አገልግሎቶቹ ብዙም ስራ ላይ ሳይውሉ ገና ከጅምሩ ጥርሳቸው የሰላ መሆኑን በሌብነት ለተሰማሩ እያሳያቸው ነው። ህዝብ ንቁ ድጋፍ ካከለበት ብዙ ወንጀሎች በኢትዮጵያ ” ደህና ሰንብቱ” ይባላሉ።

በኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ሙሉ በሙሉ ተጋራዊ ሲሆን ኢኮኖሚው ወዲያውኑ እስከ ሰባት ከመቶ እንደሚያድግ መንግስት ያስታወቀው ባደጉት አገሮች እንደሚደረገው የንግድ ስርዓቱ ላይ እዛና እዚህ በጨበጣ ማንነት እየተቀሸበ የሚሰራው ወንጀል ስለሚመክን ነው። በዚህም አገሪቱ በቀረጥ ገቢ የምታጣው ከፍተኛ መተን ያለው ሃብት ይድናል።

በቅርቡ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል ስርዓት እንዲሆን ሲደረግ በአገር አቀፍ ደረጃ በገፊና ጎታች ትስስር አሰራሩ ተግባራዊ እንዳይሆን ያኮረፉ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች፣ የነዳጅ ቀጂዎች ማህበር የሚባለው አካል ባገኘው ሚዲያዎች ተባብረው ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩበት ምክንያት አሁን ይፋ መሆኑን ለአብነት በማንሳት አሰራሩ ከወዲሁ ጥርሱን እያሳየ መሆኑን አመልክተዋል።

በዚሁ የዲጂታል ግብይት ወጥመድ የተያዙትን ከነቅጣታቸው ይፋ ያደረው የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን መንግስት የተሰጣቸውን ወይም የገባላቸውን ነዳጅ በወጉ ባልሸጡ ላይ መረጃ ማሰባሰቡንና የቁጥትር ስልቱ ራስን በራስ የማሰር እንደሆነ አመልካች ነው ተብሏል። ነዳጅን ከግብይት ስርዓት ውጭ በተገበያዩ ማደያዎች ላይ ዕገዳ መጣሉን የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ሲያስታውቅ በሙሉ ዝርዝር ሳይሆን በግርድፍ ሲሆን በቅርቡ ከከፍተኛ ቅጣትና ማዕቀብ ጋር ይፋ የሚሆን መረጃ እየተዘጋጀ እንደሆነም ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ አመልክተዋል። በሁለተኛው ዙር ቅጣት ርህራሄ እንደማይኖርም ተመልክቷል።

ከዲጂታል ነዳጅ ግብይት ስርዓት ውጪ ነዳጅን በመሸጣቸውና በስማቸው ከተጫነላቸው ነዳጅ በላይ በማደያቸው በሸጡ በአዲስ አበባና እና ሸገር ከተሞች በሚገኙ 97 ማደያዎች ላይ የአንድ ወር እገዳ እና የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ የዲጂታል ግብይት ቁጥጥሩን ያጠበቀ ለመሆኑ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል። ከዚህ ውስጥም 40 የነዳጅ ማደያዎች ላይ የአንድ ወር የነዳጅ ጭነት ዕገዳ የተጣለ ሲሆን፥ 57 ነዳጅ ማደያዎች ደግሞ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ዕገዳ የተጣለባቸው ማደያዎች ለባለስልጣኑ ከመስከረም10 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም ባለው ጊዜ በደረሰው ሪፖርት መሠረት በስማቸው ከተጫነላቸው ነዳጅ በላይ መሸጣቸው ተጠቁሟል፡፡ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ደግሞ ከተጫነላቸው ነዳጅ ከ50 እስከ 80 በመቶ የሚሆነውን ነዳጅ ብቻ በዲጂታል ግብይት መፈጸማቸው ተጠቅሷል፡፡

የነዳጅ ሕገ-ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር የሚያስችል ዲጂታል የነዳጅ ግብይት ሥርዓት ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባና እና ሸገር ከተሞች ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የዲጂታል መታወቂያ ለመውሰድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን መመዝገባቸው የሚታወቅ ነው። ይህን ተከትሎም ስራው ከተጀመረ በሁዋላ እየወጡ ባሉ መረጃዎች መንግስት ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ ፓስፖርትን ጨምሮ ኢትዮጵያዊ ማንነት የታደላቸውን የውጭ ዜጎች ዝርዝር እንደሚሰበስብ ታውቋል። በስደተኛነት ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው በሁለት ማንነት የሚንቀሳቀሱትን መለየት የሚያስችለውን ስራ ለመስራት ከሚመለከተው የዓለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም ጋር የጋዊነት ስምምነት ውል አስሯል።

ከዓለም የስደተኞች ድርጅት ከናሽናል አይዲ ፕሮግራም ጋር በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችን ወይም በድርጅቱ ስር ያሉ የውጭ ዜጎችን ለመመዝገብ ስምምነት መድረሱ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ዜናው የገባቸው መረጃውን ” የወሩ ታላቅ ዜና” ብለውታል።

በቅርቡ በኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፓስፖርትን በገንዘብ ወይም በሌብነት ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ማደላቸው በመረጃ የተደረሰባቸው ተጠርጣሪዎች የኢትዮጵያዊ ማንነት ማረጋገጫ ፓስፖርት የሰጡት በአብዛኛው ለውጭ ዜጎች ነው። መንግስት ባደረገው ክትትልና በአርተፊሻል ኤጀንሲ በኩል በተሰበሰበ ዳታ ኢትዮጵያዊ ፓስፖርት የታደላቸው አካላት ተለይተዋል። ጉዳዩን የሚያውቁ እንዳሉት ከዓለም አቀፉ የሰደተኞች ድርጅት ጋር በተገባው ውል መሰረት ስደተኞቹ ሙሉ በሙሉ ወደ መረጃ ቋቱ ማንነታቸው ሲካተት የያዙት በብር የተሸመተ የኢትዮጵያ ፓስፖርት እጃቸው ላይ እንዳለ ይመክናል። ሊጠቀሙበት ከፍለጉ ሲስተሙ በየበሩ ጥርስ ሆኖ ይይዛቸዋል። ስለሆነም ይህ ተግባራዊ ሲሆን በሃሰተኛ ሰነዶቹ ለመጓጓዝም ሆነ ያልተፈቀደ ተግባር ህጋዊ መስሎ ለመፈጸም ቢሞከር ትርፉ ተጨማሪ ቅጣትን በጎናጸፍ ብቻ እንደሆነ አመልክተዋል።

በሶስት ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያ ዜጎቿንም ሆኑ በስደት የሚኖሩትን በገቡበትና በወጡበት ቦታ ሁሉ ማንነታቸውን መሰወር ባማይችሉበት ደረጃ በመረጃ ቋቷ ውስጥ እንደምታስገባ ተመልክቷል። ይህ እንቅስቃሴ ስጋት ያሳደረባቸው ዓለም ሁሉ መዘመን ሲጀምር ድሮ የጀመረውንና እየሰራ የሚገኝበትን ሲስተም እየተቃወሙ ነው። ከምንም በላይ በውጭ አገር በዚሁ ስርዓት ውስጥ ግብር፣ ቀረጥ፣ ግዢና ሽያጭ፣ እንዲሁም አገልግሎት እየሰጡና እየተቀበሉ የሚኖሩ ኢትዮጵያ ይህን ለምን ተግባራዊ ታደርጋለች በሚል የሚያካሂዱት ዘመቻ ለበርካቶች እጅ በአናት የሚያስጭን ሆኗል።

” መንግስት ዲክታተር ሊሆን ስላሰበ ሁሉን ለምቆላለፍ ሲል ነው ይህን የሚያደርገው” በሚል የአክቲቪስትነት ካባ የተደረበላቸው ዕለት ዕለት ሲተቹ የሚያደምጡ ” አናሎግና ዲጂታል ለተቀላቀለባቸው የሚገባቸው አንዳችም በጎ ነገር የለም” ሲሉ ይተቻሉ።

በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታትም 70 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የመመዝገብ እቅድ እንደተያዘም ብሔራዊ የመታወቂያ ፕሮግራም የኮሙኑኬሽን ኃላፊ አቶ አቤኔዘር ፈለቀ  መናገራቸው ይታወሳል። አሁን ላይ ግን በሶስት ዓመት ድፍን አገሪቱን ለማዳረስ እየተሰራ ነው።

በሌላ ተመሳሳይ ዜና የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት ህግን ተከትለው ባልሰሩ 37 የንግድ ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

እርምጃ የተወሰደባቸው ንግድ ድርጅቶች ከተሰጣቸው የንግድ ፈቃድ መስኮችና ዓላማ ውጪ የሰሩ፣ ባልታደሰ ንግድ ፊቃድ ሲነግዱ የተገኙ፣ ባስመዘገቡት የስራ አድራሻ ያልተገኙና የቅርንጫፍ አድራሻ ያላስመዘገቡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በበጀት ዓመቱ መጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት 402 የንግድ ድርጅቶች ላይ በተደረገው የክትትልና የቁጥጥር ስራ 365 ንግድ ድርጅቶች በህግ አግባብ የሚሰሩና 37 ንግድ ድርጅቶች ደግሞ ህግን ተከትለው የማይሰሩ መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡


Exit mobile version