ETHIO12.COM

በፀጋ በላቸው ላይ አስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመው ኮንስታብል የኋላመብራት በ16 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

በፀጋ በላቸው ላይ የጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰው ኮንስታብል የኋላመብራት ወልደማርያም በ16 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

የህግ አማካሪና ጠበቃ እንዲሁም በፆታዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩት አበባየሁ ጌታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ውሳኔው የከተማውን ገፅታ የሚያበላሽ እንደሆነ ስለታሰበ ነው መፍትሄ ያገኘው ብለዋል።

–  ሚዲያ ላይ ባለመውጣታቸው ብዙ ተሸፋፍነው የቀሩ የጠለፋ ወንጀሎች በከተማው አሉ።

–  ይህ ውጤት የተገኘው በተለያዩ መንገዶች በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ከፍተኛ ትኩረት ስላገኘ ነው።

–  ጉዳዩ አነጋጋሪ የሆነው የከንቲባው የግል ጠባቂ ከመሆኑ፣ የመንግስትን ንብረት ተጠቅሞ በመሆኑ በከተማው ገፅታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ስለነበረው ነው ይህ ጉዳይ እልባት ያገኘው።

–  ታህሳስ 04 ቀን 2016 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተጠርጣሪው በተከሰሰባቸው ሁለት ወንጀሎች ማለትም በጠለፋ እና አስገድዶ መድፈር ጥፋተኛ ተብሏል።

–  በዛሬው እለት ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በ16 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ተሰጥቷል። ሲሉ የህግ አማካሪው ለቲክቫህ ተናግረዋል።

ባለሙያው በአጠቃላይ ፆታዊ ጥቃቶችን በተመለከተ ምን አሉ ?

የዳሸን ባንክ ሰራተኛ እንዲሁም የአላሙራ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆነችው ፀጋ በላቸው ፤ ግንቦት 15 ቀን 2015 ከስራ ስትወጣ በወቅቱ የከተማው ከንቲባ የግል ጠባቂ በነበረው ኮንስታብል የኃላመብራት ወ/ማርያም የተባለ ግለሰብ በመኪና ታግታ መወሰዷና አድራሻዋም ሳይታወቅ ለቀናት መቆየቱ የሚታወስ ነው።

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በወቅቱ እንዳስታወቀው ተጠርጣሪው ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ከፀጥታ ሀይል ለማምለጥ ሲል በሻፋሞ ጫካ ለጫካ ሲዘዋወር እንደነበረ እና ተጠርጣሪው ግለሰብ ወንጀሉን ለመፈጸም ሲጠቀምባቸው ከነበሩ አንድ ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያና ሽጉጥ ጋር  ህዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም. መያዙን የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታውቆ ነበር።

መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በአዲስ አበባ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

Exit mobile version