ETHIO12.COM

ፑንት ላንድ ለኢትዮጵያ ወደብ በነጻ አለች፤ የሶማሊ ላንድና አሜሪካ የጦር ሰፈር ስምምነት ያደርጋሉ

ከሶማሊያ ራሷን ለይታ በራስ ገዝነት የምትተዳደረዋ ፑንትላንድ “ኢትዮጵያ የባህር ዳርቻዎቼን አልምታ መጠቀም ትችላለች እኛ በየትኛውም ኢትዮጵያ ወጪ ገቢ ላይ ምንም አይነት ቀረጥ አንጥልም” ስትል በባለስልጣኗ አማካይነት መናገሯ ጫጫታ አስነሳ። የሶማሌላንድ መሪ ወደ አረብ ኢምሬትስና አሜሪካ አቅንተው ከፍተኛ የተባለ የጦር ሰፈር ግንባታ ውል እንደሚፈራረሙ ታውቋል።

ፑንትላንድ በምታሳያቸው እንቅስቃሴ ክፉኛ ያናደዳቸው የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ለፑንትላንድ መንግስት የማስጠንቀቂያ መልዕክት ልከዋል። የሶማሌ ላንድንና የፑንት ላንድን አካቶ ይቅርና መቀመቻቸውን ያለ ድጋፍ ማስተዳደር ያልቻሉት ሀሰብ ሼክ ኢትዪጵያን ጨምሮ ዛቻ ሲያሰሙ በርካቶችን እያስገርመ ነው። የፑንትላንድ ፕሬዝደንት ቀጣይ ሳምንት በሚያከብሩት በዓላሲመት ላይ እንዲገኙ ጠ/ሚ አብይ መጋበዛቸው ይታወቃል።

ሀሰን ሼክ “ሉዓላዊነታቸን ተነካ” በሚል ዛቻ ማሰማት ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ ኢትዮጵያ ተመጣጣኝ መልስ ከመመልስ ተቆጥባ ብትቆይም ትዕግስቷ ምክንያት አዘል መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች እየወጡ ነው።

” ጉዳዩን ሊያውቁ የሚገባቸው ሁሉ አስቀድሞ እንዲያውቁት ተደርጓል” ሲሉ አቶ ሬድዋን ለተናገሩት ምላሽ ከሚሆኑ በርካታ መረጃዎች ውስጥ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት አረብ ኢምሬትስን ጎብኝተው “ስትራቴጂክ” ለተባለ ስምምነት አሜሪካ የማቅናታቸው ዜና ግንባር ቀደም ነው።

በሰበር ዜና የስማሌ ላንድ መንግስት ሚዲያዎች እንዳስታወቁት ፕሬዚዳንት ሙሳ አሜሪካ የሚሄዱት አሜሪካ በበርበራ ወደብ ለምትገነባው ወታደራዊ የጦር ሰፈር ስምምነት ለመፈጸም ነው።

አረብ ኤምሬትስ “ከኢትዮጵያ ጋር የጀመርኩትን ስራ የሚያስቆም አንዳችም ሃይል የለም” ማለቷን ተከትሎ የወጣው ይህ ዜና፣ አሜሪካ “ለኔ ሲሆን ይቻላል፣ ለኢትዮጵያ ሲሆን አይቻልም” የሚል የሚጋጭ ፖለቲካ እንደማትከተል ማረጋገጫ እንደሆነ ተመልክቷል።

ኢትዮጵያና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ሰነዱን ከተፈራረሙ በሁዋላ ያነጋገርናቸው ምሁር ” አሜሪካ ጉዳዩ ተቀብላዋች። እየተጫወተች ያለችው የፖለቲካ ጨዋታ ነው” ማለታቸው አይዘነጋም።



Exit mobile version