ETHIO12.COM

በምስራቅ ኢትዮጵያን የመቆለፍ ስልት – ዝርዝር ሰነድ

“ሚስጢራዊ ማስታወሻ” በሚል ተሰንዶ ለሶማሊያ መንግስት የቀረበው የስትራቴጂክ ሰነድ የተዘጋጀው ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ ያደረጉትን የባህር በር የሃምሳ ዓመታት የሊዝ ስምምነት ለማጨናገፍ በሚል ነው። አዘጋጁ ነዋሪነታቸው በኖርዌይ የሆነ የሶማሌያ ተወላጅ ዶክተር ናቸው።

ይህ ሶማሊያ በኢትዮጵያ ላይ እንድትከተለው ታስቦ የቀረበው በወታደራዊ፣ በዲፕሎማሲ እና ፈርጀ ብዙ ስልቶች ስትራቴጂ የታጨቀበት ሰነድ ይፋ መሆኑን ተከትሎ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።

“ሚስጥራዊ ማስታወሻ” የተባለው ሰፊ ሴራ የተላከው በዋናነት ለሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ነው። “A confidential Memorandum To: HE. Hassan Sheikh Mohamoud President of the Somali Federal Republic”

ሰነዱ የተላከው ራሱ አዘጋጁ “ከሙክታር አይናሼ የሶማሊያ መንግሰት የፀጥታ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝና አማካሪ የሶማሊያ ዜጋ” ሲል ገልጿል። በየደረጃው ግልባጭም ተደርጓል።
ግልባጭ የተደረገላቸው ሃምዛ ባሬ፣ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ አብዲ ሃሺ አብዱላሂ፣ የላዕላይ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፣ አደም መሀመድ ኑር ማዶቤ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ፤ እና ለሁሉም የፌዴራል አባል ክልሎች ፕሬዚዳንቶች መሆናቸው “ሚስጥራዊ ማስታወሻ” በተባለው ሰነድ ተመልክቷል። ቀኑም ጃንዋሪ 22/ 2024 ነው።

“ጉዳዩ” ሲል ሚስጢራዊው መረጃ ለማስታወሻው የሰጠው ርዕስ “የአደጋ ጊዜ ብሄራዊ መከላከያና የቀውስ አመራር ስትራቴጂ” Subject: EMERGENCY NATIONAL DEFENCE AND CRISIS MANAGEMENT STRATEGIES የሚል ነው።

  1. የኢትዮጵያ የወራሪነት ተፈጥሮ፣ የስጋት ግምገማ ማድረግ፡ የኢትዮጵያን አይቀሬ ወረራ በተመለከተ ገፅታዎቹን፣ መጠነ ስፋቱን፣ አቅሙን፣ እና ምንጩን መረዳት የሚያስችል አስቸኳይ የደህንነት መረጃ በመሰብሰብ ትንተና መስራት፤ እንዲሁም የኢትዮጵያን እና የወረራ አጋሮች ማንነት፣ አቅምና አላማ የተመለከቱ መረጃዎችም አሰባስቦ ግምገማ ማካሄድ። በሚል ጀምሮ ዝርዝር የሚያስቀምጠው ምክረ ሃሳብ
  2. – የብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤትን ሥራ ላይ ማዋል፡-
  1. አገራዊ የአስቸኳይ ጊዜ ማወጅ፡

-አገሪቷን ወደ ብሔራዊ የመከላከያ ዕዝ እንድትሸጋገር፣ የተቀላጠፈ የሀብት ማሰባሰብ ስራን በማረጋገጥና የኢትዮጵያውያን ያልተቀየረ የወረራ ስጋት እስክናሸንፍ ድረስ የሶማሊያ መንግስት በመከላከያ ተግባራት ላይ ብቻ ያተኩር ዘንድ ብሄራዊ የአደጋ ጊዜ ህግን ተግባራዊ ማድረግ። እንደሚገባ ሰነዱ ያስረዳል።

  1. ብሔራዊ የቀውስ አስተዳደር ቡድን፡ ከፌዴራል እና ከክልል በመጡ ከፍተኛ የፖለቲካ ሰዎች የሚመራ፣ ፈጣን ውሳኔ አሰጣጥ እና ከፕሬዝዳንቱ እና ከብሔራዊ የጸጥታው ምክር ቤት ጋር ውጤታማ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ብሔራዊ የቀውስ አስተዳደር ቡድን መፍጠር።  የቡድኑ ዋና አላማ በሶማሌዎች መካከል የፖለቲካ ትስስር መፍጠር እና የሃብት ማሰባሰብ ጥረቶችን ማስተባበር ሲሆን በተለይም ወታደራዊ ባልሆኑም የሀገር መከላከያ ዘመቻዎች ላይ ጭምር አፅንዖት በመስጠት..
  2. የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ማሰማራት፡-
    የወታደራዊ፣ የፖሊስ፣ የመረጃ እና ማካዊስሊ ሚሊሻ ሃይሎችን ያካተተ የተሟላ የሀገር መከላከያ መሠረተ ልማቶችን ማንቃት እና ማሰባሰብ እና ለመጪው ጊዜ ምላሽ ለመስጠት ለፈጣን እና ለአፋጣኝ ዝግጁነት ከፍ ያለ ሁኔታን ማስጀመር።
  3. ስትራተጂካዊ ግንኙነት መዘርጋት፡
    ስለሁኔታው እና ስለተወሰዱ እርምጃዎች በየጊዜው ወቅታዊ መረጃዎችን በመስጠት ከህዝቡ ጋር ግልጽ ግንኙነት እንዲኖር ማድረግ።  የሶማሌ ህዝብን ለመከፋፈል የታለመውን ኢትዮጵያዊ ፕሮፓጋንዳ ለመመከት፣ የሀገር መከላከያ እርምጃዎችን ቀጣይነት ያለው ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያሉትን ሁሉንም የሚዲያ ጣቢያዎች ይጠቀሙ።

▪️የብሔራዊ መከላከያ ኃይሎችን ማንቀሳቀስ

  1. የሶማሌ ብሄራዊ ጦር ሰራዊትን ዘይላ አካባቢ ማሰማራት፡
    የመከላከያ አቅሙን ለማጠናከር እና ኢትዮጵያ በአገራችን ላይ ለሚሰነዘረው አይቀሬ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ቢያንስ የሶማሌ ብሄራዊ ጦር ሰራዊትን SNA ወደ ዘይላ እና አካባቢው ማሰማራት።
  2. የፑንትላንድ የጸጥታ ኃይሎችን በፌዴራል ዕዝ ስር ማድረግ፡-
    የፑንትየንድ የጸጥታ ኃይሎችን በከፊል ስልታዊ በሆነ መንገድ አስቀምጦ በሶማሊላንድ ሳይላክ በሚገኘው የ SNA ኃይሎች ላይ ሊሰነዘር የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው።
  3. በሶማሌላንድ ላይ በርካታ ወታደራዊ ግንባሮችን መክፈት፡
    የሶማሌላንድን የውጊያ አቅም ላይ የሚያነጣጥሩ ሶስት ስትራቴጂክ ወታደራዊ ግንባሮች።
      በተለይም በሶማሊላንድ ምስራቃዊ እና ምዕራባዊ አቅጣጫ ግንባሮችን በመፍጠር የሶማሊላንድን ወታደራዊ አቅም ማዳአም፣ ይህም የሶማሊያን አጠቃላይ ወታደራዊ ውጤታማነት ያሳድጋል።
  4. በሶማሊላንድ የምእራብ አቅጣጫ ሶማሌላንድ የማካዊስሊ Macawisley ኃይሎችን ማሰባሰብና ማስታጠቅ። በምእራብ ሶማሌላንድ የሚገኙትን የማዋዊስሊ ሃይሎች በማሰባሰብና በማስታጠቅ፣ በእነዚያ ክልሎች ባሉ የሶማሌ ማህበረሰቦች ዘንድ የሚገኙ  የፖለቲካ ቅሬታዎችንና ስሜቶችን ለሶማሊያ አጠቃላይ ወታደራዊ ዘመቻ ስኬታማነት ድጋፍ የማሰባሰብን አስፈላጊነት በመገንዘብ ለዚሁ ዓላማ እንዲጠቅሙን ማድረግ።
  5. ስትራተጂያዊ ወታደራዊ ጥምረቶችን መፍጠር፡-

እንደ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታንያ ካሉ ወዳጅ አገሮች ጋር ሊደረጉ የሚችሉ ወታደራዊ ጥምረቶችን ወይም የደህንነት አጋርነቶችን መመርመር። እንዲሁም ቱሪክ፣ ግብጽ፣ ሳውዲ አረቢያ እና ኳታር በተመሳሳይ።
ኢትዮጵያን ለመግታት እና (የሶማሊያን) መከላከያ ሰራዊት አቅም ለማጠናከር ከሌሎችም ጋር ትብብርን ማማተር።

  1. ወጣቶች የሶማሊያ  መከላከያ ሰራዊትን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ማድረግ፡-
       አገር ወዳድ ሶማሊያዊያን ለሀገር መከላከያው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማነሳሳትና የኢትዮጵያን የወረራ ስጋት ለማስገንዘብ ሰፊ ዘመቻ በማካሄድ የሶማሊያን የአርበኝነት ስሜት እንዲቀሰቀስ ማድረግ።

መላውን (በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኝ) ሶማሌዎችነ ለአንድ አላማ ማሰባሰብ

  1. ህዝባዊ ግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎች፡
    በሶማሊያ ብሄራዊ ደህንነት፣ ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት ላይ ያለውን አደጋ በማሳየት በሁሉም ዘርፍ በሚገኙ የሚዲያ ቻናሎች በኩል ለህብረተሰቡ ጥልቅ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ዘመቻዎች ማካሄድ፣ ይህም የጋራ ሀገራዊ ርምጃ አስፈላጊ ስለመሆኑ አጽንኦት የሚሰጥ ይሆናል።
    መረጃን በብቃት ለማሰራጨት ማህበራዊ ሚዲያዎችን፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥንና የማህበረሰብ መድረኮችን መጠቀም።
  2. የሶማሌ ሲቪል ማኅበራትን ለአላው እንዲቆሙ ማድረግ፡-
    የሶማሌ ሲቪል ማኅበራት ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ሊሰነዘርባት ከሚችለው ወረራ ለመከላከል ሊወስዱት በሚችሉት ወሳኝ ሚና ዙሪያ ማብራሪያ ለመስጠት በሁሉም የአገሪቱ ከተሞች በሚገኙ አዳራሾች የማህበረሰብ ስብሰባዎች ማካሄድ።  የሲቪል ማኅበራት የሚያበረክቱትን ልዩ አስተዋጾ ለማጉላት ግልጽ ውይይቶችን ማጠናከር፣ ቨተለይም የአገሪቱን የውጭ ሥጋቶች የመቋቋም አቅም ለማጠናከር ድርጅቶቹ የሚኖራቸውን ፋይዳ በማጉላት መወያየት።
  3. የስደተኞች መብት፡
    በሶማሌ ግዛቶች የሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች በተመለከተ አለም አቀፍ ህጎችን ማክበር። 
  4. የሶማሌ የንግድ ማህበረሰብን ማሰባሰብ፡

ዋናውን ጉዳይ በማጉላት በሶማሊያ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር ለንግዱ ማህበረሰብ ጥሪ ማቅረብ።

▪️የጋራ መስዋዕትነት አስፈላጊነት

  1. ከሶማሌ ዲያስፖራዎች ጋር መገናኘት፤ በተቻለ ፍጥነትም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲያስፖራ ንቅናቄ ማእከል መፍጠር።

IV.  ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ

  1. አፋጣኝ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን መመስረት፡-

ከዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ከተፅዕኖ ፈጣሪ የዓለም ኃያላን መንግሥታት ጋር ለመነጋገር አፋጣኝ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ማድረግ፤ የሶማሊያን የግዛት አንድነት የሚጥስ የኢትዮጵያን ተንኮል-አዘል ጥቃት በማስገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰብ፤ ግንዛቤም ማስጨበጥ።

  1. የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአስቸኳይ መሾም፡
    ጥሩ ብቃትና አቆም ያለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሾም በዚህ ሀገራዊ ቀውስ ውስጥ የሶማሊያን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ውጤታማ ለማድረግ ይጠቅማል።
  2. ከኢትዮጵያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማቋረጥ፡
    አምባሳደሩን በፍጥነት በማባረር እና ሞቃዲሾ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአስቸኳይ እንዲዘጋ በማድረግ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጥ።
  3. የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ENDF እንዲወገዱ ትዕዛዝ ማስተላለፍ፡-

ማንኛውም የ ATMIS የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ከሶማሊያ ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ ትእዛዝ መስጠት።

  1. ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረግ የትኛውንም የድርድር ጥሪ ውድቅ ማድረግ፡-
    የአፍሪካ ህብረት ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ለመነጋገር ያለውን የማይረባ ሃሳብ ፈፅሞ መተው፤ አፍሪካ ኅብረት ኢትዮጵያ በሶማሊያ ላይ የምትፈጽመው የጥቃት ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆም በግልጽ መጠየቅ አለበት። ሚስተር ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ የሶማሊያን ምድር እንዳይረግጡ መታገድ አለባቸው።
  2. አለም አቀፍ የመንግስታት መድረኮችን መጠቀም፡
    የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ)ን ጨምሮ ቁልፍ በሆኑ የባለብዙ ወገን መድረኮች ድጋፍ እንዲደረግልን በንቃት በመከታተል ኢትዮጵያ በህዝባችን ላይ የምትፈፅመውን ያልተጠበቀ ጥቃትና የጸጥታ ስጋት ማጉላት።
  3. ከኢጋድ አባልነት መውጣት፡-
    ኢትዮጵያ በሶማሊያ በኢጋድ ማዕቀፍ ውስጥ መግባቷ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ስትራቴጂካዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ምኞቷን ማሳያ ነው።  በሶማሊያ ያለው ቀውስና የፖለቲካ አለመረጋጋት የኢትዮጵያን የብሔራዊ ደህንነትና የቀጣናዊ ተፅእኖ ግቦች ለማሳካት ነው የሚሰራው።  ኢትዮጵያ በሶማሊያ የፖለቲካ ልሂቃን ውስጥ ጎጂ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ተግባር በመፈፀም የህዝባችንን የፖለቲካ አንድነት ለመናድ ላለፉት ሶስት አስርት አመታት ውስጥ በቋሚነት ሰርታለች።
  4. Global Media Advocacy፡
    በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር እና በአፍሪካ ህብረት መርሆዎች የተጠበቁትን የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ጥሰት በማሳየት የኢትዮጵያን ወረራ ለማጉላት ከአለም አቀፍ ሚዲያዎች ጋር በጋራ መስራት። እንዲሁም የኢትዮጵያን ያልተቋረጠ ጥቃትና የመስፋፋት ስትራቴጂክ ጥረቶችን በመቃወም አለም አቀፍ የሆነ ህዝባዊ አቋም እንዲጎለብት መትጋት። ይህ ለአለም አቀፍ ግንኙነትና ፖለቲካ ባለሙያዎች ጥሪ ማድረግን የሚያካትት ነው።
  5. ዓለም አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ፡
    ለሀገራችን ለሶማሊያ ዓለም አቀፍ ርኅራኄ እና ድጋፍ ለማስገኘት የኢትዮጵያ ጥቃት ሊያስከትል የሚችለውን አለመረጋጋት በተከታታይ በመግለጽ፣ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የግጭቱን ታሪካዊ ሁኔታ ለማሳወቅ ጠንካራ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዘመቻዎች ማካሄድ፣
  6. አለምአቀፍ ህግጋትን መጠቀም፡-
    ከአለም አቀፍ የህግ አካላት ጋር በመተባበር፣ በወራሪዋ/ኢትዮጵያ ላይ ክስ በማቅረብ እና ለቅጣት ወይም ሌሎች እርምጃዎችን በመፈተሽ በአለም አቀፍ ደረጃ የህግ ድጋፎችን ማፈላለግ

V. ኢትዮጵያ ላይ ኢኮኖሚ አድማዎችና ማዕቀቦች መጣል፡-

  1. የኢኮኖሚ ቦይኮት፡
    ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የንግድና የንግድ ግንኙነት በስትራቴጂክ መለኪያዎች መሰረት ማቋረጥ።  በተለይም ወደ ሶማሊያ የሚገባውን የኢትዮጵያ ጫት እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎች በማገድ የኢኮኖሚ ጫና መፍጠር።
  2. የአየር ትራፊክ ገደቦችን መጣል፡
    የሶማሊያን አየር ክልል ሙሉ በሙሉ ለኢትዮጵያ አቪዬሽን በረራዎች ዝግ ማድረግ፣ (የሲቪልም ሆነ ወታደራዊ በረራዎችን)።
    በ ATMIS ተልዕኮ ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገልግሎት ለመስጠት የተፈቀደላቸው በረራዎችን ብቻ መፍቀድ።  .
  3. በሶማሌላንድ ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ መጣል፡

የፋይናንስ ስርዓቶችን ኢላማ ያደረጉ የቅጣት ርምጃዎችን ይፋ ማድረግ፣ የሶማሊያን ቴሌኮሙኒኬሽን (የሀገረ ሶማሊያ ኮድ 252 እንዳትጠቀም ማቋረጥ፣ (በዚህም የአለም አቀፍ ጥሪዎችን እና የኤሌክትሮኒክስ ግብይቶችን ማስቆም)፣ የአየር ጉዞ፣ የዲፕሎማሲያዊ ኮንትራቶችና የአየር ክልል ገደቦች መጣል። እንደ ምግብ እና መድሃኒት ያሉ የሰብአዊ እርዳታዎችን ብቻ መፍቀድ።

SOOMAALIYA HA NOOLAATO (ሶማሊያ ለዘላለም ትኑር)

ሙክታር አይናሼ

Mobile +47 901 25 961
Email: mainashe@gmail.com

ሰነዱን ያገኘነው ከእስሌማን የአባይ ልጅ ሲሎን መጠነኛ ኤዲት አድርገናል

ይህ መረጃ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ከመንግስት ወገን ምንም የተባለ ነገር የለም። ለአስተያየትም የበቃ ተደርጎ የተወሰደም አይመስልም። ከሃያ ሺህ በላይ ወታደሮች በሶማልያ ያላት ኢትዮጵያ ወታደሮችን ስለማስወጣትም ሆነ፣ የሰላም ማስከበር ተግባሯን አስመልክቶ አጠናክራ እንደምታስቀጥል ከመግለጽ ውጭ ያለችው ነገር የለም።

Exit mobile version