Site icon ETHIO12.COM

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ራሱን አጠፋ ወይስ ሰው ገደለው?

#(መላኩ ብርሃኑ ) | ቀኑን ሙሉ ሲያወሩ ቢውሉ መስማት የማይሰለቹኝ አራት ሰዎች አሉ።ስብሃት ገብረእግዚአብሄር፣ ዘነበ ወላ ፣ አብዱ አሊሄጂራ እና ገነነ መኩሪያ።

ገነነ ከወሬው በላይ የሚያውቀው ነገር መብዛቱ ነው የሚደንቀኝ።እነዚያን በደቃቃ ፎንቶች ሊብሮ ላይ ይጽፋቸው የነበሩ መሶብ የሚሞሉ የኳስ ወሬዎችን ነፍሱን ይማረውና ታናሽ ወንድሜ በተመስጦ ሲያነባቸው ነበር የማያቸው።ኳስ አፍቃሪ ስላልሆንኩ የኳሱን ገነነን ብዙም ሳላነበውና ሳልሰማው ነው የኖርኩት።በኋላ ግን ገነነ መስማት በምወደው የድሮ ታሪኮች መጣ። ተከታታዩ ነበርኩ።

ከገነነ የሚገርመኝ ነገር…አወራሩ ነው! He was so engaging ካሜራ ፊት ሆኖ ሲናገር ፊቴ ቆሞ የሚያወራኝ ያህል ነበር ቀልቤን የሚይዘው። ቀንና ሰዓት ስምና ቦታ ሳይረሳ ሲናገር ይደንቀኝ ነበር። የትናንቱን ማስታወስ ለሚቸግረኝ እኔ ገነነ የረጅም ዘመን ታሪክን ሳያዛንፍ ወደኋላ ተመልሶ ሲያወራ ትንግርቴ ነው።

የሆነው ሆኖ ገነነ አሁን የለም።አፈሩ ይቅለለው። አሟሟቱ ግን በጣም እንቆቅልሽ ሆኖብኛል። በተለይ በቴዲ ተክለአረጋይ ጽሁፍ መነሻነት ኢትዮፒካል ሊንክ ላይ ከሰማሁት መረጃ ተነስቼ ፣ (ጥቂትም ቢሆን) የፖሊስ ወንጀል ምርመራ ሳይንስ እንደተማረ ሰው ሆኜ መረጃውን ሳብላላው ያልተመለሱልኝ ዋና ዋና ጥያቄዎች አንጎሌ ውስጥ ተጉላልተውብኛል።

ከዚያ በፊት ግን እከሌ አስነጠሰው ተብሎ ወሬ በሚሆንበት በዚህ ዘመን ገነነን ያህል ታላቅ ሰው መታመሙና እግሩ መቆረጡ ሲነገር አለመስማቴ (ሌሎች ሰምተው እንደሁ እንጃ እንጂ) ፣ ይባስ ብሎ እስኪቀበር ድረስ ሆቴል ክፍል ውስጥ ሞቶ መገኘቱ ሳይወራ ድብቅ ሆኖ መቆየቱ በራሱ በጣም ደንቆኛል።

ጊዜና አጋጣሚ እድል የፈጠረላቸው ሰዎች በሚገኑበት በዚህ ሃገር ብዙ ሰርተው አሻራቸውን ያኖሩ ባለውለታዎች እንዲህ ሲድበሰበሱ ሳይ ማህበረሰቡ ለህትመት እና ለብሮድካስት ጋዜጠኞች ያለውን ሚዛን ፣ ከብሮድካስትም ቴሌቪዠን መዝናኛ ላይ ለሚሰሩ ሰዎች የሚሰጣቸውን ‘ዕውቅና’ እያሰብኩ የጋዜጠኝነት ሙያና ማህበረሰቡ ሙያና ባለሙያውን የሚረዳበትን ክፍተት አስባለሁ።(በዚህ ጉዳይ ሌላ ቀን እጽፋለሁ) ።

ወደገነነ አሟሟት ልግባ። (ትንተናዬን ያንተራስኩት በኢትዮፒካል ሊንክ ላይ ከሰማሁት መረጃ ላይ ብቻ መሆኑን ልብ በሉልኝ።)

በዊልቼየር ላይ ነበር የተባለው ገነነ ለስራ ከገባበት ጊዮን ሆቴል በወደቤቱ ሳይመለስ ቀረ።ሁለት ቀን ሙሉ ሲጠፋ ከቤተሰቡ ‘የት ገባ’ ብሎ ተጨንቆ የፈለገው ሰው አለመኖሩን ነው የተረዳሁት። ገነነ “ስልኩን አጠፋ” ተብሎ ብቻ ሊታለፍ የሚገባው ሰው ነው ? ….ዘመዶቹ…ወዳጆቹ..ባለቤቱም ጭምር ምን ያህል ..የት ርቀት ድረስ ሄደው ፈለጉት? ይህን ያህል ታዋቂ የሆነ ሰው ሲጠፋ በተገኘው መንገድ ሁሉ ‘ፈልጉልኝ’ አይባልም?…ወድቆ ቀርቶስ ቢሆን? ለያውም በዊልቼየር ያለ ሰው…ቢያንስ የተጠለለበት የ ‘ዋአካን ሆቴል’ ሰዎች እኮ ያውቁታል። ጠፋ የሚል ወሬ ቢሰሙ እኛጋ ነው ፣ ኑና ውሰዱት ማለታቸው አይቀርም ነበር።

እዚህ ላይ መረጃው ገነነ ከቤተሰብ በተለይ ከባለቤቱ ጋር የሆነ አለመግባባት አንደነበረው እንዳስብ አድርጎኛል።በተለይም ከሁለት ቀን በኋላ “እዚህ ነኝ ያለሁት” ያለው ሰይድ ኪያርን ከሆነ ለባለቤቱ መንገር ያልፈለገበት ምክንያት ነበረው ማለት ነው። ወደቤቱ መመለስ አልፈለገም ማለት ነው። ባለቤቱም ‘የጠፋው’ ባሏ ተገኝቶ ስኳሩ ወርዷል ስትባል ሚሪንዳ አዝዛለት ብቻ አለ የተባለበት ሆቴል ሳትሄድ ቀረች መባሉም የሁለቱ ግንኙነት ቅሬታ ው

See Insights and Ads

Boost post

Like

Comment

Share

Exit mobile version