ETHIO12.COM

“ሁሉም ከዚህ ይጀምራል!” የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚያም ሟርትን የሰበረ፤

አዋጅ ፣ አዋጅ ታሪኩን በሚመጥን መልኩ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ግንባታው ተጠናቋል። የዓድዋ በዓል በደረስ ጌዜ ሁሉ ሲያፈርሱትና በሴራ ሲንጡት የነበሩ ዛሬ ምን ይሉ ይሆን? አዋጅ ዋጅ የዓደዋ ድል ከምንግዜውም በላይ አበራ!! ዓደዋ የትቁር ህዝቦች ታሪክ ዕለት ዕለት ይዘከር፣ የከበር፣ የወሳ፣ የጎበኝ፣ ትውልድ ይታነጽበት ዘንድ ህያው ሆነ።

በመሃል አራዳ ጊዮርጊስ፣ አዲስ ታሪክ ተሰራ። በዚህ አብረቅራቂ የታሪክ ስፍራ “ሁሉም ከዚህ ይጀምራል!” የሚል ነጥብ ተቀምጧል። ዓድዋ በጨለማ ውስጥ ብርሃን፣ በአይቻልም ውስጥ ይቻላልን ያሳየ ሲጀምር የኢትዮጵያ፣ ሲቀጥል የአፍሪካ፣ ከዛም የዓለም ሁሉ ጥቁሮች ድል!!

የዓለምን የጭቆናና የነጮችን የበላይነት አነካክቶ ያደቀቀ መንፈስ አድዋ፤ እንደ ወንጌል ዕለት ዕለት ሊሰበክ የሚገባ ማተብ ዓድዋ፤ ኢትዮጵያ አንድነት ብቻ እጣ ክፍሏ መሆኑን ያረጋገጠችበት የህልውናዋ አክሊል ዓድዋ!!

በበላይነት ስሜት ለጥቁሮች አጥር፣ ገደብ፣ ደረጃ፣ ጣሪያና ልክ ሰፍረው ለተነሱ ወራሪዎች በቅጡ ምላሽ የተሰጠበት፣ ቀደምት የኢትዮጵያ ልጆች በአንድነት ተጋምደው ጠላትንም፣ ባንዳውንም እንደ አንድ ላይ የወቀጡበት፣ የኢትዮጵያን ኩራት በደምና በአጥንታቸው፣ ከምንም በላይ በእምነት ማተባቸው ያጸኑበት፣ አሁንም ወደፊትም ትውልድ በኩራት ማማው ላይ እንዲንፈላሰስ ያስቻለ ዓድዋ!!

1 / 7

በየዘመኑ ትርፍራፊ ለቃሚዎች፣ የባንዳነት ምስ የተጣባቸው እንግዴዎች፣ ከከፍታ ይልቅ መርመጥመጥን ክብራቸው ያደረጉ ቢያሟርቱበት፣ ሊያጣጥሉት ቢሞክሩ፣ የሴራ መዓት ቢጎነጉኑ … አልቃሽ መስለው ሊንዱት ቢጋጋጡ ፣ ዓድዋ መንፈሱ እየለበለባቸው ዛሬ ላይ ተደረሰ።

በቅርቡ እንደታየውና እንደተሰማው ደረት ደቂዎች፣ ቅጥረኞችና ለጠላት ያደሩ ሟርተኞች የፖለቲካ ስካራቸውን ለማስፈጸም የአዝማቹን አጤ ሚኒሊክን መታሰቢያ ሃውልት ተደግፈው በበሬ ወለደ ደጋግመው አፍርሰዋታል። እመታሰቢያው ስር ሆነው ዓመጽ ጠርተው የአንድነቱን ካስማ ሊንዱ የቻሉትን ሁሉ ድንጋይ ፈንቅለዋል። ጉድጓድ ምሰዋል። በቅንጥብጣቢ ለቃሚ ሚዲያዎቻቸው ያለ አንዳች ሃፍረት ይህንኑ የትርምስ አጀንዳቸውን አናፍሰዋል። ሃቁ ግን ዓድዋ መድመቁ ነው።

የዓድዋ ሚስጢር ያልገባቸው፣ ዓድዋ አንድነት የታተመበት፣ አንድነቱ በደምና አጥንት የታተመ መሆኑን ያልተረዱ በፈጠራ የስልጣን ጥማትና የተላላኪነት ሴራቸውን በአሉባልታ ሊያሳኩ ቢዳዱም አልሆነም። ይልቁኑም “አፍራሽ” የተባሉት ” ሁሉም ከዚህ ይጀምራል” ብለው ጀምረው፣ የዓድዋን የአንድነት መንፈስ ተቋድሰው፣ ከዓድዋ ድል ‘ይቻላልን’ አንግበው፣ ከዓድዋ ‘ በጣጥሶ መውጣትን’ ተምረው የዓድዋ ድል መታሰቢያን ለትውልድ የዕለት ተዕለት መማሪያ እንዲሆን አድምቀው አነጹት።

“የኢትዮጵያውያን የአብሮነት፣ የአንድነትና የአሸናፊነት ተምሳሌት የሆነው የዓድዋ ድል የታሪክ ስብራት የሚጠግንና ለትውልድ የሚተላለፍ ህያው ታሪክ ሆኖ በመገንባቱን እንኳን ደስ አለን” ሲሉ ከንቲባዋ አጭር ስንኝ ጽፈዋል። ነገ እሁድ እንደሚመረቅ ይፋ አድርገዋል። የቀድሞ ከንቲባ ታከለ ኡማ አሻራቸው ትልቅ ነውና እዚህ ስፍራ ድርሻ አላቸው።

ለትዝታ ከዚህ ስር ያለውን ያንብቡ

አባቶች በልጆቻቸው ፊት ክብራቸው እንዳደፈ ሸማ በነተበበት ዘመን፤ ሚስቶች መከታ ጋሻየ ብለው በሚያምኑባቸው ባሎቻቸው ፊት በጭካኔ በተደፈሩበት ወቅት፤ ህፃናት በጨቅላነታቸው የልጅነት ጨዋታን ተነፍገው የነጭ ህፃናት መጫወቻ በሆኑበት በዚያ መራር የፅልመት ዘመን ይሆናል ተብሎ የማይገመት ይቻላል ተብሎ የማይታሰብ ነገር ሆነ፡፡

መላው አፍሪካዊያን በባርነት ረግረግ በሚዳክሩበት ወቅት፤ ከወደ ጦቢያ ህልም የሚመስል ወሬ ተሰማ፡፡

ድፍን የጦቢያ ህዝብ ሀገሩ መወረሯን ሲሰማ፤ ገበሬው ሞፈርና ቀንበሩን ሰቀሎ ጦርና ጋሻውን አነገበ፤ በሮቹን ወደ በረት ከትቶ የጦር ፈረሶቹን አሰገረ፤ሸማኔው ማዳወሪያውን አሽቀንጥሮ ጎራዴውን ታጠቀ ፤ የሚወዳቸው ሚስትና ልጆቹን ተሰናብቶ ወደ ጠላት ገሰገሰ፡፡

ነፃነትን ተነፍጎ ሽህ አመት ከመኖር ለነፃነቱ ሲፋለም ነፃ ሁኖ ዛሬውኑ መውደቅን የመረጠው ድፍን ጦቢያ ህዝብ ለጠላት መትረየስ ደረቱን ሰጥቶ ወደፊት ገሰገሰ፡፡ ከጣሊያን መትረየሶች ድምፅ ይልቅ የአርበኞች ፉከራና ቀረርቶ የአድዋን ተራራ አናወጣት፡፡ እስከ ጉልበቱ የሚደርስ ቦቲ ጫማ አጥልቆ ከመጣው የጣሊያን ወታደር ዳና ይልቅ በወጉ ስንቅ እንኳን ሳይቋጥር ወደ ጠላት የተመመው አርበኛ የባዶ እግር ኮቴ ድፍን ምድሪቱን ናጣት፡፡

ዘላለም ይላል አባቶቻችን እና እናቶቻችን ሕይወት ከፍለው ስለ ሰጡን ስጦታ “ነፃነት” ዛሬ ነፃ ሰዎች ነን፡፡ በባርነት ጭነት ቅስማችን ያልተሰበረ፤ በጭቆና ቀንበር ልባችን ያልተሸበረ፤ ጎንበስ ማለት የሚያንገሸግሸን: ቀና ብለን ኖረን ቀና እንዳልን ማለፍ የሚናፍቀን፤ የነጮችን ጥቃት ለመቋቋም ቆዳችን የሚሳሳብን፤ አልደፈር ባይ የጥቁር አፈር ትንታጎች ነን፡፡

ሙሉውን እዚህ ላይ ያንብቡ

Exit mobile version