ETHIO12.COM

ዘመቻ ሀሰን ሼክ መሃሙድ ” ኢትዮጵያ አላከበረችኝም”፣ መንግስት ” መሳሪያ መያዝ ክልክል ነው”

መድረክ ላይ የታዩ የአፍሪካ መሪዎችም ሆኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት ” ስለ ልዩ አቀባበልና መስተንግዶ እናመሰግናለን” ሲሉ ምስጋና የሚሰጡትን የክብር አቀባበል የሶማሌ ፕሬዚዳንት “ኢትዮጵያ አላከበረችኝም” ከማለታቸው ጋር አብሮ የሚሄድ አልሆነም። ለዚህም ይመስላ አብዛኞች የሶማሌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጫ የመጨረሻ አንቀጽ ላይ አትኩሮ የሰጡት።

የሶማሌ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሆነ ያለውን እንደሚያወግዝ ካስታወቀ በሁዋላ ” … It may be necessary for the African Union to reevaluate the location of its headquarters” ይህ የግብጽ የዘላለም ምኞትና ሴራ የምትጎነጉንበት አጀንዳ በመግለጫው መጨረሻ ላይ መካተቱ የቅሬታውን መነሻ እንደሚያሳይ አስተያየት እየተሰጠ ነው። መግለጫው ላይ የተቀመጠውን ይህንኑ አሳብ በማጉላትና በቀለም በመለየት በርካቶች ” እንዲህ ነው ጨዋታው” እያሉ በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩት ነ እንደሂነ ለመመልከት ተችሏል።

” የአፍሪካ ህብረት ምን አልባትም የዋና ጽህፈት ቤቱን መቅመጫ ስለመቀየር ሊያስብበት ይገባል” የሚል ምክርና ማሳሰቢያ የሰጠችው ሶማሊያ ዋና ከተማዋን እንኳን በወጉ ማስጠበቅ ሳትችል ኢትዮጵያ ላይ በዚህ ደረጃ ዘመቻ ለማካሄድ መንፏቀቋ ” ተልዕኮ ተቀባይ” እንደሆነች በግልጽ እንደሚያሳይ አብሮ እየተጠቆመ ነው።

ፕሬዚዳንቱ በሰጡት ማብራሪያ በሶማሊያ የሚገኘውን የኢትዮጵያን ሰላም አስከባሪ ” እንደ ሌሎች የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ” ሲሉ ምስጋና እንኳን አልቸሩትም። በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ደምና አጥንት፣ በኢትዮጵያ ድጋፍ መሽቶ የሚነጋላቸው ሼክ ሀሰን መሃሙድ ” ኢትዮጵያ ከሶማሊ ላንድ ጋር ስምምነት ከፈጸመች በሁዋላ አልሸባብ የሶማሊያን ድንበር አስከብራለሁ በሚል እስከ ሰባት ሺህ አዲስ ምልመል ወታደሮች ሰብስቧል። ይህ ሽብርን ያባብሳል” ሲሉ እግረመንገዳቸውን ጉዳዩን ለያወሳስቡ ሞክረዋል።

37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ ሲጀመር ሀሰን ሼክ መሀሙድ ” ወደ ስብሰባው እንዳልገባ የመከልከል ሙከራ ተደርጎብኛል ” የሚል ክስ ቢያሰሙም ስብሰባው ላይ ታድመው ታይተዋል። ከስብሰባው መክፈቻ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ በዝግ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ለመሳትፍ ሲንቀሳቀሱ የኢትዮያ የፀጥታ ኃይሎች ለጊዜው ካረፉበት ሆቴል እንዳይወጡ መንገድ ዘገተውባቸው እንደነበርም አመልክተዋል።

” ስለ አቀባበሉና ልዩ መስተንግዶ እናመሰግናለን” የተባለውን ኢትዮጵያን በአቀባበልና በመስተንግዶ የከሰሱት ፕሬዝዳነቱ ይህን ቢሉም በስብሰባው መሳተፋቸውና በስብሰባው መክፈቻ የቤተሰብ ፎቶ ላይ መካተታቸው ታይቷል።

ይህንኑ ተከትሎ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባሰራጨው መግለጫው ፤ ” የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሊያ ፕሬዝዳንትና ልኡካቸው ወደ 2024 የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ እንዳይገቡ ያደረገውን ሙከራ የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ መንግስ በጽኑ ያወግዛል” ሲል ጀመሮ ” የኢትዮጵያ መንግስት ድርጊት የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ደንብን የሚጥስ ነው ፤ የአፍሪካ ኅብረትን የቆየ ባህል የሚቃረን በመሆኑም ህብረቱ ጉዳዩን በገለልተኛ ሆኖ እንደሚረምር ” የሚል ጥያቄ አቅርቧል። ከላይ እንደተባለው “የህብረቱ ጽህፈት ቤት ከአዲስ አበባ እንዲነሳም” ሲል አለሳልሶ መክሯል። ይሁን እንጂ ወደ ሞቃዲሾ እንዲዛወር ፍላጎት እንዳለው ፍንጭ አልሰጠም።

ሲጀመር ለክብር አቀባበሉ ክብር ያልሰጡት የሶማሊያው ፕሬዚዳንት አቶ አሕመድ ሽዴ አቀባበል አድርገውላቸው እጅ ለጅ ተያያዘው በሞቀ ፈገግታ ሰላምታ ሲቀያየሩ በምስልና በቪዲዮ ታይቷል። የሶማሊያ ህዝብ መዝሙር በክብር ዘብ ታጅበው ከተዘመረ በሁዋላ የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ሲዘመር የክቡር ዘቡን ክብር ነግፈው፣ አቶ አህመድ ሸዴ ቆመው እያለ እሳቸው ጥለው እየተጎማለሉ ሲሄዱ የሚያሳይ የንቀት ቪዲዮ ተሰራጭቷል። ይህም ድርጊታቸው ከጅምሩ ሌላ አላማ ይዘው መምጣታቸውን የሚያሳይ እንደሆነ እንደማሳያ እንደሚቆጠር ቪዲዮውን በቴሌግራም ያጋሩ ጽፈዋል።

ይህን ነውር ትቶ የኢትዮጵያ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት የኢትዮጵያ መንግሥት ለአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ለመጡ ሁሉም ሀገራትና መንግስታት መሪዎች ያደረገውን የክብር አቀባበል ለሶማሊያ ፕሬዚዳንትም ማድረጉን አስታውቋል።

“እንደ አስተናጋጅ ሀገር ኢትዮጵያ የሁሉንም ሀገራትና መንግስታት መሪዎችን በቆይታው ደህንነታቸውን የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት። ነገር ግን የሶማሊያ ፕሬዝዳት ልኡካን በመንግሥት የተመደቡላቸውን የፀጥታ አካላት አንቀበልም ብለዋል።” ያለው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት፣ የሶማሊያ ልዑክ የደህንነት አባላት የጦር መሳሪያ ታጥቀው ወደ አፍሪካ ኅብረት ለመግባት ሲሞክሩ በኅብረቱ የፀጥታ አካላት መከለከላቸውን ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት እና የልኡካቸውን ደህንነት ከመጠበቅ ባሻገር በስብሰባው ላይ እንዳይገኙ የተፈጸመ አንዳችም ተግባር እንደሌለ፣ ወደ ኅብረቱ ቅጥር ጊቢ እንዳይገቡም ያገዳቸው አካል እንደሌለ መግለጫው አመልክቷል። ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር ቁርጠኛ አቋም አላት።

የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ሆነ ፕሬዚዳንቱ በአፍሪካ ህብረት መሪዎች ስብሰባ ላይ መሳሪያ ይዞ መግባት የተፈቀደ ስለመሆኑ ያሉት ነገር የለም። አሰራሩን የሚያውቁ እንግዶቹ ሁሉ የኢትዮጵያን ምድር ሲረግጡ ጥበቃቸውና ደህነታቸው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስት ሃላፊነት እንደሚሆን፣ በጉባኤ አድራሽ መሳሪያ ይዞ መግባት ፈጽሞ የተከለከለ እንደሆነ ገልጸዋል። ሌሎች በርካታ የጸጥታ ፕሮቶኮሎችም አሉ።

የሁሉም አገራት መሪዎችና ከፍተኛ ባለስልጣናት ይህን አክብረው ሳለ የሶማሊያው መሪ ነፍጥ በታጠቁ ጠባቂዎቻቸው ታጅበው ህብረቱ ጉባኤ አዳራሽ ለመግባት የፈለጉበት ምክንያትም ምን እንደሆነ አልሳታወቁም።

Exit mobile version