Site icon ETHIO12.COM

ዳንኤል በርሄ “ትህነግ ለትግራይ አዲስ ታቦት ሆናለች፤ እንደ ፊውዳሉ ዘመን ሌላው ህዝብ ማዳመቂያ ነው”

ከጦርነቱ በፊት ተንታኝና የትህነግን የጦርነት ዕቅድ በማስረዳት ሰፊ ተሳትፎ የነበረው ዳንዔል በሃኔ “ትህነግ ለትግራይ አዲስ ታቦት ሆናለች፤ እንደ ፊውዳሉ ዘመን ሌላው ህዝብ ማዳመቂያ ነው” ሲል በይፋ መናገሩ መነጋገሪያ ሆነ። በቅርቡ የተደረገውን ስብሰባ ” ሁሉም ነገር ሙልጭ ብሎ ጠፍቶ የሚካሄድ አድክም ነው” ሲል ወረፈ።

በርካሄ ሾው በሚባል የዩቲዩብ አውድ ላይ ዳንዔል እንዳለው ትህነግ አዲስ የትግራይ ታቦት ሆናለች። ለዚህም ምክንያቱን ሲያስረዳ ትህነግ ላለፉት ሰላሳና አርባ ዓመታት የትግራይን ህዝብ ዋና እሴት በስልት ወደ እራሱ አዙሮ “እምነት” እንዲሆን አድርጓል።

“እንደሚታወቀው” ይላል ዳንዔል እንደሚታወቀው የትግራይ ሕዝብ አማኝ ነው። ኦርቶዶክስ ነው፤ ታቦት ያለመልካል። ይህን እሴቱን በስልትና በቀስታ ትህነግ ወደ ራሱ በመቀየር የትግራይ ታቦት አድርጎ እንዳስቀመጠ ያስረዳል።

“ትህነግ ታቦት” እነደሆነች ሲያጸና “ታቦት እንደሚመለክ ሁሉ እነሱም ሁሉንም ካዳሚ አድርገውታል” ብሏል። ” ትህነግ ለትግራይ ህዝብ ይጠቅማል?” በሚል ለቀረበለት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ” ፊት አውራሪ መሸሻን ታውቂያቸዋለች” በማለት ነበር። የፊውዳሊዝምን ተግባር በፍቅር ታሪክ አዛብተው ዶክተር ሃዲስ አለማየሁ የጻፉት ፍቅር እስከመቃብር ላይ የሰፈሩትን ፊት አውራሪ መሸሻን በማንሳት ያጣቀሰው ዳንዔል፣ ” በዛ የፊውዳል ዘመን ሌላው ህዝብ ማዳመቂያ እንደነበረ ሁሉ አሁንም የትግራይ ህዝብ ማዳመቂያ ነው” ሲል የትህነግን አካሄድ ስልሳ ዓመት ወደሁዋላ ሄዶ ለማሳየት ሞክሯል።

“የትግራይ ህዝብ ማዳመቂያ ነው” ሲል የገለጸው ዳንዔል “ፊውዳል” ሲል የሳላቸውን የትህነግ ሰዎች በስም ባይጠራም ንግግሩን የሰሙ በአስተያየታቸው አቶ ስብሃት ነጋንና የእሳቸውን ሃረግ ሲጎትቱ ታይተዋል።

የትህነግን ሽንፈት ተከትሎ ጠፍቶ የነበረው ዳንዔል እየሳቀ ” እንዴት በዚህ ዘመን ሶስት ወር ስብሰባ …” ካለ በሁዋላ ከት ብሎ እየሳቀ ” አሁን ሁሉም ነገር ሙልጭ ብሎ ጠፍቶ” ሲል ይህን ያህል ስብሰባ መቀመጥ ለምን እንዳስፈለገ በመገረም ሲናገር ተስተውሏል። እንድ እሱ ገለጻ አሁን ላይ ሶስት ወር ለመሰብሰብ የሚያስችል ቁመናም፣ ምክንያትም የለም።

“ትህነግ ለትግራይ ህዝብ ይጠቅማል?” የሚለው ጥያቄ ሰፊ ቢሆንም ካረጀ የፊውዳል ዘመን አስተሳሰብ ጋር ሰፍቶ ” ሌላው ህዝብ ማዳመቂያ” እንደሆነ ያሳየው ዳንዔል፣ “ትህነግ ከሌለ ትግራይ አትኖርም” በሚል ዕምነት ሌላ አማራጭ ማየት ላቃታቸው የማንቂያ ደወል ሲልሆን አዲስ እሳቤ ትግራይ ውስጥ ለመጀመሩ ማሳያም ተደርጎ ተወስዷል።

ቢቢሲ በትግራይ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች የሚያስተምሩ የክልሉ ተወላጆችን በማነጋገር ባሰራጨው ጽሁፍ ባልተለመደ ሁኔታ ትህነግ መዘለፉ አይዘነጋም። ቢቢሲ ላይ አስተአየት የሰጡት እንዳሉት “ይህነግ አርጅቷል። የተናቀ ሆኗል። ዋጋ የለውም” የሚሉ ጥቅል አሳቦች ይገኙበታል።

ትህነግ የካቲት 11 ባከበርበት ሰሞን ብቅ ብሎ አስተአየቱን የሰጠው ዳንዔል ለትግራይ ህዝብ በትህነግ ዙሪያ መከደም እንጂ ሌላ አማራጭ እንዳይኖረው መደረጉን፣ ከዚህ በፊት ባልታየ መልኩ መናገሩ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።

በትህነግ መከፋፍለና የተለያዩ ጉዳዮች ሲፈጠሩ ለወራት መሰብሰብ ልማድ እንደሆነ ያወሳው ዳንዔል፣ የመለስና ስዬ የግል ጸብ፣ ተንባርካኪነት የሚባልበት ወቅትና ቦና ፓርቲዝም በሚል ረዣዥም ስብሰባዎች ሲካሄዱ ” ቢያንስ ምክንያት አለ” ይልና ” አሁን ሁሉም ነገር ሙልጭ ብሎ አልቆ መሰብሰ” ብሎ መገረሙን በሳቅ ያሳያል።

“ሃድነት” ወይም “አንድነት” በትግራይ ትልቅ እሴት መሆኑንን አመልክቶ፣ ትህነግ ይህን እሴት “ወደ ትህነግን መካደም” ለውጣዋለች ሲል ዳንዔል አመልክቷል። ዳንዔል በጦርነቱ ወቅት በረሃ መግባቱና ራሱን ሸሽጎ ይኖር እንደነበር አይዘነጋም። ቪዲዮውን በፊስ ቢክ ገሻን ከዚህ ዜና ስር ይመልከቱ::

Exit mobile version