Site icon ETHIO12.COM

የፊልድ ማርሻሉ ሰውኛ ማብራሪያ – “ፖለቲከኞች ባህሪያቸው መመርመር አለበት”

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ደረጃው ቢለያይም በየወቅቱ “መርመጥመጥ” እጅግ የተለመደ ነው። ዓይነቱ ቢለያይም “ባንዳነት” ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያ መከራዋ ነው። ከኢትዮጵያን ታሪካዊ ጠላቶቿ ጋር አብሮ ኢትዮጵያን መብላት፣ ሕዝቧን ማሰቃየት፣ ሃብቷን ማውደምና ዘርፎ ለዘራፊ ማስረከብ፣ ማደህየት፣ ቅርሶቿን ማስጋዝ የመሳሰሉት የክህደት ታሪክ አለን። ይህ አይካድም። ለወራሪ አድረው አገራቸውን የካዱ ታሪካቸው ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል። የሌሎቹ ኩሩ ወገኖች ወርቅ ታሪክ ከብሮ እንደሚታየው !!
ዛሬ ላይ ይኸው የቀደመው ክህደት አድጎ በዲጂታል ሚዲያ ታጅቦ ሲወደስ እየተሰማ ነው። ያገኘቱንና የቀረበለቸውን ሳይመረመሩ እንዳለ የሚውጡ መኖራቸው፣ ማሰላሰልና መመርመር ብሎ ነገር አለመኖሩ ደግሞ ለእንደዚህ አይይነቶቹ አጋጣሚውን ውብ አድርጎታል። እንዲህ ያሉት የክህደት አርበኞች ከውጭ አገር አካላት ድጋፋቸው ሰፊ ነው። ድጋፉ የሚቀጥለው ኢትዮጵያ ስትታወክና በድንብ ስትናጥ በመሆኑ ይህንኑ የክህደት አጀንዳ ለማስፈጸም የሕዝብን ስም አንጠልጥለው ይነሳሉ። የትግራይ፣ የኦሮሞ፣ የአማራ ህዝብ እየተባለ የተፈጸመው ሁሉ የዚህ ማሳያ ነው። አሁንም እየተፈጸመ ነው። በገዚር እንድተያየው ከሆነ ህዝብ አልቋል። ንብረት ወድሟል። አገር ደህይታለች። ህጻናት ትምህርት ቤት መዋል አልቻሉም። ህክምና ፣ ትምህርት፣ የእለት ተዕለት አገልግሎትና ትራንስፖርት ተስተጓጉሏል። ዝርፊያው ድርጅትም ሆነ አገልግሎት አልመርጥም። አፈናና እገታው ዓይን ያወጣ ሆኗል። ይህ ሁሉ የሚሆነው “እንታገልልሃለን” በሚባልለት ህዝብ ላይ ነው።
ለዚህ ይመስላ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ቀደም ካለው በተለይ ይህን ጉዳይ ያጎሉት። “የኢትዮጵያ ህዝብ ስማ” ሲሉ ማስተዋል ግድ እንደሆነ አመላክተዋል። “እጃችን ላይ ኢትዮጵያ አትፈርስም” ካሉ በሁዋላ ” ሊያፈርሱንና ሊስቁብን የተዘጋጁ አሉ” ሲሉ ህዝብ ረጋ ብሎ እንዲያስብ መክረዋል። የመንግስት ሚዲያዎችንም ” የት ናችሁ” ሲሉ ወቅሰዋል።
በዝቋላ አራት አባቶች መገደላቸውን አንስተው ” ጽንፈኛው ሃይል መንግስት ገደለ አለ” ያሉት የአገር መከላካከያ መሪ ” አባቶቹ የተገደሉት ገዳዮቹ ኑ ብለው የጠሯቸው ቦታ እንጂ ገዳሙ ውስጥ አይደለም። ለምን ሄዱ፣ ማን ጠራቸው? እንዴት ተገደሉ? ለም ተገደሉ?…” የሚለውን አጣርቶ መዘገብ የሚዲያው ተግባር ቢሆንም ይህ ሲሆን አለመታየቱን አጽንዎት ሰጥተው ወቅሰዋል።
“ጄኖሳይድ ተፈጸመ። መከላከያ ህዝብ ጨፈጨፈ” እንደሚባል አንስተው ” የደጋፊ የስልክ መረጃ ተቀብሎ ሪፖርት ያድረገውን ተቋም ሚዛናዊነት ጥያቄ ውስጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ከትህነግ ጦርነት ጊዜ ጀምሮ የተዓማኒነት ችግር የሚታይበትን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በስም ባይጠሩም ተግባሩ አሳዛኝ መሆኑንን አመልክተዋል።
ፊልድ ማርጫሉ አያይዘውም ከተወካዮች ምክር ቤት ተከሰተ የተባለውን ግድያ በአካል ሄደው ለማጣራት ጠይቀው አውሮፕላን አቅርበው ማስተናገዳቸውን አስታውቀው፣ ” ሚዲያው የት ነው” ሲሉ ኮንነዋል። ራሱን በተሃድሶ አዘምኗል የተባለው የአገሪቱ ሚዲያ ዘመናዊ ስቱዲዮ ባለቤት ከሆነ በሁዋላ ብዙ ቢጠበቅበትም የተባለውን ያህል አልሆነም።
“የፈጠራ ወሬ የገቢ ምንጭ ነው” ሲሉ ፎልድ ማርሻል ብርሃኑ አስታውቀው፣ የአገሪቱ ሚዲያ እውነቱን ሁሉንም ወገን አናግሮ ማጋለጥ ካልቻለ ምን ሊሰራ ነው? ሲሉ ጠይቀዋል። የተወሰኑ የዩቲዩብ አውዶችን አመስግነው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ” ሚዲያው እውነቱን በማጋለጥ ረገድ ለምን አይረዳንም” የሚል ጥያቄ እንደሚያነሱላቸው አመልክተዋል። ፊልድ ማርሻሉ በርካታ ጉዳዮችን በግልጽ አንስተዋል።
“ልጄ እንኳንም አባትህ ካድሬ ያልሆነ። ልጄ አባትህ ካድሬ ባለመሆኑ ዕድለኛ ነህ። እኔም ሳላስበው ካድሬ ሳልሆን ኖርኩ። ዕድለኛ ነኝ። ካድሬ ባህሪው ከትክክለኛ ሰውነት ያፈነገጠ ነው … ዛሬ ስለሚናገረው እንጂ ትናንት ወይም ከዛ በፊት ስለተናገረው ደንታ የለውም። ካድሬ ከሰውነት የጎደለ ነው … ” በማለት አስተያየት የሰጡ እንግዳን ማቀረባችን ዛሬ ላይ የፊርድ ማርሻሉ ወግ አስታወሰን።
ይህ አስተያየት የተሰጠው አቶ ጌታቸው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድ ሆነው በተሾሙ ማግስት ስለ ሰላም የፌደራል መንግስትን አድነቀው በተናገሩበት ወቅት ነው። ምድር ላይ ያሉ የማቆሸሻ ቃላቶችና አገላለጾችን በሁሉም ዓይነት ሚዲያዎች ያለማቋረጥ በኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያ መከላከያና በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ ሲረጩ የነበሩት አቶ ጌታቸው፣ ከዚህኛው ጫፍ ተስፈንጥረው አመስጋኝ ሲሆኑ ” አይ ካድሬነት” በሚል በርካቶች ግርምታቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም።
አቶ ጌታቸው ረዳ በጦርነቱ ወቅትና ቃላት ሳይመርጡ ሲያራክሱዋቸው በነበሩት፣ እጃቸውን እይዘው እስር ቤት እንደሚከቷቸውና እንደሚቀጡዋቸው በመጥቀስ ሲዛበቱባቸው በነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሹመት ሲሰጣቸው መቀበላቸው፣ ስልጣን ከተቀበሉም በሁዋላ ያለ ሃፍረት እሳቸው ፊት ቆመዋል። ደጋግመው ስብሰባ ተቀምተዋል።
ይህንኑ ተከትሎ ህሊናና ሞራል እንዳለው ሰው ምን እንደተሰማቸው እሳክሁን በይፋ ተጠይቀው በተለመደው አንደበታቸውም ቢሆን ምላሽ አልሰጡም። “ግፋ በለው” እያሉ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆችን ስለማስጨረሳቸው ዛሬ “ፕሬዚዳንት” ሲባሉ ምን እንደተሰማቸው የሚታወቅ ነገር የለም። በዝግ ስብሰባ ሳይቀር ዓይናቸውን በጥቁር መነጽር ከመሸፈን የዘለለ የተነፈሱት ነገር የለም። ያም ሆኖ “ካድሬ ህሊናው የደረቀ ፍጡር ነው” ለሚለው ስያሜ የዘመኑ ግንባር ቀደም የትውልድ ማስተማሪያ ሆነው ተወስደዋል። ዝርዝሩን ባይገልጹም በሳቸው ቅስቀሳዎች ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ፊልም እየተሰራ እንደሆነ የጠቆሙ አሉ።
ፊልድ ማርሻል ብረሃኑ ጁላ አጃኢብ የሆነባቸው ይህ በቅጽበት ከአንድ ጽንፍ ወደ ሌላ ጽንፍ የሚደረግ የካድሬዎች መስፈንጠር ነው። ስም ባይጠቅሱም ” የፖለቲከኞች ባህሪ ሊመረመር ይገባዋል” ሲሉ በመደነቅ አስተያየት ሰጥተዋል።
በደንብ የሚያውቋቸውና ንግግር አድምጠው ግምገማ የሚሰጡ ስለ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተደጋጋሚ ምስክር ሰጥተዋል።ቀጥታ ተናጋሪ ናቸው። ማሽሞንሞን፣ ማድበስበስ አይችሉበትም። ወታደር ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን ይህ ሰውኛ ባህሪያቸው ነው። ካድሬ ስላለሆኑ …
ስለ ኦነግና የቀድሞ አመራሮችና ስለ አሆኑ የኦሮሞ ሰራዊት እንቅስቃሴ፣ ስለ ትህነግ የጦርነት አካሄድ፣ ስለ አማራ ክልል ቀውስ አንስተው ሲያብራሩ ከቆዩ በሁዋላ የሶማሌውን መሪ አንስተው ጥቂት ከተከዙ በሁዋላ፣ “የፖርቲከኞች ባህሪ ሊመረመር ይገባል” አሉ። ስለ አገር ላይ በአጠቃላይ የመከላከያ ቁመናና ተጋድሎ ዙሪያ ማብራሪያ ሲሰጡ “ይህ ከአንድ ጫፍ ወደ ሌላ ጫፍ በቅጽበት የሚደረግ መስፈንጠር የፖለቲከኞች ባህሪ ሊመረመር ይገባል” በማለት የቆየ ጭንቀታቸውን አደባባይ አውጥተውታል።
የሶማሌን ስልሳ በመቶ የሚሆነውን ግዛት የኢትዮጵያ መከላከያ እያስተዳደረው እንደሆነ ጠቁመው፣ ኢትዮጵያ ይህን ባታደርግ የሶማሌ መንግስት ሊቆም እንደማይችል አስታውቀዋል። ለዚህ ረዥም ዓመታት የቆየ የኢትዮጵያ መስዋዕትነት የሶማሊያ መንግስት ምስጋናው ልዩ እንደነበር አውስተው አሁን ላይ ያለውን ዘለፋ ” ክህደት፣ ለስማሊያ ሰላም በሞቱ ወታደሮች ደም ላይ የተፈጸመ ክህደት” ብለውታል። ይህንንም አስታከው ነው ከኢትዮጵያ የውስጥ ፖለቲካ ሽኩቻ ጋር አይይዘው ” የፖለቲከኞች ባህሪ መጠናት አለበት” ያሉት።
ትናንት በግፍ የታረደው መከላከያ ሰራዊት ደሙ ሳይጠግ፣ በአማራ ክልልም ተመሳሳይ ድርጊት እንደተፈጸመበት በማንሳት ድርጊቱን “ክህደት” ብለውታል። “እዛም እዚህም የተቀመጡ ድጋፍ ሰጪ ሬጅመኖትች” ያሉዋቸው የመከላከያ አባላት ከትህነግ የተኮረጀ በሚመስል መልኩ በአማራ ክልል በራሳቸው ወገን ጥቃት እንደተሰነዘረባቸው ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናግረዋል።
ይህ የክልሉን መንግስት አፍርሶ ወደ አራት ኪሎ ለመገስገስ “የህልም እንጀራ ጋግሮ” የተነሳው ሃይል ከትህነግ ጋር ጦርነት ሲካሄድ ቀድሞ ሲደራጅ እንደነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ተገልጿል። ” እናውቅ ነበር” ሲሉ ብርሃኑ ጁላ እንዳሉት ይህ ሃይል የክልሉን ልዩ ሃይል በሃሰተኛ ፕሮፓጋንዳና በተጠለፈው መዋቅር ተጠቅሞ አስከዳ። የታጠቀውንም መሳሪያ ወሰደ። ይሁን እንጂ ይህ ሃይል በአብዛኛው አሁን ላይ ተመቷል። መሳሳቱ የገባው ስልጠና ወስዶ ወደ ነበርበት አቋሙ ተመልሶ እይሰራ ነው።
እዛም እዚህም እሳት የሚለኮስባት ኢትዮጵያ ስነ ልቦናዊ ውቅሩም ሆነ አደረጃጀቱ ኢትዮጵያ ላይ የሆነው የአገር መከላከያ እያለ ምንም እንደማትሆን የገለጹት የጦር መኮንኑ ” የኢትዮጵያ ህዝብ ስማ … እጃችን ላይ ኢትዮጵያ አትፈርስም፤ ግን በጥሞና አስብ” ብለዋል።
በውጭ ሃይሎች ድጋፍና ፍላጎት የፈረሱትን አገሮች ስም ዘርዝረው አሁን ላይ የሚገኙበትን አሳዛኝ ሁኔታ በማንሳት “እዚህም ሊሆን የማይችልበት አማጋጣሚ የለም”” የኢትዮጵያ ህዝብ አስብበት” ሲሉ ተደምጠዋል።
አሁን ላይ በአማራ ክልል እስር ቤት ሲሰበር ያመለጡ ወንጀለኞች ካልሆኑ በስተቀር ሌላ አስቸጋሪ ሃይል እንደሌለ አመልክተዋል። ከእስር ያመለጡት በርካታ ነብስ እጃቸው ላይ ያለ፣ በአካባቢው ባህል መሰረት ተመልሰው ሰላማዊ ኑሮ ለመኖር በቀልን የሚፈሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል። እነዚህ ደመኞች ሃያና አስር ሰው በመያዝ በየጥሻው፣ በየገዳሙ፣ በየቤተክርስቲያኑና በየሸለቆው ስለሚዘዋወሩ ለማደን ጊዜ እንደሚፈጅ አስታውቀዋል። አያዘውም ፖሊስ፣ ሚሊሻና የክልሉ አድማ በታኝ በሚገባ እየተዋቀረ ስለሆነ መከላከያ ለነሱ እንደሚያስረክብ አመልክተዋል። ይህም ሆኖ ግን ንግግር ብቻ ስለሚያዋጣ ወደ ሰላማዊ መገድ እንዲመጡ መክረዋል።
ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የሚለው ሃይል አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መመታቱን ገልጸው፣ የቀሩት ጥቂት የማይሞቱና በቅርብ ቤተሰቦቻቸውና በሚያምኗቸው እየተጠበቁ ከሚነቀሳቀሱ በቀር ይህ ነው የሚባል ተዋጊ ሃይል እንደሌላቸው ጠቁመው ዳግም ወደ ሰላም እንዲመጡ መክረዋል። የኦሮሞ ልጆችን ከማስጨረስ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። ኦሮሞ ዛሬ ላይ ያልተመለሱ ጥያቄዎች እንደሌሉት ገልጸው ካሉም በውይይት ብቻ ሊፈታ እንደሚገባ አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ እጅግ ዘመናዊ መሆኑንን፣ ውጊያ ለመምራት ተራራ ላይ መቆምን አስቀርቶ ከቢሮ ውስጥ ሆኖ ውጊያን የሚመራ፣ የተላትን አቅም በአንዴ አንብቦ አሰላለፉን የሚቀይር፣ እጅግ የዘመነ አየር ሃይል የገነባ በመሆኑ፣ ከምንም በላይ በብሄር ተጠልፎ እዛና እዚህ የሚነጉድ ባለመሆኑ አሁን በተያዘው መንገድ መንግስት ለመሆን እንደማይቻል ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ አስታውቀው ” የህልም እንጀራ ጋግራችሁ፣ እውነተኛ አታስመስሉት” ሲሉ ታጣቂ ሃይሎቹ የውጭ ሃይሎችን አጀንዳ ተሸክመው ህዝብ ከማስጨረስ የጸዳ ዓላማ ይዘው ወደ ድርድር እንዲመጡ መክረዋል።
በትግራይ የተካሄደው ውጊያ በፍጹም ሊደረግ የማይገባው እንደነበር በማስታወስ፣የአገር መከላከያ ከተመታ በሁዋላ የተጀመረው ጦርነት ያስከተለውን ውጤት እንዴት ለሌሎች ትምህርት መሆኑ ሲገባው ዳግም አማራ ክልል መድገም ፍጹም ያልተገባ መሆኑንን አመልክተዋል።
አማራ ክልል አሁን ላይ ዝርፊያ፣ ሰው መግደል፣ ማፈንና በየስርቻው እየተዘዋወሩ ህዝብን ከማሰቃየት የዘለለ ይህ ነው የሚባል የተደራጀ መከላከያን የሚፈትን ሃይል እንደሌለ ጠቅሰው የሰጡትን ማብራሪያ ከስር ቪዲዮውን ያድምጡ

Exit mobile version