Site icon ETHIO12.COM

ሮይተርስ ወደ አዲስ አበባ፤ ጃዋር ማናገር ቅድሚያ ነው፤50 ሰዎችን መርጠዋል፤ መንግስት ቅድሚያ ወደ ማይካድራ ይላል፤

ኢትዮ 12 ዜና – ሮይተርስ ሃምሳ የተመረጡ ሰዎችን በምርጫና በትግራይ ቀውስ ጉዳይ ለመንጋገር ወደ አዲስ አበባ እንደሚያቀና ኢትዮ 12 ሰምታለች። እንደ ወሬው ከሆነ ሮይተርስ አስገራሚ የተባሉ እቅዶች የያዘ ሲሆን ሊያገናቸው ካሰባቸው ሰዎች አንደኛ ደራጅ ስሙ የተጻፈው አቶ ጃዋ መሐመድ ነው። የሮይተርስ ጉዞ የዶክተር ደብረጽዮንን ጥሪ ተከትሎ መሆኑ መናበብ ያለ እንደሚያስመስል ታዛቢዎች እየገለጹ ነው።

የተለያዩ ቋንቋ የሚናገሩ አስተርጓሚዎችን መልምሎ ወደ አዲስ አበባ ለማቅናት ባለፈው ሳምን አሜሪካ ኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኙት የሮይተርስ ሰዎች ከአምባሳደር ፍጹም ጋር ተነጋገረዋል። የኤምባሲው መረጃ ምንጭ እንዳሉት ጋዜተኖቹ ወደ አዲስ አበባ ሲሄዱ የሙያ ስራ ፈቃድ ኤምባሲው እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ምን ለመስራት እንደሚሄዱም ጥቅል መረጃ ሰጥተዋል።

በሰጡት መረጃ መሰረት በአንደኛ ደረጃ በሊስታቸው የያዙት ቃለ ምልልስ ተደራጊ አቶ ጃዋር መሐመድ ሲሆን፣ አቶ ጃዋር በህግ ጥላ ስር ስለሚገኝ እስር ቤት ገብቶ ለማነጋገር እድሉ ጠባብ እንደሆነ ተነግሯቸዋል።

ወደ ትግራይ በማቅናት ነሳ ሆነው ሪፖርት ለማተናከር እንደሚፈልጉ የገለጹ ሲሆን፣ ምርጫውን ተንተርሶ ወ/ሮ ብርቱካንን ለማግኘት እቅድ ይዘዋል። ከምርጫው አጀንዳ ጋር ዶክተር ብርሃኑ ነጋን ያናገራሉ። ሌሎች ተቃዋሚዎችም ተካተዋል፤ አቶ ልደቱም አሉበት።

ሮይተርስ የስብአዊ መብትን አስመክቶ ሊሰራ ላሰበው ሪፖርት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤልን በቀለን ለማናገርና የሪፖርቱ አካል ለማድረግ አልፍለገም። ወይም በሊስቱ ውስጥ የሉም። ይልቁኑም የናይሮቢው የአምነስቲ ተወካይ አቶ ፍስሃ ተክሌ አዲስ አበባ እንዲመጡ እቅድ ተያዟል። አቶ ፍስሃ ከለውጡ በሁዋላ የተዛባ ሪፖርት በማቅረብ የሚወነጀሉና ድርጅታቸው እሳቸው በሰጡት መግለጫ ይቅርታ መጠየቁ አይዘነጋም።

መንግስት የህግ ማስከበር በሚለው ዘመቻ የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ላይ ለተፈጸመው ጭፍጨፋ ብዙም ዋጋ ከማይሰጡት መካከል አንዱ እንደሆነና ታማኝነት እንደሚጎድለው መንግስት የሚተቸው ሮይተርስ ለአምባሳደር ፍጹም ያቀረበው ጥያቄ በፍለገው መልኩ ባይመለስለትም ረቡዕ አዲስ አበባ እንደሚገባ ስምተናል። የተለየ ምክንያት ከሌለ በስተቀር አስር አባላት የያዘ ቡድን ወደ አዲስ አበባ ይዞ የሚያቀናው ሮይተርስ ማይካድራ ተገኝቶ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ እማኞችን ተይቆ ለመዘገብ እቅድ ባይዝም በኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄ እንደሚዘግበው ተገምቷል።

የሮይተርስን ጉዞ አስመልክቶ ያነጋገርናቸው እንዳሉት ” ጉዳዩ ዶ/ር ደብረጽዮን ተናገሩት ተብሎ እየተሰራጨ ላለው የድረሱልን ጥያቄ ማስደገፊያ ሪፖርት ለመስራት በመናበብ የሚከናወን ይመስላል። የኢትዮጵያ መንግስት እግር በግር እየተከተለ ማስተባበያ ማዘጋጀትና ህዝብ ምስክርነቱን እንዲሰጥ ልዩ ጥረት ማድረግ የገባዋል” ብለዋል። አያይዘውም መንግስት ፈቃድ መስጠቱን አድንቀው፣ ጎን ለጎን ደግሞ ጨውና ገለልተኛ የሚላቸውን ሚዲያዎች በመጋበዝ ወደ አንድ ወገን በማጋደል ዘገባ የሚሰሩትን ክፍሎች ማጋለጥ እንደሚገባው ገልጸዋል።

በመጨረሻ ባገኘነው መረጃ ሮይተርስ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ለማነጋገር እቅድ የያዘ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጊዜ እንደማይኖራቸው፣ ሌሎች የሚመለከታቸውን ባለስልጣናት ስራቸው ላይ ስለሆኑ እንደማንናውም ሚዲያ ሊስተናገዱ እንደሚችሉ በኤንባሲው በኩሎ ተገልጾላቸዋል።

Exit mobile version