Site icon ETHIO12.COM

ከሚከሰቱ ሁነቶች ጋር ተናባቢና ተዛማጅ የሆኑ ተግባራዊ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባም አርከበ ዕቁባይ ገለጹ

“የሚወጡ ዕቅዶችና የሚቀመጡ ግቦች እንደ ዶግማና ርዕዮተ ዓለም ሳይቆጠሩ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በማገናዘብ መስራት የኢኮኖሚ ዕድገት ያመጣል” ሲሉ የኢኮኖሚ ባለሙያው ዶክተር አርከበ ዕቁባይ ገለጹ።ዘለቄታዊ የኢኮኖሚ እድገትን ለማስመዝገብ የረጅም ጊዜ እቅድና ሰፊ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸውም ተናግረዋል። ከሚከሰቱ ሁነቶች ጋር ተናባቢና ተዛማጅ የሆኑ ተግባራዊ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል

በአለም ባንክ አዘጋጅነት በተካሄደ “የምስራቅ ኤዢያ – አፍሪካ፡ የዌቢናር ውይይት የተሳተፉት ዶክተር አርከበ፤ “በአፍሪካ የሚፈለገውን የምጣኔ ሃብት እድገት እና ልማት ለማስመዝገብ የረጅም ጊዜ ራዕይ በማስቀመጥ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል” ብለዋል።

እቅዶቹን ከመመሪያ ባለፈ ሰፊ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማካሄድ ወደ ተግባር መለወጥ እንደሚያስፈለግም ነው የጠቆሙት።“በተለይም የሚታቀዱ ዕቅዶችና የሚቀመጡ ግቦች እንደ ዶግማና ርዕዮተ ዓለም ከመቁጠር ባለፈ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችና በማገናዘብ ተግራባራዊነቱ ላይ መስራት ይገባል” ሲሉ አመላክተዋል።“ይህንንም ከቻይናና ኤዢያ አገሮች መማር እንችላለን” ነው ያሉት።

ሁሉንም አዋጭ ፖሊሲዎችና መንገዶች በመጠቀም በየጊዜው ከሚከሰቱ ሁነቶች ጋር ተናባቢና ተዛማጅ የሆኑ ተግባራዊ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባም ዶክተር አርከበ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version