Site icon ETHIO12.COM

ኢዜማ ለምርጫ ማስፈፀሚያ 100 ሚለዮን ብር እንደሚያስፈልገው አስታወቀ

ፓርቲው በቀጣይ ለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ላይ ለመወዳደር የሚያስችለውን የምርጫ ማስፈፀሚያ የሚሆን 100 ሚለዮን ብር እንደሚያስፈልገው አስታውቋል፡፡በዚህም የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እንዳዘጋጀ አስታውቆ በቀጣይ የካቲት 21 ቀን በግሎባል ሆቴል መርሃ ግብሩን ለማካሄድ ዝግጅት ማፀናቀቁን የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዘላለም ወርቅ አገኘው ተናግረዋል፡፡

በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ የተዘጋጀውን ከ 10 ሺ እስከ 50 ሺ ብር የሚደርስ ትኬት በመግዛትም ደጋፊዎቹ ፓርቲውን እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል፡፡እስካሁን ድረስ ድረስ ፓርቲው በ406 በሚሆኑ ወረዳዎች እጩዎችን መምረጡን በዚሁ መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡

በአጠቃላይም ፓርቲው የሚደርሱ 228 ቢሮዎችን መክፈቱን እንዲሁም በ10 ክልሎችና በ2 ቱ ከተመሰ አስተዳደሮች 435 ወረዳዎች ላይ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ የፓርቲው የግብአት አሰባሳቢ ኮሚቴ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡ በሔኖክ ወ/ገብርኤልጥር 28 ቀን 2013 ዓ.ም

Exit mobile version