ኢዜማ ለምርጫ ማስፈፀሚያ 100 ሚለዮን ብር እንደሚያስፈልገው አስታወቀ

ፓርቲው በቀጣይ ለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ላይ ለመወዳደር የሚያስችለውን የምርጫ ማስፈፀሚያ የሚሆን 100 ሚለዮን ብር እንደሚያስፈልገው አስታውቋል፡፡በዚህም የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እንዳዘጋጀ አስታውቆ በቀጣይ የካቲት 21 ቀን በግሎባል ሆቴል መርሃ ግብሩን ለማካሄድ ዝግጅት ማፀናቀቁን የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዘላለም ወርቅ አገኘው ተናግረዋል፡፡
በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ የተዘጋጀውን ከ 10 ሺ እስከ 50 ሺ ብር የሚደርስ ትኬት በመግዛትም ደጋፊዎቹ ፓርቲውን እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል፡፡እስካሁን ድረስ ድረስ ፓርቲው በ406 በሚሆኑ ወረዳዎች እጩዎችን መምረጡን በዚሁ መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡
በአጠቃላይም ፓርቲው የሚደርሱ 228 ቢሮዎችን መክፈቱን እንዲሁም በ10 ክልሎችና በ2 ቱ ከተመሰ አስተዳደሮች 435 ወረዳዎች ላይ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ የፓርቲው የግብአት አሰባሳቢ ኮሚቴ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡ በሔኖክ ወ/ገብርኤልጥር 28 ቀን 2013 ዓ.ም
Related posts:
የፓትሪያርኩ የውጭ ጉዞና - "ተቀነባብሯል" የሚባለው ሴራ እያነጋገረ ነው
በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕከተኛ ራሳቸውን አሰናበቱ፤ ለአራተኛ ጊዜ የተሰማው ስንብት አነጋግሪ ሆኗል
መከላከያ ምዕራብና ምስራቃ ወለጋን እያጸዳ ነው፤ በቤጊ ወደ ካምፕነት በተቀየረ ት.ቤት የነበረ የሸኔ ድርጅት ተደመሰሰ - ሸኔ አላስተባበለም
"ሚናችንን እንለይ" እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ሊጀመር ነው
በተሻለ ጥቅም ለትህነግ ነዳጅ በበርሜል ይሸጋገራል፤ ወልደያና ቆቦ ችግሩ ተባብሷል
Are There TPLF Ethiopia Insurgency Training & Support Operations In Uganda?
ቻናል 29 ትግራይና የታደሰ ወረዳ "የጦርነት ዝግጅት ጨርሰናል" ዜና
አሸባሪው - ህፃናቶችንና አዛውንቶችን በማስገደድ እንደሚማግድ እጃቸውን ለምዕ.ዕዝ የሰጡ ወዶ ገቦች ተናገሩ