ETHIO12.COM

ሀሰተኛ የገንዘብ ኖት በመስራት ወደ ገበያ እንዲገባ ሲያደርጉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ሀሰተኛ የገንዘብ ኖት በመስራት ወደ ገበያ እንዲገባ ሲያደርጉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉሀሰተኛ የኢትዮጵያን የገንዘብ ኖት በመስራት ወደ ገበያ እንዲገባ ሲያደርጉ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡ሀሰተኛ የኢትዮጵያን የገንዘብ ኖት በመስራት ወደ ገበያ እንዲገባ ሲያደርጉ ከነበሩ ሶስት ተጠርጣሪዎች መካከል ዮሴፍ ተከስተብርሃን እና ተክለብርሃን ገ/መስቀል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታቋል፡፡

No photo description available.
እጅ ከፍንጅ የተያዘ ሃሰተኛ የብር ኖት

ግለሰቦቹ በቡድን በመደራጀት ሃሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን አትመው ሲያሰራጩ መቆየታቸውን የጠቆመው ፖሊስ ኮሚሽኑ ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት በተደረገባቸው ጥብቅ ክትትልና ድንገተኛ ፍተሻ 40 ሺህ ሃሰተኛ ባለ አንድ መቶ ብር የገንዘብ ኖቶች ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል፡፡

በቁጥጥር ስር ያልዋለውና የቡድኑ አባል የሆነው ሶስተኛው ተጠርጣሪ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ተሳትፎ እንደነበረው በፖሊስ ምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን ግለሰቡ ለጊዜው ቢሰወርም በደህንነትና በጸጥታ አካላት ክትትል ስር መሆኑን ከፖሊስ ኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡እንዲህ አይነቱ ወንጀል እንዲፈፀም የሚያመቻቹ እና ህብረተሰቡን የሚያሳስቱ ደላሎች መኖራቸውን በመገንዘብ ህብረተሰቡ ለጸጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ENA

Exit mobile version