Site icon ETHIO12.COM

ባለፉት ስድስት ወራት 83 ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር የተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት ስድስት ወራት 83 ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር የተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰቡን አስታወቀ

ባንኩ ውጤት ካስመዘገበባቸው ዘርፎች የደንበኞች የተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ ሲሆን በግማሽ ዓመቱ ባንኩ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን አዳዲስ የተቀማጭ ሂሳቦች ተክፍተዋል፡፡

የዕቅዱን 221 በመቶ በማከናወን ተጨማሪ 83 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ሊያሰባስብ ችሏል፡፡

አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ ክምችቱም 678 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ይህም ከዕቅድ በላይ የ107 በመቶ ክንውን አሳይቷል፡፡ የባንኩ ደንበኞች ቁጥርም 27 ነጥብ 5 ሚሊዮን ደርሷል፡፡ የባንኩ ጠቅላላ ሀብትም 903 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገራቱን ለሚከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች ዋነኛ የፋይናንስ አቅራቢ በመሆን በግማሽ በጀት አመት ውስጥ 47 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር አዲስ ብድር አቅርቧል፡፡

በተመሳሳይ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ሰብስበዋል፡፡

ባንኩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራባቸው ዘርፎች መካከል ለተለያዩ የመንግስትና የግል የልማት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያና ለገቢና ወጪ ንግድ የሚውል የውጭ ምንዛሪ በግማሽ በጀት አመት የ2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ማቅረብ መቻሉም ነው የተገለጸው፡፡

የባንኩን አገልግሎቶች ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈትና የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶችን በማቅረብ አበረታች አፈፃፀም ተመዝግቧል፡፡ 42 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት የቅርንጫፎቹን ብዛት 1,646 ማድረስ ችሏል፡፡

የኤሌክትሮኒክ ባንክ አገልግሎቶችን ለማዳረስ ባንኩ እያደረገ ባለው ጥረት አንድ ነጥብ 4 ሚሊዮን የኤ.ቲ.ኤም ካርድ፣ 9ሺህ 200 የኢንተርኔት ባንኪንግ እና አንድ ነጥብ 8 ሚሊዮን የሞባይል ባንኪንግ አዳዲስ ተጠቃሚ ደንበኞችን ማፍራት ተችሏል፡፡

በዚህም ከ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ የሲቢኢ ብር ደንበኞች እና ከ7ሺህ 600 በላይ የሲቢኢ ብር ወኪሎችን በመመልመል ወደ ስራ ማስገባትም ተችሏል፡፡

ባንኩ ካለፈው አመት ጀምሮ በሀገራችን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ፈተና የነበረውን የኮቪድ-19 በሽታ በመቋቋም መልካም አፈፃፀም ካሳዩ ባንኮች አንዱ በመሆን በአፍሪካ ከሚገኙ 100 ምርጥ ባንኮች መካከል የ17ኛ፣ ከምስራቅ አፍሪካ ደግሞ 1ኛ ደረጃ በመያዝ አመቱን ማጠናቀቁን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ via ኦቢኤን

Exit mobile version