ETHIO12.COM

« የኢሳያስ ጦር ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን እንደ በረከት፣ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት እቆጥረዋለሁ »

የአንድ ሉዓላዊ ሀገር መገለጫ ብሔራዊ ድንበር፣ ሰንደቅ አላማና መከላከያ ሰራዊት ናቸው፣ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ባላሰበው ሰዓትና ሁኔታ የወጋው ህወሓት ነው፣ ስለሆነም የህወሓት sympathizer ስለ ሉዓላዊነት የማውራት ሞራል የለውም፣ ርዕሰ ጉዳዬ የኤርትራ ጦር ትግራይ ውስጥ ስለመገኝቱና ስለ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ነው፣

ጉዳዩን እንደ ገለልተኛ አካልና እንደ ኢትዮጵያዊ (ለያይተን) እንመልከቱው፣ መጀመሪያ እንደገለልተኛ ወገን እንመልከተው፣

ወያኔ ቀን ከሌት የሚያልመው ሻቢያን ከስልጣን ማባረር ነው፣ ይህ ሁላችንም የምናውቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው፣ ስለዚህ ከጦርነቱ በፊት ወያኔ ለኤርትራ ቁጥር አንድ ስጋት (threat) ነው፣ ህወሓት ጡንቻውን አፈርጥሞ፣ ሮኬትና ሚሳኤልን ጨምሮ የሀገሪቱን 80% ከባድ መሳሪያዋች ታጥቆ ሲያበቃ ጦርነት ሲከፍት ለኤርትራ ከስጋትነት ወደ ግልፅና ወቅታዊ አደጋ (clear and present danger) ያድጋል፣ ስጋት ወደ ግልፅና ወቅታዊ አደጋ ሲያድግ ያለበት ቦታ ሂዶ በሚገባው ቋንቋ ማናገር የተለመደ አለም አቀፋዊ አሰራር ነው፣ ያንተ እዳ ስጋትህ ወደ አደጋ ማደጉን ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ማሳመን ብቻ ነው፣ አደጋው ካፈጠጠና ካገጠጠ ማሳመን ሁሉ አይጠበቅብህም፣ ኤርትራን/ ኢሳያስን የገጠመው እንዲህ ያለው ያፈጠጠውና ያገጠጠው አደጋ ነው፣ በዚህ የክርክር መስመር የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ መግባቱ ተገቢና ትክክለኛ ነው፣

ይህ አሰራር የተለመደ እና ምክንያቲያዊ እንደሆነ ከደርዘን የሚበልጡ ማሳያዋችን ማቅረብ ቢቻልም ለጊዜው መለስ ዜናዊን ብቻ አይተን እንለፍ፣

መለስ ዜናዊ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ ሁኖ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሶማሊያ ሲገባ “የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ኅብረት/ Islamic Courts Union” የሚባለው ቡድን ኢትዮጵያ ላይ ግልፅና ወቅታዊ አደጋ (clear and present danger) ደቅኗል ብሎ ነው፣ ይህን ተረት ተረት ይዞ የሄደው ወደ ፖርላማ ነበር፣ አብላጫው ወንበር የተያዘው በኢህአዴግ ቢሆንም በወቅቱ ልደቱ አያሌው፣ መራራ ጉዲና፣ በየነ ጴጥሮስ እና ሌሎች ጥቂት ተቃዋሚዋች ፓርላማ ውስጥ ነበሩ፣

ይህን ጉዳይ ፓርላማ ይዞ ሲሄድ “ግልፅና ወቅታዊ” ያለውን አደጋ በማያሻማ መልኩ ማቅረብ ተሳነው፣ መራራ ጉዲና ተቃውሞውን አስመዝግቦ ጦርነቱን ለመደገፍ እንደሚቸገር ገለፀ፣ ልደቱ አያሌው መራራ ላይ በንዴት ጡፎ ከፍ ዝቅ ካደረገው በኋላ በሀገራዊ ጉዳይ ላይ በጋራ አለመቆም ከሀገር ክህደት እንደማይተናነስ ለመራራ ነገረው፣ ልደቱ ከመለስ ጋር ነበር፣ መራራ ፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ ሆነ፣ አፈ ጉባኤው ድምፅ አሰጥቶ አዋጁን በአብላጫ ድምፅ ወደ ማፀደቅ ሊሄድ ሲል መለስ ዜናዊ ባልተለመደ ሁኔታ እጁን አወጣ፣ አሁን ከምናፀድቀው ኦፌኮ ከአባሎቹ ጋር መክሮበትና አስቦበት በሚቀጥለው ስብሰባ በሙሉ ድምፅ እናፅድቀው አለ፣ ሰውየው መለስ ነውና የፓርላማው አሰራር ተቀይሮ ውሳኔ ሳይሰጥበት ቀረ፣ በሚቀጥለው ስብሰባ መራራን “ምን ትላለህ?” አሉት፣ በአቋሜን አለወጥኩም ባይ ሆነ፣ ልደቱና መለስ ደነፋ፣ አዋጁ በአብላጫ ድምፅ ፀደቀ፣ መራራ ጉዲና ከዚህ የሚበልጥ ውለታ ከዛ በፊትም ሆነ ከዛ በኃላ አልሰራም፣ ወደ ፊት ታሪክ ይዘክረዋል፣

ለአቅመ ንባብ ስደር ስለ እስላማዉ ፍርድ ቤቱና መሪው ሼህ ዳሂር ሀዌስ ለማወቅ ሞክሪያለሁ፣ ይህ ቡድንና መሪው ለኢትዮጵያ አንዳች ስጋት እንዳልነበሩ ተረድቻለሁ፣ የእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረት የሚባለው ቡድን የዚያድ ባሬ መንግስት ሲወድቅና ሶማሊያ በጦር አበጋዞች ስር ስትወድቅ፣ ሰው ወጥቶ መግባት ሲሳነው ሰላም ለማስከበር በኮነሬል ዳሂር ሀዌስ የተቋቋመ ቡድን ነው፣ ሱማሊያን ወደ ሰላምና መረጋጋት መልሷት ነበር፣ አትፊውን ችሎት እያስቻለ ይቀጣው ነበር፣ ስያሜው ውስጥ “ፍርድ ቤት” የሚለው የተካተተው ለዛ ነው፣ ከተቋቋመው የቁጩ የሽግግር መንግስት በላይ ተወዳጅና ተቀባይነት የነበረው የሀዌስ ድርጅት ነው፣

መለስ ዜናዊ ያካሄደው ጦርነት አሸባሪ ላይ ሳይሆን እስልምና ላይ ነበር፣ it was a war against Islam. ስለ ጉዳዩ ከኢቲቪ ብቻ የሰማህ ከሆነ የምለው አይገባህም፣ I encourage you to do your own research. ይህ ዘመቻ አልሸባብን ፈጥሯል፣ የኢትዮጵያ ልጆች እንደ ቅጠል ረግፈዋል፣ እንደ ፕሮፌሰር መድሃኔ ታደሰ ገለፃ “ክርስትና ከእስልምና ጋር የሚያደርጉት ጦርነት” ሁኖ መልኩን ቀይሯል፣ ሊቢያ ውስጥ የታረዱት ወገኖቻችን አንደ ምክንያት ይህ ነው፣ አንዱ አራጅ ያለውን ሰምቻለሁ፣ ያለው ገብቶኛል፣ መለስ ዜናዊ ጥርስ ውስጥ ከቶን ነው የሞተው፣

ህዝባዊ መንግስት ሲቋቋም ሱማሊያን ይፋዊ ይቅርታ መጠየቅ ይኖርብናል፣ የመራራ ጉዲና ታሪካዊ ተቃውሞ ትጠቅመናለች፣ የመለስ ሀሳብና ምኞት ጦርነቱ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዳለው ለማሳየት ነበር፣ በነገራችን ላይ ለፖለቲካ ቅርብ የሆኑ ሱማሌዋች ነገሩን በደንብ ያውቃሉ፣ ለመለስና TPLF ያላቸው ጥላቻ እንዲህ ተብሎ የሚገለፅ አይደለም፣ ከTPLF አልፈው ትግሬን የሚጠሉ ገጥመውኛል፣

[ባለፈው ወዳጄ Kedir Endris የመለስን ፎቶ ለጥፎ ታሪክ በበጎ የሚዘክረው ስራ እንደሰራ ሲገልፅ በጣም ደንግጫለሁ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሀይማኖት ጭቆና እንደነበር አውቃለሁ፣ በዚህ ታሪክ ሁሉም የአለማችን ህዝቦች አልፈዋል፣ majority ክርስቲያ በሆኑበት ሀገር ሙስሊሞች ተጨቁነዋል፣ majority እስላም በሆኑበት ሀገር ክርስቲያኖች ተጨቁነዋል፣ ጭቆናው (ብዙ ጊዜ) እምነታቸውን practice እንዳያደርጉ ማድረግ ነው፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ሙስሊም profile የተደረገው ግን በመለስ ዜናዊ ነው፣ ሙስሊም እና ሽብርን አንድ ለማድረግ እንደ ጀሀዳዊ ሀረካት ያሉ ዶክመንተሪ ፊልም የሰራው መለስ ዜናዊ ነው፣ በየትኛውም የኢትዮጵያ ዘመን ክርቲያንና ሙስሊሙ እንደ ስጋት (አጥፊና ጠፊ) ተያይተው አያውቁም፣ መለስ የዘራት ዘር አሁንም አለች፣ ሙስሊም ሁኖ መለስን የሚያደንቅ ሰው ይገርመኛል ለማለት ነው]

ወደ ርዕሰ ጉዳዩ ስመለስ…..

እንደ አንድ ዜጋ የኢሳያስ ጦር ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን እንደ በረከት፣ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት እቆትረዋለሁ፣ think of this for a second..ይህ ጦርነት ከትግራይ ክልል ወጥቶ የነበረ ቢሆን ዛሬ ትግራይ ውስጥ ሆነ የሚባለው በሙሉ የድፍን ኢትዮጵያ እጣ ፋንታ በሆነ ነበር፣ የኤርትራ ሰራዊትና የአማራ ልዩ ኃይል እገዛ ባይኖር ኑሮ ሀገር አትኖረንም ነበር፣ ይሄን አትጠራጠሩ፣ የኤርትራ ሰራዊት ዋናው እርዳታው ወያኔ “preemptive strike” ያለችውን ማክሸፉ ላይ ነው፣ ሰራዊታችን ተረጋግቶ፣ ራሱን እንደገና አደራጅቶ፣ የትዕዛዝ መስመሩን ቀጥሎ ወደ ጦርነቱ እንዲገባ አይተኬ ሚና ተጫውተዋል፣

ከዚህ በፊት እንዳልኩት ኢትዮጵያን የሚጠብቃት አምላክ አላት የምትሉትን 80% ተቀብያለሁ፣

እናመሰግናለን ክብር ፕሬዝዳንት!

Via kasa Anbesaw Fb.

Exit mobile version