Site icon ETHIO12.COM

“ሦስተኛውን ‹የገበታ ለሀገር› ፕሮጀክት በወንጪ ከተማ አስጀምረና”

ጠ/ሚ ዐቢይ በወንጪ የሚገነባውን የገበታ ለሐገር ፕሮጀክት አስጀመሩአዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወንጪ የሚገነባውን የገበታ ለሐገር ፕሮጄክት በዛሬው እለት በይፋ አስጀመሩ፡፡በገበታ ለሀገር የሚለማው የወንጪ -ደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት በምዕራፎች ተከፍሎ የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል።

እጅ ያልነካቸው የወንጪ እና ደንዲ ያማሩ የእሳተ ገሞራ ሐይቆች በመጨረሻ ተገቢው ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ዛሬ ሦስተኛውን ‹የገበታ ለሀገር› ፕሮጀክት በወንጪ ከተማ አስጀምረናል። ይህ ፕሮጀክት መንገዶችን እና የኤሌክትሪክ ኃይልን ያስገኛል። የቴሌኮም አገልግሎቶችን በማሻሻል የግል ባለሀብቱ በኢኮ ቱሪዝም ዘርፍ ሙዐለ ንዋይ እንዲያፈስ ያስችላል፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ

የፕሮጀክቱ አስተባባሪና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ እንደተናገሩት፥ በመጀመሪያው ምዕራፍ የወንጪ እና ደንዲ ሃይቆችን የሚያገናኝ የአስፓልት መንገድ ይሰራል ብለዋል፡፡ከዚህ ባለፈም ፣ የጤና ማዕከል፣ የቴሌኮም ማሻሻያ፣ በግል ባለሀብቶች የሚሰሩ መዝናኛ ስፍራዎች እንዲሁም የትምህርት ማዕከል እና አነስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ይገነባልም ተብሏል፡፡

የፕሮጀክቱ አስተባባሪና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ፥ ፕሮጀክቶችን መጀመርና በፍጥነት መጨረስ ልምድ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡የወንጪ – ደንዲ የተቀናጀ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት የዲዛይንና የግንባታ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ዛሬ በይፋ ወደስራ መግባቱንም አንስተዋል፡፡ፕሮጀክቱ በተለያዩ ምዕራፎች ተከፋፍሎ እንደሚካሄድ ጠቅሰው፤ በመጀመሪያው ምዕራፍ ወደ ወንጪ ሃይቅ የሚወስደው የአስፋልት መንገድ፣ ሁለቱን ሃይቆች የሚያገናኝ የአስፋልት መንገድ፣ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት፣ የጤና ማዕከል፣ ትምህርት ቤቶች፣ የቴሌኮም ማሻሻያ ፕሮጀክት እንዲሁም በባለሃብቶች የሚገነቡ ደረጃቸውን የጠበቁ ማዕከሎችን የሚያካትት እንደሆነ ገልጸዋል።

በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳነ ጨምሮ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡በዓላዛር ታደለ


Exit mobile version