Site icon ETHIO12.COM

” በኢትዮጵያ ጥቅም አንገቴ ይቀላል እንጂ አልደራደርም፣ ተላላኪ መንግስት አይኖርም ” አብይ አሕመድ ዛሬ ምን አሉ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ” አንገቴ ይቀላል እንጂ በኢትዮጵያ ጥቅም አልደራደርም፤ ይህን እውቀቁት” ሲሉ ተጽዕኖ ለማሳደር ለሚሞክሩ አካላት ተናግረዋል። ዛሬ ለፓርላማ ባቀረቡት ንግግር ኢትዮጵያ ራስዋን ለማበልጸግ ከምናቸውም አካላት ጋር እንደምትሰራ ካስታወቁ በሁዋላ ነው ” ለመበልጸግ የሚጠመዝዙን አንቀበልም” ሲሉ ነው ያስታወቁት።

በምንም ምክንያት በኢትዮጵያ ተላላኪ መንግስት እንደማይፈጠር ስያታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዝብ እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ወጣቱ የአገሮኢቱን የህግ አስከባሪ ሃይል በመቀላቀል የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ አደራ ብለዋል። ከፌስ ቡክ ፉከራ የዘለለ ውሳኔ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

ጠላት፣ ወዳጅና እጅ ጠምዛዥ አገራት እንዳሉ ያስታወቁት አብይ አህመድ፣ ጥላ እንኳን በማታ ሲሸሽ፣ ጨለማ ባጋጠመን ወቅት የኤርትራ መንግስትና ሕዝብ ያደረገልን ውለታ በታሪክ የማይዘነጋ መሆኑ አመልክተዋል።አያይዘውም ለዚህ ውለታ ልዩ ክብር እንደሚሰጥ ካስታወቁ በሁውላ ” እንዲህ ላደረገለን ህዝብና መንግስት ስድብ እንድንመልስ የሚጠብቁ የዋሆች ናቸው” ሲል በግልጽ አመስግነዋል። ተፈጠሩ የተባሉ ችግሮችን ለመፍታት ውይይት እየተደረገ መሆኑንንም አመልክተዋል።

በትግራይ ዘረፋ፣ መድፈርና የመሳሰሉ ጥፋቶች ስለመፈጸማቸው የጠቆሙት አብይ አሕመድ ” መከለከያም ሆነ የኤርትራ ሰራዊት ወይም የአማራ ልዩ ሃይል ማታራት ተደርጎ ሲጠናቀቅ እርምጃ ይወሰዳል” ብለዋል። በዞኢህ ላይ ምን ልዩነት እንደሌለ አመልክተዋል። በተለያዩ ጉዳዮች ይህን ብለዋል

ነዳጅ

በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስፈልገን ሲሆን፣ መንግስት ከፍተኛ ድጎማ ያደርጋል። ለነዳጅ የሚደረገው የወጪ መጠን የውጪ ንግድ ገቢያችንን በከፍተኛ ሁኔታ ይወስድብናል። በመንግሥት ድጎማ አማካኝነት ከአጎራባች ሀገራት ባነሰ አንድ ሊትር ነዳጅ ለሽያጭ ይቀርባል። በአንድ ወር እንኳን መንግሥት 3 ቢሊየን ብር ድጎማ አድርጓል። ነዳጅ ከምንጩ እስከ ገበያው ድረስ ከፍተኛ ችግር ያለበት ሂደት ነው። ምንጩ ላይ በኮንትሮባንድ ይቸበቸባል። በቂ የሽያጭ መሰረት ልማት የለንም። ይህንን ማሻሻል ካልተቻለ የዋጋ ግሽበቱ ያሻቅባል። ድጎማው የሚደረገው ለሁሉም በመሆኑ፣ ከፍተኛ ገቢ ያላቸው የማኅበረሰብ ክፍሎችም በረከሰ ዋጋ ነዳጅ ያገኛሉ። ለትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ብቻ ድጎማ ማድረግ የሚልቻበት መንገድ ላይ መሥራት ያስፈልገናል።

ዘርፎችን በተመለከተ

ግብርናን ማዘመን ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል። ኩታ ገጠም እርሻ ሲስፋፋ ዘመናዊነት እና የምርት ዓይነቶችን ያበረታታል። መስኖ እና ውሀ የማቆር መልካም ጅማሮዎች አሉ። የጤፍ ምርት ስራው አድካሚ ስለሆነ፣ ዘርቶ ማጨድ የሚችል ዘመናዊ ማሽን ማስገባት ጀምረናል። የበጋ እርሻና መስኖ ማስፋፋትና የፋይናንስ አገልግሎት ማሻሻልም ትኩረት ተሰጥቶበታል። ከኢንደስትሪ አንጻር አሁን ያሉን ፋብሪካዎች ብቻ በግብአት፣ ሀይል፣ መለዋወጫ እጥረትና ቢሮክራሲ ምክንያት የሚያመርቱት ከአቅማቸው ግማሽ ያህሉን ነው። እነዚህን ማነቆዎች ብናስተካክል ምርቱ ሁለት እጥፍ ይሆናል። አንድ ፋብሪካ እንኳን ሲጨመር ሲሚንቶን ጨምሮ አቅርቦቶችን በማመቻቸት በገበያው ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያስከትላል።

በማዕድን ዘርፍ ትንንሽ ማሻሻያዎችን በማድረግ ብዙ ለውጥ ለማግኘት ተችሏል። ከወርቅ ባሻገር ሌሎች ማዕድናትም መገኘታቸው ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬን የሚያስገኝ ነው። ቱሪዝምም እንዲሁ ከፍተኛ አቅም እንዳለው እያየን ነው። በአይ.ሲ.ቲ. ዘርፍ ሁለት ሳተላይቶችን አምጥቀናል፣ የአርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ ሥራዎች እየተከወኑ ነው። የወንጀል መከላከል ሥራዎች ሊሰሩ ተጀምሯል። በተለይም ዳመናን ወደ ዝናብ የመቀየር ጥረት ተሞክሮ፣ በሰሜን ሸዋ እና ጎጃም ስኬታማ ሆኗል። ተስፋፍቶም ይቀጥላል። ሁሉም ዘርፎች ቴክኖሎጂን መጠቀም የሚያስፈልጋቸው ስለሆነ፣ ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶት ይቀጥላል።

የግብርና ካፒታል ለአርሶ አደሮች የሚደረገውን ብድር ሳይጨምር በ2010 ዓ.ም. 25 ቢሊየን ብር የነበር ሲሆን አሁን ወደ 34 ቢሊየን ብር አድጓል። ለግብርና 100 ቢሊየን ብር መመደብ ቢቻል የምናገኘውም ምርት የዚያኑ ያህል ይጨምራል። ባለፉት ሦስት ዓመታት ለመንገድ ከፍተኛ ውጪ ያወጣነው የመንገድ ችግር ሲፈታ የገበያ ትስስር እንደሚፈጠር በማመን ነው። የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ በጀት በሁለት ዕጥፍ ጨምሯል። የትምህርት ጥራትን ማስተካከል እና የትምህርት ሪፎርም ላይ ሲሰራ የሁለተኛ ደረጃ ምጣኔ አነስተኛ ስለ ነበር እርሱ ላይ ትኩረት ተደርጓል። በአስተዳደር፣ ሕግ፣ ገንዘብ አቅርቦት፣ ሙስናን መከላልከ አንጻር የተሰሩ ሥራዎች ተጨምረው የካፒታል ወጫችንን ለማሳደግ ችለናል።

የዋጋ ግሽበት

ላለፉት 15 ዓመታት እየተደማመረ የመጣ ችግር ሲሆን ከፍተኛ ተግዳሮት ሆኗል። ይህም የሚጎዳው ዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ ያለውን ሕብረተሰብ ነው። በአማካይ የምግብ ወጪ 54 በመቶ፣ የቤት ኪራይ 16-20 በመቶ፣ አልባሳት 5-6 በመቶ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሕብረተሰብ ክፍሎች ወጪ ናቸው። የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ቢሰራባቸው 80 በመቶ ጫና እናቀላለን ብለን እናምናለን፣ ያንን የተመለከተ ሥራ እያከናወንን ነው። የግብይት ሰንሰለትን ለማሻሻል መንግሥት ከግሉ ዘርፍ እየገዛ ማሰራጨት ጀምሯል። ነገር ግን ገና በቂ አይደለም። ግሽበቱን ለመቆጣጠር በሺህ የሚቆጠሩ ስግብግብ ነጋዴዎችን የመቆጣጥር እና ርምጃ የመውሰድ ሥራ እየተሰራ ሲሆን፣ የጋራ ጥረትን ይሻል።

የገንዘብ ስርጭት በ15 በመቶ፣ ቁጠባ 20 በመቶ፣ 38.4 የብድር አገልግሎት አድጓል። ኮንትሮባንድ እና ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት የተደረገው ጥረት የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ቀንሶ ገቢ እና ቁጠባ እንዲያድግ አስችሏል። 6.2 ሚሊየን ዜጎች የባንክ ሂሳብ ከፍተው 98 ሚሊየን ብር ቆጥበዋል። ይህም አርሶ አደሮችን ወደ ዘመናዊ የገንዘብ አያያዝ ለማስገባት የሚችል ሆኗል። የፋይናንስ ዘርፍ ምን ያህል ጤናማ መሆኑን ለመለካት እድል ሰጥቷል። የባንክ የገንዘብ ዝውውር ጣሪያ 730 ሚሊየን ብር ተብሎ የሚታሰብ ቢሆንም፣ 899 ቢሊይን ብር ገቢ ተደርጓል። ባለፉት 6 ወራት ብቻ 1.2 ትሪሊየን ብር ቁጠባ ተደርጓል።

የፊስካል ፖሊሲ አፈጻጸም ወጪና ገቢን በተመለከተ እድገት ቢታይም አሁንም ዝቅተኛ ነው። በ2010 ዓ.ም. እና በ2011 ዓ.ም. መካከል 20 በመቶ እድገት የነበረ ሲሆን፣ በ2012 ዓ.ም. ደግሞ 30 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። በዚህ ዓመት በስምንት ወር ብቻ 191 ቢ ብር ገቢ ተደርጓል፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የዓመቱን ገቢ ሊያክል ጥቂት የቀረው ቢሆንም ገና በቂ አይደለም። የካፒታል ወጪያችን በ2012 ዓ.ም. 124 ቢሊየን የነበር ሲሆን፣ 160 ቢሊየን የዚህ ዓመት በጀት ነው። የካፒታል ገቢ ሲጨምር ፕሮጀክቶች በሚፈለገው ልክ መጠናቀቅ ይችላሉ።

የማክሮ አኢኮኖሚ ጉዳዮችን በተመለከተሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያን በተመለከተ ዐበይት የትኩረት መስኮቻችን የብድር ጫና መቀነስ፣ መጠናቀቅ ያልቻሉና የሀገር ኢኮኖሚ ማነቆ የሆኑ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ እና ገቢን ማሳደግ ነበሩ። እንደ አንበጣ፣ ጎርፍ እና ግጭት የመሳሰሉ ትልልቅ ጋሬጣዎች ተደቅነውብን ነበረ። ማሻሻያው ሲታቀድ ኮቪድን ታሳቢ ያላደረገ ቢሆንም፣ ምላሽ መስጠት ነበረብን። በዚህ ሁሉ መካከል አኢትዮጵያ 6.1 በመቶ እድገት አስመዝግባለች።

Exit mobile version