Site icon ETHIO12.COM

አብይ አህመድ አስመራ እየመከሩ ነው፤ የጦር መኮንኖችና በመቶ የሚቆጠሩ ወታደሮች ተማረኩ

” በጨለማ ጥላ እንኳን ሲከዳ ላልተለዩን የኤርትራ መንግስትና ሕዝብ ልዩ ክብር አለን፣ ውለታውን አንረሳውም ” ሲሉ በአደባባይ ምስክርነት የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለስራ ጉብኝት አስመራ መግባታቸው ተሰምቷል።

በአዲስ አበባ የሚገኘውን የኤርትራ ኤንባሲ በመጥቀስ የመንግስት መገናኛዎች ዜናውን ይፋ አድርገዋል። ጉብኘቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ ማብራሪያ ሲሰጡ ያነሱትን ህግ የተላለፉ ወታደሮች ጉዳይ አስመልክቶ ለመነጋገር ይሁን ለሌላ ኤምባሲው ያለው ነገር የለም።

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለዶ/ር ዐቢይ እና በእርሳቸው ለተመራው ከፍተኛ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን አቀባበል አቀባበል ሲያደርጉ ታይቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ወደአስመራ ያቀኑበት ዋና ምክንያትና በቆይታቸው ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ስለሚወያዩባቸው ምክንያቶች በስፋት ባይገለጽም፣ ስለ ትህነግ መቸረሻ፣ በምስራቅ አፍሪቃ ሊፈጠር የሚችለውን የሁለቱ አገራት ህብረትና በህግ ማስከበሩ ዘመቻ ህግ ተላልፈዋል የተባሉትን የጦር ሰራዊት አባላት አስመልክቶ እንደሚወያዩ ተገምቷል።

ኤርትራ በተለይም ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ላይ ያተኮረውን የሃያላኑ ማስፈራሪያ የሚያስተነፍስ የጋራ ስልት እንደሚነድፉ እምነታቸው መሆኑንን የገለጹም አሉ። በምንም ይሁን በምን ሁለቱ መሪዎች ትህነግን እስከመጨረሻ ለማጥፋት የይዙትን አቋም ለአፍታም እንደማይቀይሩ የበርካቶች እምነት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ በተደረገ የህግ ማስከበር ዘመቻ አስራ ሁለት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መማረካቸውና መቶ የሚቆጠሩ የትህነግ ታጣቂዎች መማረካቸው ተሰምቷል። መረጃ የሚያደርሱን ክፍሎች እንዳሉት ይህ ሃይል እዚህ ግባ በማይባል የተኩስ ልውውጥ ነው እጁን የሰጠው። የህግ ማስከበሩ መንግስት የሰጠውን የሳምንት እድሜ በመጠባበቅ ላይ በመሆኑ ጥቃት የማድረግ ሃሳብ እንዳልነበረው አስታውቀዋል።

Exit mobile version